ጊዜውን ያላባከነ ሰው ሞተ አይባልም። አረፈ ይገልጽልኛል።

 

May be an image of 1 person and text
 
 
በሌላ በኩል ትውልድ የተካም ሞተ ሊባል አይገባም። ተክቷል እና። ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ሠርቷል። ጊዜው አልባከነም። እወላጅ አባቱንም፤ ባለቤቱንም በወል አጥቶ ያን ተቋቁሞ አገልግሎቱ ሳይቋረጥ ቀጥሏል። ጋዜጠኛው ፀጋውንም አልተላለፈም። ፀጋው ጋር ተዋህዶ ፀጋውን አስከብሮ በትውልዱ ድልድይ ሠርቶ፤ ባትሎ፤፥ተግቶ፤ ታትሮ ወደ ጠራበት ጽረ አርያም ሁሉንም ሰጥቶ ሳይሰስት፤ ሁሉንም ለግሶ ሳይንቆጣቆጥ እና ሳይለግም ወደ ዘላለማዊ ህይወቱ ገስግሷል። እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ መልዕክት፤ መክሊት፤ ጥሪ ይዞ ይወለዳል የምለው ፍልስፍና አለኝ።
 
እንዲሁም ትልቅ ሰው ሞተ አይባልም። ትልቅ ወንዝም ደረቀ አይባልም። ዕድሜ ዘመኑን ጥቅም ላይ የዋለ ቋሚ አሻራን በእጁ ያበጀ ትልቅ ሰው ህልው ነው። መንፈሱ ይኖራልና። ተግባሩ ይሰጣልና። ድርጊቱ ቁሞ ያስተምራልና። ዛሬ ጋሼ አማኑኤልን፤ ጋሼ ዘውዱን ጋሼ ተክሌ መጡብኝ። ድምፃቸው ሽው ውል አለብኝ። ሦስቱም የጀርመን ድምጽ የአማርኛ ቋንቋ ክፍል ባልደረቦች ኃላፊወች እና አስተዳዳሪወች ነበሩ። ለዛቸው ቃናቸው ጣማቸው ትውልድን በሙያ የመቅረጽ ቅንነታቸው ልዩ ነበር።
 
ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻም መልዕክቱን አድርሶ፤ ጥሪውን አንሰራፍቶ፤ መክሊቱን አቆላምጦ እና አለምልሞ የኖረ ሰው ነበር። ፍቅር ሰጥቶ ፍቅርን በገፍ ያለ ገደብ ያገኜም ዕድለኛም ሰው። ሚሊዮኖች የዚህ ዕድል ባለቤት ሳይሆኑ ያልፋሉ። እሱ ግን ዕድለኛ ነው። ሁሉን አይቶ፤ ሁሉንም አጣጥሞ ተወዶ፤ መውደድን አከፋፍሎ የኢትዮጵያን ህዝብ ታላቅነት በውል እንዲታይ ምክንያት ሆኖ አርፏል። እኛም ተከተይ ነን። ቀሪ የለም። ልጁን ጃፒ እና መላ የኢትዮጵያን ህዝብ ቤተሰቡን እግዚአብሄር ያጽና። ቢያንስ ለቀሩት ጋዜጠኞች ፍቅርን ክብርን እንለግስ። ጨምተን ታግሰን ጋዜጠኞችን እንውደድ። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን። 
 
"መሬት ነህና ወደ መሬት ትመለሳለህ።"
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
 
ሥርጉትሻ 2024/01/14

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።