ፀጋዬ ራዲዮ ላይፍ ላይ ነበር። ዛሬ ጥረ 14 ቀን 2021 የመጀመሪያ ሴንዱንግ ነበር ለአዲሱ ዘመን።

 ጋዜጠኝነት ነፍስን የሚገራ ልዩ ሙያ ነው። ከዚህ ሙያ ውጪ መኖር ህልውናን ማጣት ሆኖ ይሰማኛል። ኖርኩኝ እምለው የፀጋዬ ራዲዮን ፕሮግራም ስሰራ ብቻ ነው። ወዘተረፈ ፈተና ልክ በማይወጣለት ትዕግስት እና ቅንነት ከአለ አንድ አይዞሽ ባይ 16 ዓመት ተቆጠረ። ስፖንሰር የለውም። አጋዥ የለውም። ፈታኞቹ ሊያዘጉት የሚታትሩት የራሳችን ወገኖች ግን ብዙ ናቸው። ያው እኔ ሳልፍ የፀጋዬ ሥም መነሳቱ ይቆማል። ግን እነ ችኩል ይጣደፋሉ ስጠራ ለሚከረቸመው ይዋጋሉ። ያልታደሉ።!!!

 No photo description available.
 https://www.lora.ch/programm/alle-sendungen?list=Tsegaye
 
ፀጋዬ ራዲዮ ላይፍ ላይ ነበር። ዛሬ ጥረ 14 ቀን 2021 የመጀመሪያ ሴንዱንግ ነበር ለአዲሱ ዘመን። ራዲዮ ሎራ በሰባዕዊ መብት ጉዳይ የሚሠራ የኮሚቲ ራዲዮን ነው። ያው በወር እንደ አቅማችን ክፍያ እንከፍላለን። በኮሞሽን ነው የሚስተዳደረው። ኮሚሽኑ በአባለቱ የተመረጡ ናቸው። ደሞዛቸውን አባላቱ እና በጎ አድራጎት ድርጅቶች ይደጉሙታል። ማስታወቂያ አይሰራበትም። ክልክል ነው።
ሰፋፊ የሰባዕዊ መብት ዝግጅቶችን፤ ኮንሰርቶችን ያዘጋጃል። የጸጋዬ ራዲዮ በብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን ሥም የተመሠረተ ነው። ለእሱ መታሰቢያ ነው። ብዙ ፈተና አስተናግጄበታለሁኝ ዕጣ ነፍሴኢን። ያው በቅሎ መታዬት ጸሩ የሆነው ግንቦት 7 እስኪበቃው ታግሎታል።
ግን እስካሁን አልቆመም። አለ። የእኔ አስትንፋስ እስካለች ድረስም ይቀጥላል። ሥሙ ግን የቅኔው ልዑል ብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን ተተክሏል። ይህ ነበር ተጋድሎው። ተሳክቶልኛል። እአከ2008 አስከ 2021 ድረስ ቀጥሏል። 
 
ኢሳት ከመፈጠሩ በፊት የተፈጠረ ራዲዮን ነው። ብቻዬን ነው እምሠራው። አገር ማለት ምን ማለት ነው የሚል የልጆች ፕሮግራም ነበረው። እፍታ፤ ጠብታ፤ የወግ ገበታ፤ ውርሰ ጽናት የሚሉም ቋሚ ዝግጅቶቸን ሲያሰተናግድ ቆይቷል። 
 
ዛሬ 2021 ምን እንዳመላከተኝ አለወቅም ባሉኝ ማህበራዊ የትስስር መድረኮች ሁሉ አዬር ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ሼር አድርጌዋለሁኝ። ለምን ስለምን አላወቀውም። ቅጽበታዊ ውሳኔ ነው። ምን ሠራሽ የሚል ጥያቄ ከ5 ወር በፊት ቀርቦልኝ ነበር። በአንድ ሰው ክንድ ተዘርዝሮ የማይልቅ ተግባር ከውኛለሁኝ። አሻራዬ በአገርኛው ቋንቋ በጋዜጣ፤ በመጽሄት፤ በመጽሐፍ ታትሟል። ተመስገን ነው። ሎራን ለመጎብኘት፤ ለመገምገም የሚመጣ ማንኛውም አካል የሚቀጠረው በ በእኔ መሰናዶ እና ከእኔ ቀጥለውሎ በሚቀርቡት ዝግጅቶች ነው። ድንቅ ጊዜ አሳልፌበታለሁኝ። 
 
ፈተናውን የምታዩት ነው እኔ በአንድ ጉዳይ ከተጋሁኝ የተጋሁለት ድርጅት፤ ሰብዕና እራሱ እኔን ተጻሮ እኔን ይፎካከራል። እኔ ግን ምንግዜም መልካም ነገር ከማድረግ አልቆጠብም። ምርቃቴን መክሊቴን አልቀጣውም። አልቆነጥጠውም። ከአቅሜ በላይ የሆነ ስብራት ካልገጠመኝ በስተቀር። መጻፍ ስሜት ከተጎዳ ያቅታል። በተለይ የውስጥ ያደረግከው አምከንዮ ከሆነ። በቅንነት በድንግልና ከደከምክበት።
የሆነ ሆኖ ውዶቹ በሚቀጥለው 15 ቀንም በዕለተ ሃሙስ ከ15.00 እስከ 16.00 ድረስ ይተላለፋል። አባቴም ኢትዮ አፍሪካዊው ባለቅኔ እኔ እስካለሁ ድረስ ይነግሳል ሲዊዘርላንድ ዙሪክ ከተማ ላይ። አማርኛ ቋንቋም አጤ ይሆናል። ኢትዮጵያ አገሬም ትክበራለች ከነሞገሷ።
ሥረጉተሥላሴ
SerguteSelassie
ሰው እንሁን። እረሳችን እናሸንፍ።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።