#የአብን ዕርገት ወይንም ስርገት ቢያንስ አዲስ አበባ ላይ?
#ይህን የመንግሥት ብቻ ሳይሆን አቤቶ አብንም ሼር ማድረግ ይኖርበታል ችግሩን።
#አቤቶ የአዲስ አበባው ብአዴንም ከታጣፊ አልጋው ተነስቶ አንድ ሊለው ይገባል። እነ ዶር ሂሩት ካሳም።
////////-------------//////////
##ከአቶ ሳተናው በላይ ገፅ የተገኜ ዩአቶ አባይ ዘውዱ ዘገባ።
"ከተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ተፈናቅለው በአዲስ አበባ አስኮ መናኽሪያ የደረሱ ከ300 በላይ አማራዎች እርዳታ እየጠየቁ ነው።
አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ጥር 6 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ ሸዋ
ከኦሮሚያ ክልል በአማራዊ ማንነታቸው ተለይተው ጥቃት የደረሰባቸው ወገኖች አዲስ አበባ አሰረኮ መናኽሪያ ይገኛሉ።
የተፈናቀሉትም ከምስራቅ ወለጋ ዞን ስቡስሬ፣ ጎቡሰዮ እና ጉዳያ ቢላ እንዲሁም ከምዕራብ ሸዋ ዞን ባኮቲቤ ወረዳ መሆኑን ገልጸዋል።
ከጥር 16 ቀን 2014 ጀምሮ ተፈናቅለው አዲስ አበባ ከደረሱ በኋላ እየለመኑ ዘመድ ያለው በየዘመዱ፣ በየቤተ ክርስቲያኑ፣ በየመስጊዲዱ እና በየበረንዳው እየተጠለሉ መቆየታቸውን ይገልጣሉ።
አስኮ መናኽሪያ ውስጥ ነው ያለን ቁጥራችን ከ300 በላይ ይሆናል የሚሉት የአሚማ ምንጭ በማንነታቸው ምክንያት በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና በግብረ አበሮች መጠቃታቸውን አስረድተዋል።
መንግስትም ሆነ የሰብአዊነት ጉዳይ ይገደናል የሚሉ ወገኖች ትኩረት ነፍገውናል የሚሉት ተጎጅዎቹ ብርዱ፣ጸሀዩ እና ርሃብ እየተፈራረቀብን ለከፋ ችግር ተዳርገናል ብለዋል።
ድጋፍ የሚያሰባስቡ በጎፈቃደኞችም በከፍተኛ ስጋት ውስጥም ሆነው ከፖሊስ እየተሸሸጉ በጎ የሆነውን ነፍስ የማዳን ስራ እንደሚፈጽሙ ተናግረዋል።
ተፈናቃዮች ጥር 5 ቀን 2014 የተወሰኑ የፖሊስ አባላት ወደ አካባቢው በማቅናት አነጋግረው ከመሄድ ውጭ መፍትሄ እንዳልሰጧቸው ተናግረዋል።
"መ/ቤቱ ሁሉ ፊቱን አዙሮብናል" የሚሉት ተጎጅዎቹ አሁንም የድረሱልን ጥሪ እያረቡ ነው።
አሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና ግብረ አበሮቹ ታህሳስ 25 ቀን 2014 ከቀኑ 10 ሰዓት አካባቢም በስቡስሬ ወረዳ ወሊገልቴ በተባለ ቀበሌ ልዩ ስሙ ዲኒ አካባቢ ያሉ አማራዎችን "ለስብሰባ እንፈልጋችኋለን" በማለት ከ20 በላይ በሚሆኑት ቤቱን በማቃጠልና በጥይት መጨፍጨፋቸው ይታወሳል።"
አባይ ዘውዱ
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
14/01/2022
መጨረሻው ናፈቀኝ ………
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ