"የአማራ ፋኖ ትጥቅ እንዲፈታ ፌድራሉ ወሰነ" #ፋኖነት ደሜ ነው መለያዬ!
"የአማራ ፋኖ ትጥቅ እንዲፈታ ፌድራሉ ወሰነ"
ይላል ፋሲሎ ኤችዲ።
ይህ ማለት እያንዳንዱ የአማራ ልጅ ሲወለድ ፋኖ ሆኖ ነው የሚወለደው። አያውቁም። ጎንደር ልጅ ሲወለድ ቅቤ ይውጣል። ቅቤውን በአፈሙዝ እንዲውጥ ይደረጋል።
እኔ እራሴ አቀባብዬ መተኮስ እችላለሁ። ሰልጥኛለሁ። ብሄድ ቀጥታ ውጊያ ወረዳ መግባት እችላለሁ። የከተማ ልጅ ነኝ። ግን ትውፊታችን ያ ነው። ኮልቷ፣ ክላሽኗን ተንተርሼ ነበር እማድረው። አዋና። ጫካዋንም አውቃታለሁ። ጉድቧንም። አቀበት ቁልቁለቱንም። ቆላ ደጋውንም።
አትሰቡት። መላ ህዝቡ ይሸፍታል። ይሸፍትም! ያን ዘልዛላ የግርባው ብአዴን የምድር እንቧያችሁን ይዛችሁ ትቀራላችሁ።
የምርኮ አለቃችሁን ጅጅጋ መላካችሁን ሰምቻለሁ። ለምን እንደሆን አውቃለሁ። አቶ ሙስጠፌ ኡመር። ተራቸውን የሚጠብቁ ለእርድ የተዘጋጁ ቀጣይ ኢላማችሁ ናቸው። አማራ ክልል አንድ ነገር ስታስቡ ለሚዛን እምትሮጡት ጅጅጋ ነው። አይምሰላችሁ። ሲከር ይበጠሳል። ሲሞላም ይፈሳል።
አይደለም እናንተ ዲሞክራቶች በቀጣዩ ምርጫ የሚገጥማቸውን ፈተና ያወቁት አልመሰላቸውም።
የአማራ ህዝብ አቅሙ ያልናቃት፣ ያልሸፈተባት፣ ያልተዋት ኢትዮጵያ ናት። የትናንትም፣ የዛሬም፣ የወደፊትም የአቅማችን ፏፏቴ ከዛ ይመነጫል። ትንታጎችን ሚሊዮኖችን በዚህች ቅፅበት ታጣላችሁ። ድምፃቸውን አጥፍተው በዝምታ ውስጥ ያለ አሉና።
ምነው የእናንተ ኦነግ በጠራራ ጠኃይ ሥልጠና ሲወስድ፣ ሎጅስቲክስ ስታሟሉ አልጨነቃችሁ? ነፍሳችሁን ላቆዬ የአማራ ፋኖ ብድሩ ይህ ነውን? አትሰቡት። ሽፍትነት ከአፈሙዝ ይልቅ የህሊና ይብሳል። ጠያፎች!
የአማራ ፋኖ በአሸባሪነት ሊከሰስ ይችላል ስልም ነበር። ቀናጣ ያሉ ዕይታወችን ሳደምጥም እረፋ ስል ነበር። የአማራ የለም ቲወሪ አራማጁ የአቶ አንዳርጋቸው የፋሺዝም ቲወሪ ሁኑ ቅስቀሳ የአማራን ህዝብ በጆኖሳይድ ለማስጠዬቅ ነው። ከወሰን አትለፋም ብያለሁ።
አሁን ደግሞ እርቃናችሁን ኑሩ እዬተባለ ነው። ጥጋብ በዛ። ልኩን ላላወቅ በልኩ ይኖር ዘንድ ማሳወቅ ይገባል። ያን ጣፊያ ድርጅት ብአዴንን ትተህ ጀግናዬ፣ መኩሪዬዬ፣ አለኝታዬ ፋኖ እራስህን አድምጥ! ጠላት ይራድ! ይንቀጥቀጥ! ያርግድ!
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
12/01/2022
ፋኖነት ደሜ ነው መለዬዬ!
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ