12.01.2020 ከቶ አሁንስ ተረኝነት አለመሆኑን ተረዳን ይሆን?

 

ከቶ አሁንስ ተረኝነት አለመሆኑን ተረዳን ይሆን?
 
ይህ መከራ ማለዳነቱ ለኢትዮጵያ ነው። አፍሪካም ቀጣይ ናት። የፖለቲካ አስተሳሰቡ ከፍ ወደ አለ ደረጃ ማደግ አለበት የምለው ለዚህም ነው። የሶልዳሪቲ ትግልም ያስፈልጋል የምለውም ለዚህ ነው። ጉዳዩ የተረኝነትም፣ የፈረቃም አይደለም። ከዛ ከፍ ያለ ነው። የኦሮሚያ አገራዊነት ዕወጃ ነው። የአማራ ሊሂቃን የተጨፈጨፋበት ሚስጢርም ይኽው ነው። የሰኔ 15 ቀን 2011 ዓም ትልም ይኽው ነበር እገታ።
አዲስ አበባን ለኦሮምያ ርክክቡ የተፈፀመው መስከረም 5 ቀን 2011ዓም ነው። ኢትዮጵያም እንዲሁ። ዕውነቱ ይህ ነው። ስለዚህ በስክነት ቀጣዩን መራራ ተጋድሎ አህዱ ለማለት የጥምኖ ጊዜ መውሰድ እና በጥበብ ቀጣዩን ምዕራፍ መጀመር ነው።
መደናገጥ አያስፈልግም። የሰው ልጅ ደህና ከሆነ ፈቃደ እግዚአብሄር በራሱ ጊዜ የሚሠራው ታምር ይኖራል። ይህም ለበጎ ሊሆን ይችላል ብሎ ማሰብ ይገባል።
ከዚህ ቀጥሎ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን በቁም እስር ላይ እንደነበር ይታወቃል። በቀጣይ ምን ሊያደርጉት እንደሚችሉ አይታወቅም። መራራው ጊዜ የገባቸው ጥቂት ስለነበሩ አሁንም አዲስ የመማሪያ ሌሰን ለተኙ ሁሉ ተሸልሟል። ጃዋሪዝም ይህን ይመስላል። የፈለገውን የማስፈፀም ሙሉ አቅም አለው።
ኢትዮጵያዊው ሰው ቀፎውን ነው ያለው። ተቦርቡሮ፣ ተጎርጉሮ ደመ ነፍሱን ነው የሚንቀሳቀሰው። ነገስ? በእንቅልፋችን ልክ ይወሰናል?
አይዞን። ያ እንዳለፈው ሁሉ ይህም ያልፋል። ፅናት ብቻ ሳይሆን በአብይዝም እና በተደማሪ የወግ ገበታ እራስን አለመገበር ይጠይቃል።
የባልደራሱ ባለ አደራው ትውልዳዊ ድርሻውን በሚገባ ተወጥቷል። አደራውን በሚገባ አሳክቷል። ቀጣዩ ጉዳይ ህልውናውን የተነጠቀው ህዝብ የልዕልና ልቅና ምላሽ ነው የሚጠበቀው። ኢትዮጵያ አጥር ውስጥ ናት የምለውም ለዚህ ነው። የአዲስ አበባ ህዝብ ታግቷል።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ትዕግሥት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።