ክቡር ፈቃዱ ተክለማርያም።
![ምስል](https://blogger.googleusercontent.com/img/b/R29vZ2xl/AVvXsEiYNt6Et4zBqVzByFfzO2OT7lRqCBkO4VyjEudcHZN_XUnV7VeC6DxmXjk-7kp2iGGpMWYWerPZTGdomrUe9acIdoYYnPueS4Zoz5_Bi5hdR3XALHwk-tu0NdmbD7l36mrmdinsoBh_y4s/s400/fke.jpg)
!እባክህ አንጣህ? ከሥርጉተ ሥላሴ 15.03.2018 (ከጭምቷ - ሲዊዘርላንድ።) “ ብርቱ የሆነ እርሱ ታላቅ ሥራን በእኔ አድርጓልና፤ ሥሙም ቅዱስ ነው። ምሕረቱም ለሚፈሩት ከትውልድ ትውልድ ይኖራል። ስለዚህም ምክንያት ፍጥረት ሁሉ ያመሰግኑኛል ” ( ሉቃ . ምዕራፍ ፩፥ ከቁጥር ፵፱ ፶፩) !እባክህ አንጣህ? እምዬ ትጠጋህ ድንግል ትዳስስህ እሷ ትሁንልህ ምህረቷ ይዳብስህ። !እባክህ አንጣህ? ምልጃዋ ይሁንህ አለሁህ ትበልህ፤ አ ለ ችልህ ውስጥህ የዕምነት ደግነትህ። !እባክህ አንጣህ? ትኑር ል ን ነፍስህ ይኑርልን ጸጋህ ይሁንልን ግርማህ ማቱሳላ ዕንቁህ። !እባክህ አንጣህ? ፈቃዱ ይሁንህ ለእኛ ሲል ያኑርህ፤ ትጠብቅሃለች የተስፋ ሐገርህ የንጋት መንበርህ የምህረት አድባርህ፤ ድንግል አደራሽን እናቴ አደራሻን - እንዳታሳፍሪን፤ ቅዕባሽ ይሁነን - ስለእኛ ሁኝልን ቀድመሽ ተገኝልን፤ ቸሩነ ን አብስሪን። · ም ርኩዝ። http://yehaarts.com/interviews_next.php?rollId=Fekadu%20Teklemariam „ከፈቀዱ ተ/ መርያም ጋር እንጨዋወት።“ https://www.youtube.com/watch?v=Gy6tCsRrCqs „Ethiopia: በአርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም የህክምና ጉዳይ ላይ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ“ · ለዬኔዎቹ ቅኖቹ። ለ ጥበብ አባቱ፤ ለዘመን ዋርካው ለአርቲስት ፈቃዱ ተ/ ማርያም - ይሁንልኝ። ዝብርቅ ባለ በመረባበሽ ስሜት ነው የሠራሁት።