ልጥፎች

የአቦ ሌንጮ ለታ የፖለቲካ አቋም እና መጪው ተስፋው።

ምስል
           ?                                   ከሥርጉተ - ሥላሴ 15.05.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።)      „ከእንቅልፍ የምትነሱበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቧልና።                                                                                              (ወደ ሮሜ ምዕራፍ ፲፫ ቁጥር ፲፩)             ለሰሞናት ብቻ አይደለም ይህ የጥያቄ ምልክት ስለ ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር በህሊና ቦታ ሊሰጠው ይገባል የምለው ለቋሚነት ነው። ዝም ብል በወደድኩኝ ግን የምሳሳለትን የለማ አብይ ገድ „የኢትዮጵያዊነት ሱስ ነውን“ „የሚሊዮኖችን ድምጽ“ ከአደጋ ለመከላከል የሚሰማኝን ከመግለጽ መቆጠብ አይገባም ብዬ ስለማምን ነው። የማልደራደርበትም ቀን ከሌትም ዕንቅልፌን ትቼ አቅሜን ያፈሰስኩበት የዘመኔ የማግስት ጮራዊ ፈለጌ ነውና። ተፈጥሮዬም ይኸው ነው። በተያያዘም ለማከብራቸው ለጸሐፊ አቶ ግርማ ካሳ የምለው ይኖረኛል።             እንዴት ባጁ?      ጤና ይስጥልኝ የማከብረዎት አቶ ግርማ ካሳ እንዴት ሰነበቱ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። በወርሃ መጋቢትመጨረሻ       ይመስለኛል ግንቦት 7 ከኤርትራ ጋር ያለውን ግንኙት እንዲያቆርጥ በጻፉት ጉዳይ በሌሎች ጉዳዮች ላይ ጹሑፍ ስጽፍ በቀላል    የፖለቲካ ድርድር ሊሆን እንደማይችል ጽፌ ነበር። እርግጥ ነው ሥመዎትን አላነሳሁትም። ምክንያቱም በዛ ጹሑፍ ላይ ክብርት         ወ/ሮ አና ጉምዝን ጨምሮ በርከት ያሉ ወገኖቼን አንስቼ ስለነበር እንዳይበዛ በማሰብ ነበር። አሁን መቼም ክብርት ወ/ሮ አና ጉምዝ ቃ

ኦ!

ምስል
ኦ! – ከሥርጉተ ሥላሴ June 2, 2015 |  Filed under:  ነፃ አስተያየቶች  |  Posted by:  ዘ-ሐበሻ 307 SHARES Facebook Twitter 02.05.2015 /ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ/ ይድረስ ለፓን አፍሪካኒስቱ ወገኔ ለተከበሩ አቶ ቴወድሮስ ዳኜ – „እንዳላፍር ልቤ በሥርዓትህ የቀና ይሁን“ / መዝሙር ምዕ. 118 ቁ. 80 / „ እንዳያመም ጥራው እንዳይበላም ግፋው“ በቅድሚ እንዴት ሰነበቱ። ለአፍሪካውያን የስደትና የሰቆቃ መከራ የበኩለዎትን ድርሻ ለመወጣት በማድረግ ላይ ያሉትን ዬሰብዕዊነት  ጥረት አብዝቼ አከብራለሁ፤ ኢምንት ብሆንም አመሰግናለሁ። ከመልካም ነገር ፍቅርና ተስፋ መኖርና መሆን አሉና። እኔ ብዙን ጊዜ የኢትዮጵያ ሙሑራን በሰብዕዊ መብት እረገጣ፤ በዘበጠ አስተዳደር ጉዳይ ላይ ያላቸው ተስትፎ አናሳ ነው፤ የበቃም አይደለም በማለት ወቀሳን ከወገኖቼ ሳዳምጥ የአያያዝ አቅም ከሙሁራዊ ሥነምግባር ውስጠት ጋር የማጣጣም ብቃት አንሶን ሊሆን ይችላል የሚል ዕድምታ ስለነበረኝ ምንም ብዬ አላውቅም። ዛሬ ግን ተናጠሉን ሙሁርነት ብቻ ሳይሆን እንደ ቀደምቶቹ ኢትዮ – አፍሪካውያን ዕንቁዎች መስመሩን ለመከተል መቁረጥ ብቻ ሳይሆን ተግባር ላይ በተገኙት ወንድሜ ላይ ቅሬታዬን ከዕንባዬ ጋር ልልክለው እንሆ ወደድኩኝ። ሃዘኔ የምር ልቅሶዬም ከቁስለት – የተቀዳ ነው። ውድና የተከበሩ ኢትዮ አፍሪካዊው አቶ ቴወድርስ ዳኜ – ጎሰኝነት ወይንም መንደርተኝነት ያልተመጣጠነ የአስተሳሰብ እድገት ወይንም የአስተሳሰብ ድህነት ጽንስ ነው። እድገቱም ከቤተሰብ ቀጥሎ ያለ ስለሆነ ሁለመናው በእንጭጭ ዕጭ ተፈጥሮው ላይ ስለሚወሰን አህጉራዊ ኃላፊነትን በተቆርቋሪነት ላበሰለ ወገን፤ በወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ