ልጥፎች

እኔን።

ምስል
    እኔን። እባካችሁ ግፍን ፍሩ። እባካችሁን በቀል ይብቃችሁ። ስንት ዘመን ልትኖሩ ይሆን ? ይህ ግፍ ኢትዮጵያን ስንት እርግማን ያመጣባት ይሆን ??   " ፃድቅን መቅጣት፤ ጨዋ ሰውንም በፃድቅነቱ መምታት፦ መልካም አይደለም። "   ጠቅላይ ሚር አብይ ፓስተር ናቸው ይባላል። ወሮ ዝናሽ ታያቸው ቀዳማዊ እመቤቷም ዘማሪ ናቸው። በዚህ ግፍ ውስጥ ዘማሪነትስ ሆነ ፓስተርነት በፈጣሪ ዘንድ አገልግሎቱ ተቀባይነት ይኖረው ይሆን ? ሁልጊዜ በተቋማት ግንባታ በትቤት የሚተጉት ቀዳማዊት እመቤት ይህን ግፍ እና ግፍ ህሊናቸው ችሎ ያራምዳቸው ይሆን ? ከቤተሰብስ በዚህ ዕድሜ ያለ አጎት አይኖር ይሆን ? አዛውንቷ ኢትዮጵያስ እንደምን ይከፋት ? ዛሬ ነገ ስንብታችን አናውቀውም። ለፀፀት ይቅርታ ለመጠዬቅ ቀጠሮ አያስፈልገውም። ዛሬውኑ ባለ ዕድል እኒህ አዛውንት አባት ከእስር ተፈተው በክብር ተከብረው እንዲኖሩ ያለስጋት ሊደረግ ይገባል። ውቦች እንዴት አደራችሁልኝ። ደህና ናችሁን ? ኑሩልኝ። ሥርጉትሻ 2024/05/20 ጊዜ ራዲዮ ነው።  

ምዕራብውያን ሆነ አውሮፓውያን በኢትዮጵያ #ተስፋ ላይ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል ባይ ነኝ። ከተደጋገመ ግድፈትም ቢቆጠቡ ስል በትህትና ዕይታዬን አጋራለሁኝ።

ምስል
  ም   ም ዕራብ ውያን ሆነ አውሮፓውያን በኢትዮጵያ # ተስፋ ላይ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል ባይ ነኝ። ከተደጋገመ ግድፈትም ቢቆጠቡ ስል በትህትና ዕይታዬን አጋራለሁኝ። " አቤቱ በቁጣህ አትቅሰፈኝ፦ በማዕትህም አትገስፀኝ። " ( መዳ ምዕራፍ ፴፯ ቁ ፩ ) በማያቸው ሰሞንኛ ጉዳዮች ኢትዮጵያን ዳግም # ጨቀጨቅ ውስጥ ሊዘፍቅ የሚችሉ ውሳኔወች እንዳይኖሩ እሰጋለሁኝ። ኢትዮጵያ በማህበረ - ኦነግ መሪወች ልክንም መመዘን የተገባ አይመስለኝም። እንደ ሦስት ዓመት ህፃን ልብሱን አስተካክሎ መልበስ የማይችል። ቢሮውን በሥርዓት አደራጅቶ ለመምራት እንኳን አቅም የለሽ ሰብዕና የምስራቅ አፍሪካን፤ የአፍሪካ ቀንድን፤ የኢትዮጵያም ተስፋ ይሆናል ብሎ የምክር አገልግሎት መጠዬቅ፤ ለቀጣዩ የኢትዮጵያ ተስፋም እጩ ማድረግ # በፍፁም # ሁኔታ # ስህተት ነው። የ 32 ዓመታቱ የኢትዮጵያ መከራ እንዲያበቃ ከተፈለገ በሰው ልጅ ሰቆቃን ግድ የማይለው ሰብዕና፦ አጽናንቶ፤ አይዟችሁ ብሎ የማያውቅ ተፈጥሮ የመፍትሄ አካል አድርጎ መራመድ በብዙኃኑ ህልውና # የጭካኔ ውሳኔ ነው። ኢትዮጵያ አጽናኝ መንፈስ፤ አጽናኝ ቲም ያስፈልጋታል። ምዕራባውያን ሆኑ አውሮፓውያን ሰውን ማዕከሉ ያረገ ተፈጥሯዊ ሥርዓት ለኢትዮጵያ ያስፈልጋታል የሚል ግልጽ አቋምና ውሳኔ ላይ ሊደርሱ ይገባል። በኢትዮጵያ ፖለቲካ ኢትዮጵውያን እንደ ጥንቸል የዶክተሪን መሞከሪያ ጣቢያ መሆኗ ዲታ አገሮች ሊያማቸው ይገባል። ርህርህና፤ ደግነት፤ አጽናኝነት ትምህርት ቤት የላቸ