ልጥፎች

የዘመኑን የፖለቲካ ባህሬ መረዳት ይታደጋል? እንዴት? ስለምንስ?

ምስል
  የ ዘመኑን የፖለቲካ ባህሬ መረዳት ይታደጋል ? እንዴት ? ስለምንስ ?   «እኔስ ወደ ማንከስ ቀርቤያለሁ እና ቁስሌም ሁልጊዜም በፊቴ ነውና።» ( መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፴፮ ቁጥር ፲፯ )   ገ ና በጥዋቱ ነበር እኔ ዘመኑ የገዳን ሥርዓት በኢትዮጵያ ማስፈን ነው በማለት ሙግት የጀመርኩት። በሌላ በኩሉ የዘመኑን የፖለቲካ ባህሪም ገዳን ይመስላል ብዬ ሞግቻለሁኝ። ከገዳ የሚጠቅም ነገር ከኖረ ልምዱን መውሰዱ ባይከፋም ኢትዮጵያ በገዳ ልክ ትሠራ ግን ግራጫማ ዕሳቤ ነው። ጨለማ ያልልኩት ገዳ ኢትዮጵያዊ መልክም ስላለው ነው። ገዳን የሚቀበሉ፤ በገዳ ሥርዓተ ህግ የሚተዳደሩ የኛው ወገኖች ስላሉ አጨልሜ አልመለከተውም።   ·                  ቁ ምነገር።   በ ቁምነገር ገዳ የኢትዮጵያ የተበጀችበትም የተሠራችበትም ሥርዓት አይደለም። ኢትዮጵያ ከገዳ የቀደመ የመፈጠር ጥበብ ስላላት። ኢትዮጵያ በገዳ አምሳል ብትፈጠር ኢትዮጵያ የ 80 እና ከዛም የሚበልጥ ብሄረሰብ አንባ ባልኖሆነች። የማህበረሰቦችም ቋንቋና ባህልም ይዋጥ ነበር። በሃይማኖት ዘርፍ ኢትዮጵያ መ ልኳ፦ በባህል ሁነትም ኢትዮጵያ ቀለሟ ሌላ ይሆን ነበር። ገዳ በታሪኩ ታሪክ አዋቂወች እንደሚሉት ወረራ፤፦መሥፋፋት፤ አስምሌሽን እና ዲስክርምኔሽን በመሆኑ ልሙጥ ትሆን ነበር ኢትዮጵያ።   ገ ዳ ፊደል የለውም። ስለዚህ በዕውቀት ዘርፍም ይኖር የነበረው መከራ የገዘፈ በሆነ ነበር። ገዳ የኢትዮጵያ በ 16 ኛው መቶ ክዘመን ከ 20 በላይ ማህበረሰቦችን ው