ልጥፎች

ክፉት ውበትም ጌጥም አይደለም። ሥርጉትሻ

ምስል
  ክፉት ውበትም ጌጥም አይደለም። ሥርጉትሻ 2024.05.18   ውቦቼ ውብ ሰንበት። አሜን።

የኢትዮጵያ ፖለቲካ የባህሪ መለያ ከህግ በላይነቱ ብቻ ሳይሆን በህግ አፈፃፀም ተጠያቂነትም ላይ በቀለኛ፣ ቂመኛ እና #ዱለኛ መሆኑ ነው።

ምስል
                 የ ኢትዮጵያ ፖለቲካ የባህሪ መለያ ከህግ በላይነቱ ብቻ ሳይሆን በህግ አፈፃፀም ተጠያቂነትም ላይ በቀለኛ፣ ቂመኛ እና # ዱለኛ መሆኑ ነው። ረጅም እርዕስ ነው። ዕርዕሶቼ አጫጭር ናቸው። አንዳንድ ጊዜ በ 4 ዕርስ አንድ ወጥ ጹሁፍም እጽፋለሁ። በቅድሚያ እንዴት አደርን ማህበረ ቅንነት ? ምዕራፍ 13 ቀጥሏል ውስጥን በመመርመር ላይ። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሃኪም የለሽ ነውና። እኔ ሃኪሙ ነኝ እያልኩ አይደለም። ኧረ ምን በወጣኝ ???   " አቤቱ ታድነኝ ዘንድ ፍቀድ፥ አቤቱ፦ እኔን ለመርዳት ፍጠን። " አሜን ይደረግልን። ይሁንልንም።" አሜን። ( መዳ ምዕራፍ ፴፱ ቁ ፱፫ ) # ጥቂት ። በወንጌል መጀመሬ የሚከፋቸው ታዳሚወች ገጥመውኛል። እኔ እኮ የፖለቲካ ድርጅት መሪ አይደለሁም። ብሆን አላደርገውም። በሌላ በኩል ወንጌል አቅም አለው ህሊናችን የመግራት። በተጨማሪም ፀላዬ ሰናያዊ እሾሆችንም ያባርራል። ከዚህ ሌላ እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ወይንም ሰብለ ህይወት እራሴን ተውሼው ወይንም ተወርጄው አላውቅም። በራሴ ርዕይ እና ጎዳና ቀጥ ያለ አቋም ያለኝ ነኝ። በልጅነቴ የሚያውቀኝ ሰው ዛሬም ቢገኜኝ ብትጠይቁትም እሷ ስትፈጠር እንዲህ ናት ይላችኋል። ወጣገባ ሰብዕና የለኝምና። ሞቅ ቀዝቀዝ ዳመን ፍክትም የለም። በማናቸውም እኔን በሚሻ ቦታ የራሴም የጠና ቀለም እና አርት ያለኝ ሰው ነኝ። ስለዚህ ጎርፍ ለሚያመጣቸው ዕይታወች ባርባር የሚለኝ አይደለሁም። ያማ ቢሆን