ልጥፎች

#ድርድር እና የሰው ልጅ። ሕይወት #አናጋሪም #ተናጋሪም፤ #አናባቢ #ተነባቢም ና

ምስል
  #ድርድር እና የሰው ልጅ። ሕይወት #አናጋሪም #ተናጋሪም ፤ #አናባቢ #ተነባቢም ና ት።   (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱) "የሰው ልጅ መንገድ ያዘጋጃል እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያዘጋጃል።" እጽዋት ቅኖች ናቸው። ቅን ባይሆኑ ፍሬ ሳይሆን ትል ያፈሩ ነበር። እኛስ???? ድርድር የፈጣሪ ሥጦታ ነው። ፈጣሪ ሠራሽም ነው ለእኔ። የመኖር ጥበብ ነው። ከቀስት እንድን ዘንድ የመዳንም ምልክት ነው ለእኔ።። ህይወት ድርድር ናት። የድርድርም ውጤት ናት። የሰው ልጅ እና ድርድር አብረው የተፈጠሩ ናቸው። ድርድሩን ስታፈርሰው ቅጣት ይኖራል። አዳም ከፈጣሪ አምላክ ጋር የነበረውን ድርድር አፍርሶ ነው የሃጢያት መርገም የወረደው። አባ አባት ነውና በፍጥሮቹ ስቃይ ደስተኛ አልነበረምና ስቃዩን እንደ ሰው ሆኖ አይቶ ስቅለትን መረጠ። ስቅለቱ የኃጢያትን ግድግዳ ሰብሮ የእርቅ ድልድዩን ትንሳኤን ሰጠን። የዚህ ትርጉም ማመሳጠር የኔ ፀጋ አይደለም። በቁሙ ንባቡ የሰማያዊ ግርማ ሞገስ ድርድር ሂደቱ ከተሰጠን ስጦታወች የመኖር ጥበብ ውስጥ አንዱ ነው። ለድርድር ልኩ ማስተዋል፤ ጥሞና፤ ፀሎት እና ፈቃደኝነት ነው። ሦስተኛው የግጥም መዐሐፌ "ውል" ነው እርዕሱ። #ውል ። የድርድር አስኳል ነው። ውል ላልቶ ሲነበብ ትዝታ፦ ሽውታ ይሆናል። ሽውታም በራሱ ጠብቆ እና ላልቶ ሲነበብ የራሱ ትርጉም አለው። ሽውታ ቅፅበታዊነትንም ያመለክታል እንደማለት። ውል ዘመኑ በትርፍ ስሌት የተመሰጠረ ነው። ወይንም ሰጥቶ በቀበል የእኩልዮሽ መርህ። እናት እና ልጅ ውል አላቸው። እንቁላሉ ሰው ለመን ጽንሱ ሀሌት ካለበት ጀምሮ። በመኖር ውስጥ ውል - ድርድር - ስምምነት የሌለበት፤ ክርክር - ሙግት የሌለበት የመኖር ዘይቤ አይገኝም። ዕብን የሚባሉት እንሰሳት ውሻ፤ ደሮ፤ ፈረስ

#ጤና

ምስል
  #ጤና እባካችሁ ብዙ በኩላሊት ጠጠር የሚሰቃይ ሰዎች አለ--- #ሼር_ያድርጉት የኩላሊት ጠጠርን በ10 ቀናት ውስጥ ለማስወገድ ------------------------------------- በአሁኑ ሰዓት የኩላሊት ጠጠር በጣም በብዙዎች ዘንድ የሚከሰት ችግር ሆኗል፡፡ ጠጠሩ የሚፈጠረው በሚኒራሎች እና በአሲዳማ ጨው በኩላሊት ውስጥ ሲሆን የሚከማቸው በኩላሊት ውስጥ ወይም በላይኛው የሺንት ቧንቧ አልያም በሽንት ፊኛ ውስጥ ሊሆን ይችላል፡፡ የሚፈጠሩት ጠጠሮች በሽንት ቧንቧ አማካኝነት ሊወገዱ ይችላሉ፡፡ የተወሰኑት ግን እዚያው ሊቆዩ ይችላሉ፡፡ እዚያው የሚቆዩ ጠጠሮች ካልተወገዱ፣ አንድ ላይ ትልቅ ጠጠር መፍጠራቸው አይቀርም፡፡ ምናልባት የጎልፍ ኳስ ያክል መጠን ሊደርስም ይችላል፡፡ ይህም የሽንት ቧንቧን ሊዘጋ፣ በምንሸናበት ሰዓት ከፍተኛ ህመም ሊያስከትል፣ ማቅለሽለሽ፣ እንዲሁም ማስታዎክ ያስከትላል፡፡ እነዚህ ችግሮች ጠጠሩ አስካልተወገደ ድረስ ቀጣይነት ይኖራቸዋል እንጂ አይተውንም፡፡ የኩላሊት ጠጠርን ለማስወገድ የሚሆኑ ዘዴዎች የኩላሊት ጠጠር ከሰውነታችን በተለያዩ መንገዶች ሊወገድ ይችላል፡፡ ይህም በጠጠሩ መጠን እና አይነት ይወሰናል፡፡ የኩላሊት ጠጠር በውስጣችን እንዳለ ካወቅን ስለሁኔታው የጤና ባለሙያ ማማከር የመጀመርያ ስራችን መሆን አለበት!!! ዋናው ነገር ግን አስቀድሞ መከላከል ነው፡፡ ይሄም በቀላሉ ከቤት በምናዘጋጃቸው ነገሮች (home remedies) የኩላሊት ጠጠርን መጠን መቀነስ እና በሽንት አማካኝነት እንዲወገዱ ማድረግ ይቻላል፡፡ ከነዚህ home remedies መካከል በጣም የምታዎቀው የሚከተሉትን ነገሮች በመቀላቀል የሚገኝ ነው። እነርሱም፦ • 1 ብርጭቆ ንጽህ ሙቅ “ውሃ” • 2 የሾርባ ማንኪያ “የአፕል ጭማቂ” • 1 ወይም 2 የሾርባ ማንኪያ “ማር”

ቁሞ ሲሄድ

 ዕውነት ቁሞ ሲሄድ ተስፋ ይቃረባል። ዕውነት ጓዳ አደር ሲሆን አቅም ይሸሻል። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 01/06/2021

አሳቻው ጠቅላይ ሚኒስተር 01.06.2021

  #አሳቻው ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ፣ ፆታ፣ ዕምነት፣ አቋም፣ ሰዋዊ ኖርምስ፣ ኃይማኖት፣ ዕውቀት አለኝ የሚሉት፣ ነኝ የሚሉት አሳቻ ነው። ይህን በድምፅም በፁሑፍም ሠርቸዋለሁ። ሥርጉተ©ሥላሴ

#ልጆቻችን ወደ ሞት መላክ ይታሰብበት።

ምስል
    · #ልጆቻችን ወደ ሞት መላክ ይታሰብበት።   ዕለተ ሰንበት ማዕዶተ ርትህወሰባዕዊነት በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። "ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።" (ትንቢተ - ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯) #ማዕዶተ ርትህወሰባዕዊነት ሰው መሆን መቻል አምጦ መውለድ ካልተቻለ የኢትዮጵያም፣ የልጆቿም መከራ ይቀጥላል። ዛሬም ከዛ የክፋ አዬር ጭካኔ ካልወጣው ቀዬ ወደ ደንቢደሎ ዩንቨርስቲ የሚመደቡ ተማሪወች እንዳሉ እዬተደመጠ ነው። በዚህ ቋያ ወቅት ወደ ኦሮምያ ቀንበጥ እና ሸበላን መላክ ሥም የለሽ ግማድ ነው። ይታሰብበት። ለጭካኔ ስንቅ ማቀበል ኃጢያት ይመስለኛል። ወላጆች ቢያስቡበት መልካም ነው። እግዚአብሔር ይስጥልኝ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 22/05/2021 ፈጣሪ ሆይ! ኢትዮጵያን እባክህ ቅረባት? እባክህን?

ቀን ሲሰጠው

  ዕውነት ሸሸውም፣ ቅበረውም፣ ተሸሸገውም፣ ሸውደውም ያው እሱነቱን ለብጦት፣ በአርቲፊሻል ቀሽሮት አያውቅም ቀን ሲሰጠው ይበራል፣ ያበራል። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 01/06/2021

ዕውነት ቋንቋ አለው። ዕውነት ግሥ አለው ይገስሳል፣

 ዕውነት ቋንቋ አለው። ዕውነት ግሥ አለው ይገስሳል፣ ዕውነት ስዋሰው አለው ድንጋጌ ችሎትም። ስትስተው የአደባባይ ቄጤማ ያደርግኃል። ያራግፍኃል። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 01/06/2021

#ሦስቱ ሰኔወች #ሦስቱ ጥቅምቶች የአዋሳው 11/11 የምርጫ ሸፍጥ ምህንድስና ነው።

ምስል
  #ሦስቱ ሰኔወች #ሦስቱ ጥቅምቶች የአዋሳው 11/11 የምርጫ ሸፍጥ ምህንድስና ነው።    ዕለተ ማክሰኞ ማዕዶተ ይግቡ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። "ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።" (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯) #ዕፍታ ለትውስታ። #ሦስት ሰኔወች፣ #ሦስት ጥቅምቶች፣ 11/11 ነገረ አዋሳ ለምርጫ ምህንድስና የተሰሩ የሞገድ መጽሐፍ፣ እና የ90 ደቂቃ በኢንተቤ ትወና የተከወነባቸው የገዳ ምርጫ ቦርድን ህጋዊ ዕውቅና ለማሰጠት የተሰናዱ ኦፕሬሽን ናቸው ብዬ በድምፅም በፁሑፍም በተደጋጋሚ ሠርቻለሁኝ። ይህን ሊቀ ትጉኃን አቶ ሰለሞን ኃይሌ የማይወዛወዙ ዶፋን ችለው ከእኔ ብራና ጋር የዘለቁት ቅኑ የብራናዬ ታዳሚዬ ያውቁታል። ግን ሰሚ አልነበረም። እስከዚህ ድረስ በጥልቀት ሄዶ የምርጫ መሰናዶ ስለመደረጉ የተነተነ ተንታኝ አላውቅም። #ሙሉ መሰናዶ እና ሂደቱ። ምርጫን አስበው በሱማሌ ማፈናቀል የሠሩትም ለዴሞግራፊው ስኬት ስለምርጫው ስለመሆኑ ኦህዴድ ስልጣን ከመያዙ በፊት ስለመሆኑም በአፅህኖት ፅፌያለሁ። ከዛም በኋላ "እንሞታታለን እንጂ ቤተ - መንግሥት አንለቅም" የጠቅላይ ሚር አብይ አልነበረም። በጨፌ ስብሰባ ለተነሳው ጥያቄ ዶር ለማ መገርሳ ሲመልሱ ቃሉን ተጠቅመውበታል። የቁም ሰማዕቱ ዶር አብርኃም ዓለሙ ተርጉመውት በርዮት ሚዲያም፣ ዘሃበሻ ላይም ለህትምት በቅቶ ስላነበቤኩ ያም ለምርጫ መሰናዶው ጥጉ እስከምን እንደሆነ ፅፌበታለሁ፣ በድምፅም ሠርቸበታለሁ። ግን አልተስተዋለም። ይህም ብቻ አይደለም እሳት ለብሰው ነፍሳቸውን ስተው እንደ አንድ ወጠጤ ጎረምሳ ጅማታቸው ተገታትሮ እሳት ጎርሰው እሳት ለብሰው ዶር አብይ አህመድ "ጦርነት ውስጥ