ልጥፎች

Navigation. Über der Schimmel Führer. Dr. Kereis (PM Abiy Ahmed Ali)

ምስል
  Navigation. Über der Schimmel Führer. • Dr. Kereis (PM Abiy Ahmed Ali) • Thema Notfall News Maker.   Ihre Persönlichkeit ist wie ein Gel. Die Eilmeldungen Schöpfer sind Premierminister Abiy Ahmed. Es ist Ihr Brand. Ihre Leitung ist Schimmel. Lassen Sie mich Ihnen etwas sagen, was Sie nicht wissen. Während der vierjährigen Amtszeit von Premierminister Abiy Ahmed gab es keine offiziellen Neuigkeiten Nachrichten. Es sind vier Jahre voller Eilmeldungen. Eilmeldung: Bis zu fünf pro Tag. Dr. Krise oder Connell Krise Abiy Ahmed haben eine Haushaltskrise. Sie organisieren Krisen; Sie führen eine Krise an und sie machen die Eilmeldungen. Vier Jahren, es gibt keine offiziellen Nachrichten in Äthiopien. Tut weh. Sie sind die Natur der Presse getötet. Sie haben den Mediennatur in Eis verwandelt. Die Nachricht ist nur Tod und Trauer oder Brände oder die Zerstörung von Städten oder Kriege. Der Kapitän ist der Premierminister. Sie führen Äthiopien auf unbekannte Weise. Das äthiopische Volk leidet u

ሰማዕቱ ደብረ ኤልያስ። ግፍ የተፈፀመበት ፃድቁ እና ሐዋርያው ቅዱስ ባዕት።

ምስል
  ሰማዕቱ ደብረ ኤልያስ። ግፍ የተፈፀመበት ፃድቁ እና ሐዋርያው ቅዱስ ባዕት።   "ዬቤትህቅናት በላኝ።" እንዴት ነን? አይዞን። ይህ ክፋ ዘመን ያልፋል። ከሊቀ ትጉኃን ከአቶ ኪሩቤል ዘላዓለም ዬተገኜ ነው። "ደብረ ኤልያስ" "የሐዲስ ዓለማየሁ ፣የዮፍታሔ ንጉሤ፣የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ሃገርየነመልካሙ በጎሰው፣የነዶ/ር ኢሳይያስ የትውልድ ከተማ። ዛሬ በቅዱስ ኤልያስ በዓል ዋዜማ ላይ በሥፍራው ተገኘሁ። አካሄዴ በደብረ ኤልያስ የተሠራውን ሆስፒታል ለደገፉ ምስጋና ለማቅረብ በተደረገው ፕሮግራም ለመሳተፍ ነበር። ይህንን በቀጣይ እመለስበታለሁ። ነገ ታሕሳስ 1 ቀን 2015 የሚከበረውን የቅዱስ ኤልያስን በዓለ ልደት ዋዜማ ለማየት ከታደሉት አንዷ በመሆኔ ከሥራ ባልደረቦቼ ጋር ሆነን ወደ ገዳሙ ተጓዝን። ከየገጠሩ መንደሮች ከሩቅም ከቅርብም ለጠበል ጣዲቅ የሚሆን ምግብ የተያዘበት መሶብና ገምቦ እየያዙ ወደ ቤተክርስቲያን የሚጓዙትን እያየን በአቧራማው መንገድ ወደዚያው አቀናን። እነሆ ታላቁ ገዳም ከነሙሉ ግርማው በኢትዮጵያ ባንዲራ አሸብርቆ በምእመናኑ ደምቆ ጉብ ብሏል። ቅዱስ ኤልያስ በእሳት ሠረገላ በእሳት ፈረሶች ተነጥቆ ወደ ሰማየሰማያት ሲወሰድ የሚያሳየው ውብ ሥዕል በአፀደ ቤተክርስቲያኑ መሐል ጉልህ ሥፍራ ይዟል። " "በመጽሐፍ ቅዱስ የተፃፈው ገድሉ እንደሚያስረዳው "ከደቀ መዝሙሩ ከኤልሳዕ ጋር እየተነጋገሩ ሲሔዱ የእሳት ሠረገላ፣ የእሳት ፈረሶች በመካከላቸው ገቡና ለያዩዋቸው፡፡ ኤልያስም በእሳት ሠረገላ ዐረገ፡፡ ኤልሳዕም የኤልያስን ወደ ሰማይ መወሰድ አይቶ ጮኸ፤ ኤልያስም ልብሱን ከሁለት ከፈለው፡፡ መጠምጠሚያውንም ለኤልሳዕ ጣለለት፡፡ የኤልያስ ጸጋና በረከትም በኤልሳዕ ላይ አደረ" ይላል።

1% በኢትዮጵያ የፖለቲካ ውክልና የሌለው የገበሬው ምጣት ዘመን 32 ዓመት አስቆጠረ

ምስል
  1% በኢትዮጵያ የፖለቲካ ውክልና የሌለው የገበሬው ምጣት ዘመን 32 ዓመት አስቆጠረ ።    ብዙ በጣም ብዙ ጊዜ ጽፌበታለሁ። ለጠቅላይ ሚር አብይ አህመድም እንደ ሰው ቁጠሩኝ ባሉበት ዘመን ግንቦት 5/2010 መቶ ቀናታቸውን ሳያጠናቅቁ ነበር ወሳኝ ብሄራዊ ጉዳዮችን ነጥብ በነጥብ ዘግቤ ያሳሰብኳቸው። ካሳሰብኳቸው በኽረ ጉዳዮች አንደኛው የገበሬው ጉዳይ ሲሆን ሁለተኛው ደቡብ ሱዳንእና ጋንቤላም ነበሩበት። በጣም በስፋት ነበር የፃፍኩት። የቁቤ ትውል መልሶ በብሄራዊ ስሜት ማነጽም ይገኝበት ነበር። ኢትዮጵያ ዬገበሬወች አገር ሆና ግን ዬኢትዮጵያ ገበሬ የፖለቲካ ውክልና የለውም ሰፊው ማህበረሰብ። ሁለገብ በሆነው የኦነግ ጆኖሳይድ ተጠቂ ከሆነው የአማራ ማህበረሰብም ገበሬው ግንባር ቀደም ነው። ልጆቹን በማገት፤ በጅምላ በመጨፍጨፍ፤ የቤት እንሰሳቱ ላይ ጆኖሳይድ በመፈጸም ሰፊ የሆነ ፀረ መኖር ዘመቻ ሲካሄድ እንሆ 50 ተቆጥሯል። አገር ተደፈረች፤ ሉዓላዊነት ተነካ ሲባልም በገፍ የሚያልቀው የአማራ ገበሬ ነው። ያኮረፈ ሁሉ የሚተመው ምሽግ የሚያደርገውም አማራ ገበሬን ነው። የኢሊባቡር፤ የጋሞ፤ የባሌ፤ የጅማ፤ የአርባምንጭ፤ የአሰላ ወዘተ ጫካወች በሰላም ውለው ሲያድሩ የአማራ ቀዬ ግን ዕድሜ ልክ ስቃይ ብቻ። በዚህ በአምስት አመቱ የሌኮ አብይ አህመድ የቤርሙዳ ትርያንግል ዘመን ጭካኔን፤ አረማዊነትን፤ በዓይነት አይተናል። ዬአማራ ገበሬ ልጆቹን ወደ ትምህርት ቤት እንዳይሄዱ፤ ከቀደመው ከዘመነ ህወሃት እንዳይወልዱ እንዳይከብዱ የማምከን ተግባር ተፈጽሞበታል። በዚህ መከራ ውስጥ ያለፈው ትውልድ ነው አሁን ለንብርብር መከራ እዬተዳረገ ዬሚገኜው። ዬአማራ ገበሬ ምርቱን ተዘዋውሮ እንዳይሸጥ ማዕቀብ ተጥሎበታል። ይህን ሁሉ የቻለ የአማራ ገበሬ አሁን ደግሞ #ማዳበሪያ ታግዷል። ዬእ

በጎርፍ ውኃ ጠጅ አይጣልም።

ምስል
  " ስምምነትን መቃወም ፍትኃዊ አይደለም።" በትውስት አቅም መፍትሄ አይገኝም። በጎርፍ ውኃ ጠጅ አይጣልም።    አዲስ ዋልታ ሊቃናቱን ያወያዬበት ርዕሰ ጉዳይ ነው። ግን ፍትህ ለዶር አብይ መንግሥት ምንድን ነው? ህግ አውጥቶ ከንቲባ መሾም? ወይንስ በህዝብ የተመረጡ የፓርላማ፤ የምክር ቤት አባላትን ተዳፍሮ ከምክር ቤቱ፤ ከፓርላማው ፈቃድ ውጪ ማሰር እና በበቀል መበቀል ነው? ይህ ይሆን ፍትኃዊነት? እሳቸውን ለስልጣን ያበቃውን የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ መልስ ሳይሰጥ በጭነት 3 አዳዲስ ክልሎችን ፈጥሮ በባጀት እጥረት እያገላበጡ ማሸት? ወይስ ከፋኝ ያለን ማህበረሰብ በማሽን መፍጀት ማሸማቀቅ? ወይንስ አማራ የተባለን ህዝብ አልይህ ብሎ ለብቻው ከልሎ በህግ አውጣ ቀንዳም የበቀል ሾተላይ ሙሉ ዘጠኝ ወር የበቀል ግጥግጠኛ መሆን??? የአማራ እናት እትብትን እና ማህፀንን በጭካኔ መጨፍጨፍ፤ ማሰር ማንገላታት? መቼ ነው የምክክር ኮሚሽኑን እዬነጣጠሉ ጥቃት የሚፈፅሙበት። የሳቸው የጠቅላይ ሚሩ ማለቴ ነው #አስፈንጥሮ መፈጥፈጥ ልማዳቸው ነውና። ከሄሮ ወደ ዜሮ። ግን አዲስ ዋልታ የት ላይ ይሆን ቢሮው??? ጁቢተር ወይንስ ኡራኖስ? አገራዊ ምክክሩ ምን አስቀረ? እሱ እያለ እኮ ነው ደብረ ኤልያስ፤ መራዌ መአት የሚዘንበው? አቅም አልባ አቅም ነን ፋንታዚ ይመስለኛል። በጎርፍ ውኃ ጠጅ አይጣልም። የገረመኝ የደህንነት ዋስትና እንሰጣችኋለን መባሉ ነው። የእናንተ ደህንነት ዋስትና ካገኜ በቂ ነው። መንግሥታዊው ሥውር አካል ዕውቅና ተሰጥቶት በጠራራ ፀሐይ ያሻውን በሚያደርግባት ኢትዮጵያ? "እኛ ዋስትና እንሰጣለን"??? የቅንጡ ጥያቄ ነው በሞት በዓት ኢትዮጵያ። ለመሆኑ ሚዛን ካለ መቼ ነው ፋኖ ኦፊሻል ጥያቄ የቀረበለት። "ተራ

#ድርድር እና የሰው ልጅ። ሕይወት #አናጋሪም #ተናጋሪም፤ #አናባቢ #ተነባቢም ናት።

ምስል
  #ድርድር እና የሰው ልጅ። ሕይወት #አናጋሪም #ተናጋሪም ፤ #አናባቢ #ተነባቢም ናት።    (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱) "የሰው ልጅ መንገድ ያዘጋጃል እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያዘጋጃል።" እጽዋት ቅኖች ናቸው። ቅን ባይሆኑ ፍሬ ሳይሆን ትል ያፈሩ ነበር። እኛስ???? ድርድር የፈጣሪ ሥጦታ ነው። ፈጣሪ ሠራሽም ነው ለእኔ። የመኖር ጥበብ ነው። ከቀስት እንድን ዘንድ የመዳንም ምልክት ነው ለእኔ።። ህይወት ድርድር ናት። የድርድርም ውጤት ናት። የሰው ልጅ እና ድርድር አብረው የተፈጠሩ ናቸው። ድርድሩን ስታፈርሰው ቅጣት ይኖራል። አዳም ከፈጣሪ አምላክ ጋር የነበረውን ድርድር አፍርሶ ነው የሃጢያት መርገም የወረደው። አባ አባት ነውና በፍጥሮቹ ስቃይ ደስተኛ አልነበረምና ስቃዩን እንደ ሰው ሆኖ አይቶ ስቅለትን መረጠ። ስቅለቱ የኃጢያትን ግድግዳ ሰብሮ የእርቅ ድልድዩን ትንሳኤን ሰጠን። የዚህ ትርጉም ማመሳጠር የኔ ፀጋ አይደለም። በቁሙ ንባቡ የሰማያዊ ግርማ ሞገስ ድርድር ሂደቱ ከተሰጠን ስጦታወች የመኖር ጥበብ ውስጥ አንዱ ነው። ለድርድር ልኩ ማስተዋል፤ ጥሞና፤ ፀሎት እና ፈቃደኝነት ነው። ሦስተኛው የግጥም መዐሐፌ "ውል" ነው እርዕሱ። #ውል ። የድርድር አስኳል ነው። ውል ላልቶ ሲነበብ ትዝታ፦ ሽውታ ይሆናል። ሽውታም በራሱ ጠብቆ እና ላልቶ ሲነበብ የራሱ ትርጉም አለው። ሽውታ ቅፅበታዊነትንም ያመለክታል እንደማለት። ውል ዘመኑ በትርፍ ስሌት የተመሰጠረ ነው። ወይንም ሰጥቶ በቀበል የእኩልዮሽ መርህ። እናት እና ልጅ ውል አላቸው። እንቁላሉ ሰው ለመን ጽንሱ ሀሌት ካለበት ጀምሮ። በመኖር ውስጥ ውል - ድርድር - ስምምነት የሌለበት፤ ክርክር - ሙግት የሌለበት የመኖር ዘይቤ አይገኝም። ዕብን የሚባሉት እንሰሳት ውሻ፤ ደሮ፤ ፈረስ

አማኑኤል አድርጎት ከሆነ እንኳን ደስ አለወት። #ይገባልም።

ምስል
      አማኑኤል አድርጎት ከሆነ እንኳን ደስ አለወት። #ይገባልም ። "የሰው ልብ መንገድ ያዘጋጃል እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።" (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱) የማከብረወት ዶር ዳንኤል በቀለ እንዴት ሰነበቱ? አንድ #እሸት የሆነ የዕውቅና ዜና ሰማሁኝ። ዕውን ከሆነ ይገባል። የአውሮፓ ህብረት ለክብርነተወ ሰጠ የተባለው ዕውቅና ሰብዓዊነት በኢትዮጵ ያለበትን ሁኔታም ዕውቅና የሚሰጥ ስለሆነ ዘርፈ ብዙ ጥቅም አለው ብዬ አምናለሁኝ። ከሁሉ በላይ በጽናት እርሰወን አምነን ሲከፋን እባከወት ይከታተሉት እያልን አቤት ለምንል ወገኖችም ከደስታ በላይ ሐሴት ነው ብዬ አምናለሁ። ደስታ ለምድራዊ ሲሆን ሐሤት ግን መንፈሳዊ ሁነትን ያካታል ብዬ አምናለሁ። የሆነ ሆኖ ኢትዮጵያ እራሷ ሰባዕዊ፤ ተፈጥሯዊ እና የሰባዕዊ መብትም ተሟጋች እንደሆነች አምናለሁ። ዝክረ ታሪኳ በጎ፤ አወንታዊ ቅናዊ ርህርህናዊ ተግባር የተፈፀመባት አገር ስለነበረች። እና እማማ እና ልጆቿ ፀጋችን ተላልፈን ምርቃታችን ስለተነሳ እንጂ #ኢትዮጵያኒዝም በራሱ ሊማሩት የሚገባ #አንከር ክስተት ነው ብዬ አምናለሁ። ኢትዮጵያ ላልከበደቻቸው ወገኖች በሚስጢሯ ልክ እስከሆኑ ድረስ እንዲህ ያለ ሞገስ፤ እንዲህ ያለ ማዕረግ እንዲህ ያለ ሽልማት ያስገኛል። ሆነም // አልሆነም #ሱናሜውን ታግሰው ከቲመወት ጋር በምታደርጉት ጥረት አለን የምንለው አኃቲ ተቋም መኖሩ በራሱ ልዩ በረከት ነው። የተቋማት ጥራት እና ቅልጥፍና ቢበራከት አያሌ ችግሮቻችን ይፈታሉ። ለትውልዱም ተስፋዊ ጉዞ ምቹ መደላድል ይገኛል። በግዙፋ የኢትዮጵያ አሳቻ የፖለቲካ ተፈጥሮ ውስጥ ሳይታክቱ፤ ወጀቡን ታግሶ መዝለቅ በራሱ ለኃላፊነት እና ተጠያቂነት አዲስ መስመር ቀራጭ መሃንዲስ ይሆናል ብዬ አምናለሁ። ለሚያደርጉት ትጋት እና ጽናታዊ

ምፃዕተ አማራ።

ምስል
  ምፃዕተ አማራ። አሁንም አማራ ዬ100 ሚሊዮን ህዝብ ችግር ተሸክሞ እራሱን ለሰማዕትነት ብቻ እንዲያሰናዳ የሌት ተቀን ተልዕኮ ለማሳካት በወረፋ ተሰልፏል። ለአማራ ህዝብ ያለው ፈጣሪ አምላክ ብቻ ነው። እኔ እምነቴ በአምላኬ ብቻ ነው። ተስፋዬም አምላኬ ብቻ። "ዬቤትህ ቅናት በላኝ።" ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 30/05/2023 ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

ኢትዮጵያ ያለችበትን የሲኦል ዘመን ያሳያል።

ምስል
      ጭንቅ ላይ ያለው አርቲስት ታሪኩ ኢትዮጵያ ያለችበትን የሲኦል ዘመን ያሳያል። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" መስቀል አደባባይ ተናገር ሲሉት አልገባንም። የገባን ቅኑ አማራ የሰጠውን ድጋፍ አንስቶ ከባህር የወጣ አሳ ሲሆን ነበር። ዓለምን ያነጋገረው፣ የአለምን የጥበብ ዓውድ በአንድ መንፈስ የገራው፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ግሎባል ተደናቂነት ያተረፈው አርቲስት ታሪኩ በምን አይነት ስልት ጭብጥ፣ ኩምትር እንዳደረጉት ዛሬ ጥዋት አዬሁት ሰይፋሻ ሾው ብድግ እና ዘጭ፣ ዘጭ እና ብድግ ትዕይንቱን። ለጋው የጥበብ ሰው ቅባዕውን ትቶ ከቤቱ ይቀመጥ ዘንድ የታቀደው የኦነግ ግብ ተልዕኮውን ፈፅሟል። ብቅ የሚል ኢትዮጵያዊ አይፈቀድለትም። ይህን እንደ አንድ ኦብጀክት ወስዶ ጥናት ቢሠራበት የሄሮድስ አብይ አህመድ አሊ (ዶር) ጥልቅ ፕሮጀክት #ሰውን #ማፈረስ እንደምን እንደሚሳካላቸው ያሳያል። እሳቸው ከመጡ ከቀደመው የተወጠነው ከእረኛዬ፣ የእግር እሳት በስተቀር አንድ የተሳካ የጥበብ ሁነት ኢትዮጵያ አላዬችም። ሥራወችን ስታዩ አዳዲሶችን ቅባዓ የበነነባቸው ነው። እንደ ሌላው ቦታ ተቸምችው ለዛ ቢስ ሆኖ ታገኙታላችሁ። ጀምራችሁ አትጨርሱትም። እንደ እንጨት የተገተረ ሸክም ይሆንባችኋል። ያ አልባብ ባልባብ የነበረው የጥበብ አውድ ሸሽቷል። ለነገሩ በደም ለተነከረ ዘመን። ጥበብ የተቀበረበት ዘመን ላይ እንገኛል። ዋናው ዒላማው ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰብዕና እንዳይፈጠር ነው። ሚስጢሩ ያ ነው። ሁለተኛው አናቱ ጉዳይ ዬኢትዮጵያ ክብር እና ሞገሷ በጥበብ ውስጥ ማዬት ለኦነግ #ጣሩ ስለሆነም ነው። ሚስጢረ ኢትዮጵያ፣ ዓዕማደ ኢትዮጵያ ኦነግን ያጣጥረዋል። ሌላው የህዝብ መንፈስ ተረጋግቶ መኖሩም አይፈቀድም። ሁልጊዜ በሰበር መሰባበር አለበት እና። ያልንኮተ ኢትዮጵያዊ መንፈስ ያለ እንዳ