እምዬ ሲዊዝ የዓለምን ክፋ ነገር ያሸነፈች #ጀግና ናት። እምዬ ሲዊዝ የዓለምን ጭካኔ የተጠዬፈች የርህርህና #ንግሥት ናት። እምዬ ሲዊዝ ህውከትን ሃራም ያለች የሰላም #ልዕልት ናት።

 

እምዬ ሲዊዝ የዓለምን ክፋ ነገር ያሸነፈች #ጀግና ናት፤ 
እምዬ ሲዊዝ የዓለምን ጭካኔ ፈጽሞ የማትተባበር #ንፁህ አገር ናት።።
 
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
እምዬ ሲዊዝ የዓለምን ክፋ ነገር ያሸነፈች #ጀግና ናት።
እምዬ ሲዊዝ የዓለምን ጭካኔ የተጠዬፈች የርህርህና #ንግሥት ናት።
እምዬ ሲዊዝ ህውከትን ሃራም ያለች የሰላም #ልዕልት ናት።
እምዬ ሲዊዝ በአዬር ብክለት ህዝቧም፤ እንግዶቿም፤ ጎረቤት አገራትም ጤናቸው እንዳይጎዳ ልዩ #ፀጋ ያላት አገር ናት።
እምዬ ሲዊዝ #ነፃነትን ለሰው ልጆች በትክክል፤ በዕውነት ገቢር ላይ ያዋለች ድንቅ አገር ናት።
እምዬ ሲዊዝ ለመንፈስ፤ ለመላ አካላት #መረጋጋትን በነፃ የምታድል ድንቅ አገር ናት። እምዬ ሲዊዝ #አሸናፊ ናት። ለምንግዜም።
 
 
 No photo description available.May be an image of 1 person, playing soccer and playing footballMay be an image of 5 people, people playing football, people playing soccer and text
 May be an image of 4 people, people playing football, people playing soccer and textMay be an image of 3 people and text
እምዬ ሲዊዝ የዓለምን ክፋ ነገር ያሸነፈች #ጀግና ናት።
እምዬ ሲዊዝ የዓለምን ጭካኔ የተጠዬፈች የርህርህና #ንግሥት ናት።
እምዬ ሲዊዝ ህውከትን ሃራም ያለች የሰላም #ልዕልት ናት።
እምዬ ሲዊዝ በአዬር ብክለት ህዝቧም፤ እንግዶቿም፤ ጎረቤት አገራትም ጤናቸው እንዳይጎዳ ልዩ #ፀጋ ያላት አገር ናት።
እምዬ ሲዊዝ #ነፃነትን ለሰው ልጆች በትክክል፤ በዕውነት ገቢር ላይ ያዋለች ድንቅ አገር ናት።
እምዬ ሲዊዝ ለመንፈስ፤ ለመላ አካላት #መረጋጋትን በነፃ የምታድል ድንቅ አገር ናት። እምዬ ሲዊዝ #አሸናፊ ናት። ለምንግዜም።
 
#እምዬ ሲዊዝ እና እግር ኳስ። የአውሮፓ ጨዋታም በእኔ ቅኝት።
 
እምዬዋ ኳስን ለሰው ልጅ የህሊና ሰላማዊ #ቴራፒ የምታይ ናት። ስለዚህ ውድድሩም፤ ፋክክሩንም የምታዬው ከዚህ ጥልቅ ዕሳቤ በመነሳት ነው። የሲዊዘርላንድ ድንቅ የእግር ኳስ ቲም፤ ክሩው፤ አሰልጣኙ እንደ እናታቸው እምዬ ሲዊዚ በፍፁም ሁኔታ #የተረጋጉ ነበሩ። እኔ ያስተዋልኩት ይህ ነው። መረጋጋት ደግሞ ስንት የዓለምን ህውከት ሊታደግ እንደሚገባ ሊታወቅ ይገባል። እራሱ ኮሌጅም ነው።
 
እምዬ ሲዊዝ በተገኜችበት፤ በታደመችበት ቦታ ሁሉ #ስክነት - በመርህ፤ እርጋታ - #በህግ ከብረው ይገኛሉ። እስኪ ከሲዊዝ ፖለቲከኞች ከሌሎች አጋሮች ጋር ባለ ግንኙነት አንጥፋልኝ፤ ጎዝጉዙልኝ የሚል አይታችሁ ታውቃላችሁን? እምዬ ሲዊዝ ሰባት መሪ ነው ያላት። ሁሉም እንደ አንድ፤ አንዱም እንደ ሁሉ ተስማምተው፤ ተግባብተው፤ ተደማምጠው ኃላፊነታቸውን በተሰጣቸው የህግ የምርጫ ጊዜ በርጋታ፤ በስክነት ይከውናሉ። የሚጎድል ነገር የለም። ሥርዓቱ #መርኽ ዘለቅ ነውና።
 
የእግር ኳስ ቲሙን እኔ የማዬው ከሲዊዝ አጠቃላይ ተፈጥሮ አንፃር ነው። እግዚአብሄር ይመስገን አሁን ብቁ፤ ሊቀ- ትጉኃን፤ ጭምት አሰልጣኝ ብሄራዊ ቲሙ አግኝቷል። የእምዬ ልጆች ቋሚ በሆነ ብቃት እስከ መጨረሻው ተፋልመዋል። ጨዋታውን ያልቀጠሉት #በፔናሊቲ ምክንያት ነው። ፔናሊቲ ደግሙ ቀን ሲሰጥ እና ዕድል ድምር ነው ድሉ። 
 
 ቀድመው ጎል ያስቆጠሩ እነሱ ነበሩ። ጎሉ እንደገባ ደስታ ነበር። ያ ደስታ ላይ እያሉ ነበር ተጋጣሚያቸው የእንግሊዝ ቡድን አፀፋውን ጥቃት ፈጽሞ #አቻ የምታደርገውን ነጥብ ያስቆጠረው። ይህ ሊገጥም የሚችል ነገር ነው። ተፈጥሯዊም ነው። 
 
ጨዋታው ተራዘመ። በተራዘመው ጊዜም ግባቸውን ሳያስደፍሩ 30ው ደቂቃ ተጠናቀቀ። ከዛ መለያው ፔናሊቲ መጣ። ፔናሊቲ ላይ እኔም ስጋት ነበረኝ። ይህንንም አስቀድሜ ጽፌው ነበር። ፔናሊቲ ዕድልም ስለሆነ። ለፔናሊቲ ፀጋ ያላቸው እና የሌላቸው ተጫዋቾች ስለሚኖሩም። በዚህም አንድ ብቻ ነው የሳቱት። 
 
ይህ እራሱ ለእኔ የሰጠኝ ግብረ መልስ የእምዬ ሲዊዝ ቲም በፔናሊትም ወደፊት #ተስፋ እንዳለው ነው። የተከደነ አቅም የሲዊዝ ብሄራዊ ቡድን አለው።
 
ሌላው የእንግሊዝ ብሄራዊ ቲም ጋር ነው የገጠሙት። የእንግሊዝ ብሄራዊ ቲም ሁለት ጨዋታ አይቻለሁ አጨዋወታቸው #ሞናትነስ ነው። ሞናትነስ ጨዋታ ለተጋጣሚውም፤ ለተጫዋቾችም አድካሚ እንደሚሆን ይታወቃል። ለተመልካችም እንዲሁ። ልዝ እንጨት ታውቃላችሁን? ልዝ እንጨት ወይ አይነድ፤ ወይ አያነድ ዓይነት። ሲዊዝሻን የገጠማት ይህ ነው። 
 
አንድም ማራኪ የኳስ አርት የተፈጠረበት አገር የእንግሊዝ ቡድን እንደ ቀደምትነቱ ጥበብ አላዬሁም። ከስሎብም ጋር፤ ከሲዊዝሻም ጋር ባደረጉት ጨዋታ ማን ተጫውቶላቸው #ለቀጣዩ ዕድል እንደበቁ እግዚአብሄር ይወቀው። 
 
የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድንም አልፏል። በዚህ ዓመት ፈረንሳይ በምን ሁለገብ አቅሙ? የዕድል ጉዳይ ካልሆነ። ስፔኖች ሁልጊዜም #ቋሚ አቅም ነው ያላቸው። ወደ ላይ አይስፈነጠሩም፤ ወደ ታችም ዝቅ አይሉም። ኮንስታንት አቅም ነው ያላቸው። 
 
በቀጣይ ጨዋታዋች ያው እንግሊዝ አሰልቺ አቅሙን ይዞ ገብቶ ጨዋታውን ለዛለዞ ካላደረገው በስተቀር ስፔኖች ለዋንጫ ሰፊ ዕድል ይኖራቸዋል። በተለይ ከፈረንሳይ ጋር ከተገናኙ ጨዋታም እናያለን ብዬ አስባለሁ። የአውሮፓ ጨዋታ እኔ ዋንጫው ሳይሆን የሚናፍቀኝ የጥበቡ ማቹሪቲ ነው። ጀርመን እና ስፔን ያደረጉት ፋክክር ደረጃውን የጠበቀ የጨዋታ አርት ነበር ያዬነው።
 
ትናንት ምሽት ላይ ሆላንዶች ቀንቷቸዋል። ቱርኪወች ነበሩ መጀመሪያ ለግብ የበቁት። ሆላንዶች አቻ የምታደርጋቸውን ነጥብ ካስቆጠሩ በኋላ ወዲያውኑ ማጥቃታቸውን አጠናክረው ቀጥለው ሁለተኛ ግብ አስቆጥረው በሙሉ የጨዋታ ጊዜ ቱርኪወች የእምዬ ሲዊዝ ዕድል ገጥሟቸዋል። ዘንድሮ ቱርኪ ትንታግ ተጫዋቾችን ይዞ ነበር የቀረበው።
በቀጣይ ጨዋታ ሆላንዶች የሚገጥሙት #የእንግሊዝን ብሄራዊ ብድን ነው። 
 
የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን የግል ብቃት ያላቸው ኮከብ ተጫወቾች ቢኖሩትም ሜዳ ላይ ይህን አቅም አቀናጅቶ የመጫወት ኮኦርድኔሽን ስስ ሆኖ አይቻዋለሁ። ጨዋታቸው አሰልቺ፤ እና ለተጋጣሚው ቲም አድካሚም የሆነው ይህ ይመስለኛል እንደ እኔ እይታ።
 
የእምዬ ሲዊዝ ልጆች ሁሉንም አቅማቸውን ተጠቅመዋል። በችግር ጊዜ መፍትሄ የማፍለቅ ልዩ ተስጥኦ ያለውን #ሼኪሪንም በተራዘመው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠቅሟል። ልክ 60 ደቂቃ ላይ ቲሙን #ሪፍሬሽ የሚያደርግ ዳብል የተጫዋቾች ቅዬራም አድርጓል። ጨዋታው ሲራዘምም ለፔናሊቲ ብቁ የሆኑትን ወደ ጨዋታው አስገብቷል። #ቀረ የሚባል ነገር የለም። በአሰልጣኙ በኩል የለም። 
 
ቅንጣት ወቀሳ ማቅረብ አይቻልም። እኔ የጀርመኑን ZDF ውይይት ቀድመው የሰጡትን ትንብያ ተከታትያቸዋለሁ። ሙሉ #ኮንፊደንስ በእምዬ ሲዊዝ ልጆች ነበራቸው። በጣም እርግጠኛም ነበሩ የእምዬ ሲዊዝ ልጆች ለቀጣዩ ዕድል እንደሚበቁ።
 
በዕለት ዕለት ህይወታችን ፈቃደ እግዚአብሄር አለ። የዩንቨርስ ተፅዕኖም ቀላል አይደለም። እርግጥ ነው የእምዬ ሲዊዝ ልጆች ለቀጣዩ ዕድል በቅተው ቢሆን ኖር ሆላንድን #ከማሸነፍ፤ ለዋንጫ ጨዋታ ለመብቃት ምንም የሚያግዳቸው ነገር አልነበረም። እንቅፋት የሆነው የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን #ሞናትነስ የሆነው የአጨዋወት ስታይሊንግ ነበር።
 
ስሎባኪያም ለቀጣዩ ጨዋታ ያልታደለው በዚህ ነው። ስሎቦች ቀንቷቸው ቢሆን ጥሩ ጨዋታ ከአብሪ ድል ጋር ለእምዬ ሲዊዝሻ ይሆን ነበር። እኔ ዛሬ ያብራራሁትን የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን በቀጣይ ከሆላንድ ጋር በሚኖረው ጨዋታ ማዬት ትችላላችሁ። ካላስተካከሉት። ወይንም ተመልሳችሁ ሁለቱን ጨዋታ እዩት። አድካሚ፤ አሰልቺ የአጨዋወት ስልት ነው እዬተከተሉ ያሉት።
 
 
ገዳማዊቷ እኔ የምኖርባት ቪንተርትሩ ፀጥ ረጭ ብላለች። ማምሻውን ምንም የአውቶሞቢል ድምጽ አልነበረም። አሁን ከእኛ 10.37 ነው የፀጥታው ግርማ ይገርማል። እንዲህ የሚሆነው የባይናክተን ምሽት እና ማግሥት ነበር። ዛሬ ድባቡ ፀጥ ረጭ ነው። ግብረ መልሱ ተገምቶ የነበረው ሐሴትን የማጣት ይመስላል። እርግጥ ነው አብዛኛወቹ የሲዊዝሻ ዕለታት የተረጋጉ ዝምተኞች ናቸው።
 
ሲጠቃለል በዚህ ወሳኝ ጨዋታ የእምዬ ሲዊዝ ልጆች የመጀመሪያውን ጎል በእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ላይ፤ በጀርመን ብሄራዊ ቡድን ላይ፤ በጣሊያን ብሄራዊ ቡድን ላይ ማስቆጠር ዕፁብ ድንቅ ብቃት ነው። ከዋንጫ በላይም ድል ነው። 
 
ከሁለት ዓመት በኋላ በሚካሄደው የዓለም ዋንጫም የሲዊዝ መላ ህዝብ ልጆቹን በሞራል ሊያግዛቸው ይገባል። በዘርፋ አቅም ያላቸውም ሙሉ ተሳትፎ በማድረግ ኳስ ሰላም ነውና ድሉን ለሰላማዊቷ አገር ለማብቃት ከእያንዳንዱ በግል ከሁሉም በጋራ ብርቱ ጥረት ይጠበቃል። እነኝህን ዕንቁ ልጆች መርዳት ይገባል። ብሩህ አሰልጣኙም በሙሉ አቅም ሊታገዙ ይገባል።
 
ጀርመን በሚመለከት ትንሽ ልበል። ሙሉ አትኩሮት የሚሰጠው የጀርመን ብሄራዊ እግር ኳስ ብዙ ሥራ ከፊቱ እንደሚጠብቀው ይሰማኛል። ብዙ መሥራት አለባቸው። ጎረቤት አገር ኦስትርያም በድንቅ ብቃቱ እንዲቀጥል ተስፋዬ ነው። ምክንያቴ ትውልድ በትክክል የሚታነጽበት፤ ክፋትን፤ ጭካኔን፤ ጥላቻን የምንታገልበት ትልቁ መድረክ ሰላማዊው የእግር ኳስ ጨዋታ ስለሆነ። 
 
በእግር ኳስ ውስጥ ፍቅር አለ፤ ትህትና አለ፦ መከባበር አለ፤ ዕውነት አለ፦ መተዛዘን አለ፦ ህግ አለ፦ ዳኝነት አለ፤ ደስታ አለ፦ ህብራዊነት ኢንተግሬሽን አለ፤ ተስፋ እና ሳቅ አሉ፤ ጋብቻ እና ፍቅርም አለ። ኢኮኖሚም። ዕውነት እና መርህም አለ። ጥበብ ፕሬስም አለ።
ሙሉ ፍቅር በትህትና ለሲዊዝ ብቁ፦ ትጉህ ብሄራዊ ቡድን።
 
ዕንቁ ዕድል ቢያመልጥም ዕንቁ ዕድል ፊት ለፊት ይጠብቃል። ተስፋ አያልቅም፤ ተስፋ አይዝልም፤ ተስፋ አይደክምም። ተስፋ ትጉህ የድል አርበኛ ነው። ተመክሮው እራሱ ድል ነው። ወጣቶችን ያቀፈ ስለሆነም ለቀጣይ ጊዜ ብዙ ችግር አይገጥምም። በዕድሜ ምክንያት የሚሰናበቱ የሉም እና። ብቃቱን ወደ ልቅና ማሳደግ ብቻ ነው የሚጠበቀው። ይህን ማድረግ ደግሞ ይቻላል። ይቻላል። ለእኔ አሸናፊወች ናችሁ! Stolz. Punkt.
 
#ልዩ ማስታወሻ።
 
የሲዊዝን እግር ኳስ ኮከቡን የሸኪሪን ፎቶ የለጠፍኩት ሸኪሪ ለቡድኑ ወሳኝ ስለሆነ ነው። የትውልዱ ሞዴል ነው። ጭንቅላቱ መፍትሄ የማፍለቅ ፍጥነቱ ሁልጊዜ ይገርመኛል። ብዙ ታዳጊወች በእሱ መንፈስ ተነሳስተዋል። ትውልድ ነው። ከሁሉ በከባድ የጨዋታ ጊዜ መፍትሄ የማፍለቅ አቅሙን አድናቂው ነኝ። በጣም ያላጠረ ጊዜ ካገኜ ልዩ ነው። 
 
#ቅባዕም አለው። ጨዋታው ከረዘመ ደግሞ ይደክመዋል። የሲዊዝ ብሄራዊ ብድን ሸኪራን ሊያጣ አይገባም። #በአማካሪነት ቢጠቀምበት፤ ታዳጊወችን በማሰልጠን ዘርፍ እራሱን የቻለ ዲፓርትምነት ኑሮ ኮከብ ሸኪሪ ቢመራው የሚል ዕሳቤ አለኝ፤ ቢታሰብበት መልካም ነው።
የእኔ ውዶች እንዴት አረፈዳችሁ። ደህና ናችሁ ወይ። መልካም ሰንበት። አሜን።
 

ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
07/07/924
ተስፋ ከድል ጋር ያገናኛል ብቃትን ወደ ልቅና ማሳደግ ከተቻለ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።