የፈራሁት ነው የሆነው። ከጨዋታ በኋ ላ የትናንት ማምሻ ዘገባዬ።

 

የፈራሁት ነው የሆነው። ጨዋታው 1-1 ነበር። መጀመሪያ ጎል ያስቆጠሩት የእምዬ ሲዊዝ ልጆች ነበሩ። ደስታቸውን ሳይጨርሱ ነበር እንግሊዞች አቻ የምታደርጋቸውን ጎል ያስቆጠሩት።
ከእንግሊዞች ጋር ጨዋታ ሞናትነስ ነው። የእምዬ ልጆች በብቃት ተጫውተዋል። ፔናሊቲ እምፈረው ነገር ነበር። ደረሰ። ይህም ሆኖ ያልጠበቅኩት አቅም ከእምዬ ሲዊዝ ልጆች አይቻለሁ። አንድ ነው የሳቱት። ይህ መልካም አቅም ነው።
ዘጠና ደቂቃ በእኩል ነጥብ። ተጨማሪ ሰላሳ ደቂቃ በእኩል ነጥብ። በፔናሊቲ አንድ መሳት ነው ከቀጣዩ ጨዋታ የእምዬ ሲዊዝ ልጆች የተሸነፋት። ብቃት ያለው ጨዋታ አሳይተዋል። ቲም ወርካቸው የሚደንቅ ነበር። ቀጣዩ ቱርኪ እና ሆላንድ ናቸው። ሁለቱም ድል ርቋቸው የኖሩ ስለሆኑ እንዲቀናቸው እመኛለሁ። እንግሊዝ ከአሸናፊው ቡድን ጋር ይገጥማል ማለት ነው። ነገ በተረጋጋ መንፈስ በሚገባ እጽፈዋለሁኝ።
የእምዬ ሲዊዝ ልጆች አንዲት ትንሽ ነገር ማድረግ ቢችሉ ተጨማሪ ጊዜውም ፔናሊቲም አይመጣም ነበር። መልካም ሌሊት። አሰልጣኙ ትጉህ እና ብርቱ ሲሆን ሊሆን የሚገባውን ሁሉ አድርገዋል። እራሱ ሼኪሪን ልቤ አስቦት ነበር። ገብቶ ጥሩ ጨዋታ አሳይቷል።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
06/07/024
ለቀጣዩ ተስፋ እግዚአብሄር ይጨመርበት። የእምዬ ልጆች ጥሩ ደረጃ ላይ ነው የሚገኙት።
 England gegen Schweiz
 

google.com
England gegen Schweiz
Spielinformationen, Neuigkeiten u

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።