ልጥፎች

"WORLDFIRST"

ምስል
  "WORLDFIRST" የጨዋታ ሰዓት እረፍት እና ተጨማሪ ደቂቃወች ታክለው። 21.02 - 22.56 ቀን 14.06.2024   ዛሬ በጀርመኑ ሙኒክ አሪና ስኮትሾቹ እና ጀርመኖች ከምድብ #Aየ2024 የእግር ኳስ ውድድር የመክፈቻ ግጥሚያቸውን አካሄዱ። ቀዝቀዝ ብሎ የጀመረው ጨዋታ በጀርመኖች 4 ጎል በአንድ ቅጣት ምት 5 ለአንድ በሆነ ውጤት ጨዋታው ተጠናቋል። ጀርመኖች እግር ኳስን ከብሄራዊነት ጋር አዋህደው ስለሚዩት ልዩ የህሊና አቅም አይባቸዋለሁ።   ዛሬ ቀዝቀዝ ብሎ በተጀመረው እግር ኳስ ውድድር ስቲዲዮሙም አልሞላም ነበር። የባዬር ሙንሽንን የፍፃሜ ውድድር ያህል እንኳን ደምቆ አላዬሁትም። የሆነ ሆኖ የጀርመኖች ቀደምት ጎል ጠባቂ አማኑኤል ኖዬር፤ ቶኒ ሙለር ከነባሮቹ ተጫወቾች አይቻለሁ። አብዛኞቹግን አዲስ እና ወጣቶች ናቸው። አሰልጣኙ እራሱ ወጣት ናቸው አዲስም።   ጀርመኖች የመጀመሪያውን የጨዋት ክፍለ ጊዜ ሦስት ነጥብ አስቆጥረው ነበር የተጠናቀቀው። የቅጣት ምቱን ማግኜታቸው ብቻ ሳይሆን ስኮትሾች አንድ ተጨዋች በቀይ ካርድ ተቀጥቷል። ሁለተኛው ክፍለጊዜ አንድ ተጫወቻቸውን ስኮትሾች ሚስ ቢያደርጉም ለአንድ ጎል በቅተዋል።    ደጋፊወቻቸውም ትንሽ ተነቃቅተው ነበር በሁለተኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ጀርመኖች ሁለት ግብ በማስቆጠር 5 ለ 1በሆነ ውጤት ጨዋታው ተጠናቋል።   ጀርመኖች መጀመሪያ ዕድል ከቀናቸው ይጠነክራሉ። መጀመሪያ ጎል ከተቆጠረባቸው ግን ይዝላሉ። እንደ እረጅም ጊዜ ተከታታይ በዚህ ዙሪያ አሰልጣኞቻቸው ቢሠሩ መልካም ይመስለኛል። የመጀመሪያ ጎል ማስቆጠር ጥረት ማጠናከር ወይንም ጎል ከተቆጠረባቸው መጀመሪያ ላይ ሳይዝሉ ጠንክረው መቀጠል።    ዕውነት ለመናገር ያ ደማቁ የአውሮፓ እግር ኳስ ጨዋታ አይመስልም። የበረደው ነበር። ዓለም ትቅደ

#አማራነት #ወንጀል #አይደለም።

  #አማራነት #ወንጀል #አይደለም።   ለዓላማቸው #የማይሰበሩ ሳተናወች። ዕውነት ይምራኝ ብለው የፈቀዱ #የብዕር #ትጉኋን አማራነታቸው ብቻ ያሳሰራቸው #የነፃነት ዓራት ዓይናማወች። ያልተበገሩ የማይበገሩም። የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ፀረ አማራ አስተዳደር ፊት ለፊት የሞገቱ ደፋሮቹ። አይዟችሁ ውዶቼ እንደ ደመነ አይቀርም ይበራል - ይፈካል። አማራነት ወንጀል አይደለም። ግን የእኔ ውቦች እንዴት አደራችሁልኝ? ሥርጉ 15/06/024 #አማራነት #ይከበር ! #አማራነትን #መበቀል #ይቁም ! #ዕውነት #በመርኽ #ያሸንፋል ።

ፋኖሻ ባንክ #አይዘርፍም። #ሲያምራችሁ ይቅር። ማጣፊያ ሲያጥር የሞገድ ጋዜጣ ትዕይንትን መዘዝ።

ምስል
    # ፋኖሻ ባ ንክ #አይዘርፍም ። #ሲያምራችሁ ይቅር። ማጣፊያ ሲያጥር የሞገድ ጋዜጣ ትዕይንትን መዘዝ። #ፋኖ #ማንነቱን #አይዘርፍም ። ፈጽሞ። ፋኖሻ #ኢትዮጵያን ያከብራታል ያስከብራታል እንጂ አይዘርፋትም። የአማራ ሕዝብ የዘረፋ ታሪክ የለውም። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ በውጭ አገር ፈሰስ አድርገው የያዟቸው አገር ቤት ለጠቅላዩ ሥልጣን የሚታገሉ የመሹ አሉ። እኔ አውቃለሁ ይህን። ሙሉ 6 ዓመት እኔን መዳፋቸው ውስጥ ለማስገባት ታክተዋል። ግን አልቻሉም። ፋኖ አደራጀን ብለው አብሬያቸው እንድሠራ ጠይቀውኛል። ህሊናዬን እንዳከራይ። መታሰቡ እራሱ ይገርመኛል። እራሴን አፍርሼ በደራሽ ግርግርግር እንደማልጨባረቅም ልቦናቸው ያውቀዋል። የሆነ ሆኖ ፋኖ ሰማይ ዝቅ ምድር ከፍ ቢል የህዝብ ገንዘብ ይዘርፋል ብዬ አላስብም። ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አይደለም ኢትዮጵያን ታላቋን አሜሪካ የሰለሉ እኮ ናቸው።ግዑዝ አካል የሰላም ሚር ብለው፤ ባልተፃፈ ድንጋጌ ከኤርትራ ጋር ተስማማሁ ብለው ዓለምን አላግጠውበት እኮ የመጀመሪያው የሰላም የኖቤል ኢትዮጵያዊ ተሸላሚ ሆነዋል እኮ። አይደለም በሚገዙት አገር። ቀርቶ። የሞገድ ጋዜጣ ልበ ወለድ መሞከሪያ ጣቢያ ኢትዮጵያ ካደረጓት ሙሉ ስድስት ዓመት። ሴራው እና ዜናው እኩል ይወጣል። 100 ቀናቸው እራሱ በሞገድ ጋዜጣ ትዕኝት የተቃኜ ነበር። እኔ እምነግራቸው ይቅርበወት ነው። ፋኖ መነፈሱ የሚሊዮን ድምጽ ነው። መቼውንም አያሸነፋትም። እርስወ ግን ይሸነፋሉ። መልካሙ ነገር ድልዝልዝ ያለው በሴራ ጉዞ ታርሞ ወደ ዕውነት መቀራረብ ነው የሚበጀው። የህዝብ ዕንባ የጠራው መንፈሱ ትሁት፤ ቅን ገር እና ቆፍጣና ነው። የቀናውም ይሄው ቅንነቱ እና ፍፁም ታማኝነት ነው። ስርቆት ዝርፊያ የአማራ ህ

ጥሳም።

  ዕውነት አንደበትን #አስገድዳ #ታስከፍታለች ። #ዝምታን ጥሳም። ሥርጉ2024/06/15

#ትቀጠቅጥማለች።

  በቀል #ትቀጣለች ። #ትቀጠቅጥማለች ። ሥርጉ2024/06/15

#የፈካ

  ዕውነት አያኮርፍም። ዕውነትም #አያድምም ። ዕውነት ባህሬውም ተፈጥሮውም #የፈካ #ያስቻለው #የተደሞ #ምዕራፍ ነው። ሥርጉ2024/06/15

እንዲያውም

 ዕውነት #ውድድር #ፋክክር ውስጥ ትውር አይልም። እንዲያውም ዕውነት ምንም ዓይነት #ፕሮፖጋንዳ ፤ የትኛውንም ዓይነት ፕሮፖጋንዲስት ፈልጎ አለማወቁ ልዩ #ክስተት ያደርገዋል። ሥርጉ2024/06/15

#መትነን

  የሰው ልጅ ዕውነትን ገፍቶ ስለምን ዕብለትን እንደሚያስጠጋ አይገባኝም። #እንዲገባኝም #አልፈቅድም ። ለምን? በወናነት መኖር ስለማልሻ። ዕብለት እኮ #ቀፎ ነው። ዕብለት #ወናነት እኮ ነው። ምን አለኝ የሚለው አለው አይዋ ዕብለት? #ብን #ትን ብቻ። የነጠፈም ነው። ለአደራም፤ ለትውልድ ቀርቶ ለራሱም #መትነን ነው ነገረ ስራው። ሥርጉ2024/06/15

#ፈረስ #በኋላ #እግሩ

  #የኢትዮጵያ #ፖለቲካ #ባህል #ፈረስ #በኋላ #እግሩ #ሲጋልብ #ዓይነት #ነው ። #ዛሬም #ድብድብ #ነገም #ድብድብ ። የዱላው #ክትክታ አለማለቁ ይገርመኛል። አልቦሽ። ሥርጉትሻ2024/06/15

#ግሽፈት

 የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ብቻ አይደለም #ግሽፈት ( #ኢንፍሌንሽን ) የገጠመው። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ባህልም ( #ኢንፍሌሽን ፤) #ግሽፈት ገጥሞታል ብዬ በጽኑ አምናለሁ። ሥርጉ2024/06/15

ስትል

  ጥበብን ስፍ ብዬ የምወዳት #የልብን ስለምታናግር፤ ስለምታደፋፍርም ነው። ጥበብዬ #ስታጽናና #ከህሊናዋ ነው። #አይዞሽ ስትል እኮ ቁልምጫዋ #በገፍ #ማዕዱን አቅርባ ነው። ሥርጉትሻ 2024/06/15

#አንጎል #ድንቢጥም አላት

  #አንጎል #ድንቢጥም አላት። እኛ የምንለዬው #ህሊና ስላለን ነው። ህሊናችን ደግሞ #ለተፈጥሯዊነት እና #ለሰባዕዊነት #ብቻ ነው የተፈጠረው። #ዕብንነት መፍቀድ #አንጎል ብቻ ይኑረኝ ማለት ነው። ሥርጉትሻ2024/06/15

ሐሤቴ

  ከዘለለው ጋር #አለመዛለሌ ። ከጎረፈው ጋር #አለመጉረፌ ። ሥርጉትሻ 2024/06/15

በተከፋች

  በተከፋች አገር ውስጥ የሚያድጉ ወጣቶች ሁለመናቸውን #ተዘርፈው ያድጋሉ። ወጣትነታቸውንም ይዘረፋሉ ከሞት ከተረፋ። ይህ ማለት ለምን #ተፈጠራችሁም ነው። ሥርጉትሻ 2024/06/15

Traumhaft. ቅኒት ሆይ! እንኳን ቀናሽ። ተመስገን።

ምስል
  Traumhaft. ቅኒት ሆይ! እንኳን ቀናሽ። ተመስገን።   ሲዊዝ እና ኡንጋር ጨዋታቸውን አሁን አጠናቀቁ። የሲዊዝ እግር ኳስ ብቃት ልዩ ነበር። ሲዊዞች በመከላከል ላይ የሚያተኩሩ ጨዋታቸው ፍፁም ሰላማዊ ነበር። ዛሬ አራት ደቂቃ ላይ ነው ባለ ቢጫ ነበር የሆኑት። ጨዋታቸው በተለይ የመጀመሪያ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ አግሬሲብ ነበር። የቲም ወርኩ፤ ቅንጅቱ የተሟላ ነበር። በመከላከል ሳይሆን ማጥቃት ተኮር ነበር። ከትናንቱ የስኮትሽ እና የጀርመን የመክፈቻ ጨዋት ይልቅ ዛሬ ሞቅ ያለ ጥሩ ፋክክር ነበረው። አርቱም ሳቢ ሆኖ ነው አገኜሁት። የሲዊዝ አንከር ተጫዋች ጭምቱ እና ተወዳጁ አንድ ሚሊዮን የፌቡ ተከታይ ያለው #ሸኪራ ባይኖርም ንቁው #ሻካ ነበር። #በጠይም #ዕንቁ #ህብርነት በአዲስ አሰልጣኝ፦ በልዩ የጨዋታ ቴክኒክ ያዬሁት የቅድስት አገር የሲዊዝ ጨዋታ ለእኔ ልዩ ነበር። የተነቃቃ የውስጥ የሆነ ነበር። በጨዋታው አራት (4) ቢጫ፥ ለበርካታ ጊዜ የማዕዘን ምት ሲዊዞች አግኝተው ነበር። በነገራችን ላይ የሲዊዝ ጎል ጠባቂም #ምስጉን የተረጋጋ እና ጠንካራ ከሚባሉት ውስጥ ነው። ዛሬ። ፈጽሞ ያልጠበቅኩት የጨዋታ ትዕይንት ከሲዊዝሻ ቲም አዬሁ። ስለሆነም ቀጣይ ተስፋውን #ስሰፍረው #ቲፍ ። #ሲዊዝ 3 ለአንድ ኡንጋርን ረታለች። የሚገርመው ሦስተኛው ጎል በተስተጓጎለ የጨዋታ ጊዜ የተገኜ በተጨማሪ ጊዜ የተገኜ #ታካይ ድል ነበር። ቦነስ ይባል። ሌላው ደጋፊም የሲዊዝ በበቂ ሁኔታ መኖሩ ብቻ ሳይሆን #አትኩሮቱም ተሳትፎውም #ልዩ ነበር። አዬ ድንቡልቡልዬ ሚሊዮንን በፍቅር ልትነጂ የተፈጠርሽ። ታድለሽ! ድለቃው ፌስታሽ ኢቬንትሽ። ምሩቅ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 15/06/2024 #ኳስዬ የማቱሳላን ዕድሜ!

ዶ/ር አብረሃም አመሓ ሜታ ፊዚክስ 5% Vs 95%

ምስል

Live:ሜታ ፊዚክስ ሃሳቦች ዙሪያ አቅራቢ: ዶክተር አብረሃም አምሃ

ምስል

በስደት ተሳትፎዬ በፎቶ የተደገፈ ፌቡ ላይ አለ ማየት ትችላላችሁ።

  Facebook https://www.facebook.com › sergute.selassie

የሞዴል፤ ሞድሬተር ዳኛ እና የአዲስ ሃሳብ አፍላቂ የልዕልት ዬሃይዲ ዓለም እና ለአዲስ ትውልድ ግንባታ ያላት ልቅና።

ምስል
  የሞዴል፤ ሞድሬተር ዳኛ እና የአዲስ ሃሳብ አፍላቂ የልዕልት ዬሃይዲ ዓለም እና ለአዲስ ትውልድ ግንባታ ያላት ልቅና። " የሰው ልብ መንገድ ያዘጋጃል፦ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።" (ምሳሌ ፲፮ ቁ ፱) ጤና ይስጥልኝ የማከብራችሁ የአገሬ ልጆች እንዴት አደራችሁ? ደህና ናችሁ ወይ። ትናንት 19ኛ ዓመቱን ያከበረው የጀርመን ምርጥ ሞዴሎች ውድድር የመጨረሻ ቀን ነበር። ብዙ የተማርኩበት፤ ሁለቱ መፃህፍቶቼ የተፃፋበት መሠረታዊ የመነሻ ሃሳብ ትውልድን ከዘመኑ ሥልጣኔ ጋር፤ መክሊቱ፤ ጥሪው ሜሴጁ ሳያልፍበት በጥዋቱ እንዴት ይገነባል የሚል ፍለጋዬ ዓለም ዓቀፍ የመክሊት ውድድሮችን እንድከታተል አስችሎኛል። 1) 6ኛ መጸሐፌ "የተስፋ በር" ልጆች እና ወላጆችን፤ ልጆቻችን እና ማህበረሰቡ፤ ልጆች እና ግሎባላይዜሽን፤ ልጆች እና መምህራን የመነሻ ሃሳብ የተካተተበት ነው። 2) 7ኛ መጽሐፌ "ርግብ በር" ማህበረሰብ እና ትዳር በትውልድ ግንባታ ላይ ምን ድርሻ አላቸው? ድርሻቸውን እንዲወጡ ዕድሎች እንዴት ማኔጅ ሊደረጉ ይገባል የሚል የመነሻ ሃሳብ ነው። ሁለቱም ጀርመን አገር በታለንት፤ በሞድ፤ በሙዚቃ ውድድር ከማያቸው ክፍተቶች በአገሬ በኢትዮጵያ በማህበረሰብ አደራጅነቴ አያቸው በነበሩ ጥንካሬ እና ድክመቶች፤ እኔ አባቴ አበይ በጥዋቱ ወደ ጥበብ ያስገባኝ ሁኔታ፤ የእናቴ የእብዬ ክትትል በሞድ ዙሪያ ልምዴን ያጋራሁበትም ነው። ሌላው ቁጥቧ ሲዊዝስ በዚህ ዘርፍ ያላትን ተሳትፎ አክያበታለሁ። ብዙውን የተስፋ ጎዳና ዳሜጅ በሚያደርገው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ህሊናን ላለማከራዬት በወሰድኩት እርምጃ ስቶር ያሞቃሉ። እና ለእኔ የኦስትራሽ በስሱ፤ የጀርመን በጉልሁ፤ የሲዊዝ በመጠኑ በዘርፋ የሚካሄዱ ውድድሮች አቅጄ የምከታተላቸው ናቸው።