ፋኖሻ ባንክ #አይዘርፍም። #ሲያምራችሁ ይቅር። ማጣፊያ ሲያጥር የሞገድ ጋዜጣ ትዕይንትን መዘዝ።

 

May be an image of 1 person, smiling, scarf and hospital
May be a doodle of text 
#ፋኖሻንክ #አይዘርፍም#ሲያምራችሁ ይቅር። ማጣፊያ ሲያጥር የሞገድ ጋዜጣ ትዕይንትን መዘዝ።
#ፋኖ #ማንነቱን #አይዘርፍም። ፈጽሞ። ፋኖሻ #ኢትዮጵያን ያከብራታል ያስከብራታል እንጂ አይዘርፋትም። የአማራ ሕዝብ የዘረፋ ታሪክ የለውም።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ በውጭ አገር ፈሰስ አድርገው የያዟቸው አገር ቤት ለጠቅላዩ ሥልጣን የሚታገሉ የመሹ አሉ። እኔ አውቃለሁ ይህን። ሙሉ 6 ዓመት እኔን መዳፋቸው ውስጥ ለማስገባት ታክተዋል። ግን አልቻሉም። ፋኖ አደራጀን ብለው አብሬያቸው እንድሠራ ጠይቀውኛል። ህሊናዬን እንዳከራይ። መታሰቡ እራሱ ይገርመኛል። እራሴን አፍርሼ በደራሽ ግርግርግር እንደማልጨባረቅም ልቦናቸው ያውቀዋል።
የሆነ ሆኖ ፋኖ ሰማይ ዝቅ ምድር ከፍ ቢል የህዝብ ገንዘብ ይዘርፋል ብዬ አላስብም። ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አይደለም ኢትዮጵያን ታላቋን አሜሪካ የሰለሉ እኮ ናቸው።ግዑዝ አካል የሰላም ሚር ብለው፤ ባልተፃፈ ድንጋጌ ከኤርትራ ጋር ተስማማሁ ብለው ዓለምን አላግጠውበት እኮ የመጀመሪያው የሰላም የኖቤል ኢትዮጵያዊ ተሸላሚ ሆነዋል እኮ። አይደለም በሚገዙት አገር። ቀርቶ። የሞገድ ጋዜጣ ልበ ወለድ መሞከሪያ ጣቢያ ኢትዮጵያ ካደረጓት ሙሉ ስድስት ዓመት። ሴራው እና ዜናው እኩል ይወጣል። 100 ቀናቸው እራሱ በሞገድ ጋዜጣ ትዕኝት የተቃኜ ነበር። እኔ እምነግራቸው ይቅርበወት ነው። ፋኖ መነፈሱ የሚሊዮን ድምጽ ነው። መቼውንም አያሸነፋትም። እርስወ ግን ይሸነፋሉ።
መልካሙ ነገር ድልዝልዝ ያለው በሴራ ጉዞ ታርሞ ወደ ዕውነት መቀራረብ ነው የሚበጀው። የህዝብ ዕንባ የጠራው መንፈሱ ትሁት፤ ቅን ገር እና ቆፍጣና ነው። የቀናውም ይሄው ቅንነቱ እና ፍፁም ታማኝነት ነው። ስርቆት ዝርፊያ የአማራ ህዝብ ባህላችን አይደለም። ፍብረካ ዜና ነው። የፋኖ ንቅናቄ የገበሬ ንቅናቄ ነው። #ገበሬ ደግሞ #ራሱን #አይዘርፍም። ፈጽሞ።
አውቃለሁ ፋኖ እንዲጠላ እንዲገለል ፆም ፍቺ ላይ ጦርነት ተከፍቶ በፆም የደከመ ሕዝብ ሬሳ ታቀፍ ሲባል። ትራጀዲውን ማን ተዋናይ አክተር ሆኖ እንደሚከውን አውቃለሁ።
"ልብ ይስጠወት"
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉትሻ 15/06/024

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።