ድብድቡ መቼ እንዴት ይቁም።

 

ድብድቡ መቼ እንዴት ይቁም።
"አድርገህኛል እና አመሰግንኃለሁ።"
 May be an image of 1 person, smiling and buttonMay be an image of 1 person and smilingMay be an image of 1 person
May be an image of 1 personMay be an image of 1 person, smiling, eyeglasses and jewelry
ክወና ነው። ለምን ማፍራት ተስኖን #ፈሰስን? #ቀዳዳችን ስለምን በረከተ? #ቦክሱስ መቼ ይቁም? #ክፋነት መቼ ይቀበር? በራስ ላይ መዝመት ከተቻለ ሁለንም ብትክ ጉዳዮች ቀብረን ወደ ቀደመው ዊዝደማችን ጉዞ መጀመር እንችላለን። ዊዝደማችን ለተፈጥሯችን ዕውቅና ሰጥቶ በሱ ውስጥ ለመኖር መፍቀድ ነው። ወጪ አይጠይቅም። ትልም አይጠይቅም። ከራስ ጋር መታረቅ ብቻ ቁልፋን የመፍትሄ ትልምን ያስረክበናል።
ስህተት ውስጥ ትናንትም፤ ዛሬም ብቻ ሳይሆን ስህተትን ለማስቀጠል ትጋታችን ሊገታ ይገባዋል። ሁሉም በግድፈት ተነክሮ ነው የኖረው። በሌላ በኩል ደግሞ ሁሉም አለኝ የሚለው አቅም አለው። ለድክመቱ መሻሪያው የራስ ዳኝነት ነው። ለአቅሙ ደግሞ በውጭጭ አቅም ቅንነትን መግቦ አገርን፤ አደራን፤ ትውልድን ማዳን ይገባል።
የታሠሩ #እስረኞች ሁሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሊፈቱ ይገባል። #ተኩስ #አቁም ሁሉም ሊያውጅ ይገባል። አቅምን ንቆ ከመነሳት ለአቅሙ ዕውቅና ሰጥቶ #በልኩ #ትኩረት ሊሰጥ ይገባል። #እላፊ መሄድም አይገባም። ስድብ፤ ማዋረድ፤ ማቃለል ለምን???
መውደቃችን ከውስጥ መቀበል አለብን። በመውደቃችን ልናፍር ይገባል። የሚሠሩ መልካም ነገሮችንም ዕውቅና መስጠት ይገባል። ግን ምንም ዓይነት ሥልጣኔ ከሰው ልጅ ህይወት፤ የመኖር ዋስትና በላይ ሊታይ አይገባም። ፈጽሞ።
በጣም ስጋት አለኝ። የአማራን ህዝብ #አቅሎ የማዬት ፖለቲካ። በፍጥነት ሊታረም ይገባል። የሰይጣን ጆሮ ይደፈንና " የአማራ ህዝብ እገነጠላለሁ" ካለ ኢትዮጵያ #ባላ የሌለው ቤት ትሆናለች። የመካከለኛው ምስራቅ ፖለቲካም ሙሉ በሙሉ ይቀዬራል። ብዙ ያልነገርኳችሁ ተሳትፎ አለኝ። ብቻዬን የሠራሁት። ቤተሰቦቼ ፖለቲካ ስለማይሹ ደጀ ሰላማቸው ላይ ነው ያሉት። ግን እኔ በሰለጠንኩበት በሠራሁበት መስክም እተጋለሁ። አንድ ዕጣ ነፍሴን ይህን ያክል ከሠራሁ ሁሉ አማራ አቅሙን ቢያማክል ተመን የለሽ በረከት ይሆናል።
ምንም ሳያግደኝ ብዙ ነገር ሠርቻለሁ። የአማራ ህዝብ #ቅን ነው። ቅንነቱ ደግሞ የሰጠው #ጥንካሬ አለው። #አትካዱት#አታደብዝዙት። እኔ ኑሬበት ስላዬሁት ነው። እና የአማራ ህዝብ እናቴ፤ አገሬ፤ ወገኔ ብሎ ላደረገው ተጋድሎ፦ በገፍ ላበረከተው አስተዋፆ #ዕውቅና መስጠት ይገባል። ለተበደለውም #ይቅርታ ሊጠዬቅ #ካሳ ሊሰጠው ይገባል። ልጆቹ ተሰደንም ፍዳ ስለምናይ። ይህ ደግሞ እርግማን እንጂ በረከት አላመጣም፤ አያመጣም። የአማራ ህዝብ ሥልጣኔ ሁለገብ ነው። ግሎባልም ነው። ማሸነፍ አይቻልም። ከአቅሙ ጋር #ተግባብቶ፤ ተስማምቶ ለድርሻው የድርሻውን ፈቅዶ ሰጥቶ አገር - አደራን - ትውልድን ማስቀጠል ይገባል።
ሳይለንት ማጆሪቲ ላይ #ውህድ ማንነት እንደሚያል ይሰማኛል። አማራ በጋብቻ፤ በአበልጅነት፤ በጉርብትና፤ በሰንበቴው በማህበሩ ተዋህዷል። ሳይለንት ማጆሪቲው በብሄራዊ ሰንደቁ ጥሪም #ሀሌታ የሚሆነው ሚስጢሩ ይህ ነው። ይህ ብልጠትን ሳይሆን #ብልህነትን ይጠይቃል። ብልህ እንሁን።
በተለይ ገዢው "ብልጽግና" የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ መንግሥት የሞገድ ጋዜጣ ትወና ማቆም ይኖርበታል። ኢትዮጵያን አፍርሶ ለመሥራት የአማራ ፈቃድ ተጥሶ አይሆንም። ሥልጣኑ የተገኜው ሙሉ 45 ድምጽ ከአማራ ነበር። የሎቢው ተከድኖ። ህወሃት + ሻብያ መንበረ ሥልጣኑን የተረከቡት በአማራ ህዝብ ድጋፍ ነው። የህወሃት እና "የብልጽግና" ጦርነት በህወሃት መሸነፍ የተጠናቀቀው የአማራ ሙሉ አቅም ተይዞ ነው። በኢትዮጵያዊነት ላይ ጥልቅነት ያላቸው አፋር፤ ጉራጌ፤ አማሮ ወዘተ ……… ሚስጥራቸውን ስለማይረግጡ ጠንካሮች ናቸው።
#እንታረም። ፈቅደን።
ፈንታሌ የሚባል ሚዲያ አለ። ያልሰማናቸውን አመክንዮ ሹክ የሚለን። የአቶ ጌታቸው ረዳ ጉዞ በአሜሪካ እና አቀባበሉ የዳጎሰ መጸሐፍ ይወጣዋል። ሰሞኑን ስለ ግንቦት 7 አንድ ቃለ ምልልስ አቅርቧል። ሴቶችን መሞገት አልፈቅደውም። ሁለት ፍሬ ስለሆን። ግን ብንታረምስ እንዲህ ካለው ነገር ለማለት ነው። የግንቦት 7 ሊቃናት ኢትዮጵያ አሉ። #ህይወታቸው #አያሳስብም???? ሌላስ ግንቦት 7 አስገድዶ ነበር ስብሰባ ፈንድራይዚንግ የሚያደርገውን??? #እእ። እኔ ተገድጄ ስብሰባ ተገኝቼ አላውቅም። ለራሴ ሚዲያ ለዘገባ ፈቅጄ ወድጄ ነው የምሄደው። ፈንድ ራይዚንጉም በይፋ ነው ሲካሄድ ያዬሁት።
ጨርቁን ብንነካው እንድናለን የሚሉ ሚሊዮን ደጋፊም፦ አባልም የነበረው ተስፋዊ የሚሊዮን ድምጽ ድርጅት ነበር። ሊቃናት በሙሉ መዳፋ ላይም ነበሩለት። በቅንጅት የተበተነውን ሃሳብ አሰባስቦ፦ አደራጅቶ እና አቀናጅቶም መርቷል። ይህን አይቻለሁ። ለዘመኑ ጥሪውን በስደት ከውኗል። ስህተቱን ሞጋቹ ነበርኩ። ፕሮፖጋንዲስት አያስፈልገኝም። እንዲህ ነበር እንዲያ እንዳትሉኝ። አውቀዋለሁ። ድክመቱ በሁሉም የፖለቲካ ድርጅት የሚታይ ነው። ለምን? የግራ ፖለቲካ ባህል ስለሆነ።
እና ፈንታሌ ሚዲያ ላይ የሰማሁት ዛሬ ኢትዮጵያ ላለችበት ሁነት ይህ ጠቃሚ ነው ወይ ነው ጉዳዬ??? #አይጠቅመንም። ቢጠቅም የአቶ ጌታቸው እረዳ አቀባበል እና የአማራ ሁኔታ ብዙ በጣም ብዙ የሚያጽፍ፤ የሚያስሞግት ነበር። አላደረኩትም። የአለንን፤ እራሴ በእጄ ያበጃጀሁትን፤ የደከምኩበትን #መድፋት ስላላስፈለገኝ። ከድኜ ነው ያቀረብኩት።
በፈንታሌ ሚዲያ የቀረበችው እህታለም ክብርቷ አዲስ ነገር አልነገረችንም። ውጭ ሆነን ስንከታተል ለነበረው። የሁለት አንጋፋ #መሪወቹ ኤርትራ መገኜታቸው ብቻ ነው አዲሱ። ለእሱ ደግሞ ሁለት ሰከንድ ዘገባ ይበቃዋል። ሌላው አባይ ሚዲያ ነው። እምሳሳለት ወንድሜ ነው። ዴንማርክ በኢትዮጵያ ጉዳይ በ2008 እኤአ አግኝቼው ሳዬው ሚኬኤልን ነው የመሰለኝ። ትጋቱ፦ እርጋታው። የፀጋዬ ድህረ ገጽን ሊንክ ያደረገው ብቸኛው ድህረ ገጽም አባይ ሚዲያ ነበር። ኢትዮጵያ ነፍሱ ናት። እና አባይ ሚዲያ ሥሙ ሲነሳ ሰቀጠጠኝ። ሌላው ልጅ መሳይ ነው። ብዙ ደክሟል። እሱ ሳይኖር ጭር ይላል አድባሩ። ፀጋውን ራሱ በሚጽፋቸው መነባንቦች አያለሁ፦ ጥበብ ባትፈራ??? ካለሙያውም አይገባም ባለሙያ ይጠይቃል። እምሞግተው ግን እማከብረው ፀሐፊም ነው። ትናንት ባላተረፍንበት መዳከር አይገባም። ቢያንስ ጥበብን እናትርፍ። ጋዜጠኝነትን እናትርፍ።
ማዳን ብንማር ምን አለ? ድብድቡ ቢቆም። ቂም ቢሻር። ምህረት ይቅርታ ቢነግሥ ምን አለ። ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ይታወቃሉ። ለሳቸው የሚሰጥ መረጃ ምን ሊያመጣ እንደሚችል መገመት ይቻላል። ለሳቸውም ባይጠቅም። ከሁሉ የኢትዮጵያ እናቶች እንባ ለምን አያሳስበንም። " ሁሉም እናት አለው።" አሳራቸውን ያዩት የአቶ ልደቱ አያሌው ክብርት እናት የተናገሩት ነው። አባይ ሚዲያ ኢትዮጵያ ነው ያለው፤ የግንቦት ሰባት አናትም።
የምንሰጣቸው መረጃወች እናቶችን እንዳይጎዳ በተለይ እናቶች ሴቶች የሚዲያ ሰወች ብንጠነቀቅ። መሪ ዳንቴል አይደለም። እና መሪወችን መገበር ፈቅዶም የሚገባ አይመስለኝም። መከፋት በግል ሊኖር ይችላል። ግን እናትም፦ እናት አገርም ይታሰቡ እንደማለት።
እርገት።
በጨቀጨቅ መዳከር ይቁም። ከዚህ በላይ ምን ይኮን? ቦክሱም ይገታ። ምን አተረፍንበት። የዓለሙ ሎሬት የሰላም አባት ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድም ብፁዑ አባታችን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ዬሰጡትን " ኧረ ልብ ይስጥህ " እኔም እደግመዋለሁ። ኢትዮጵያ የከበደችን ለሁላችን ነው። ለሁላችንም አምላካችን ልብ ይስጠን። አሜን። የይቅርታም ድፍረት ይስጠን። አሜን።
ውቦቼ ውዶቼ በዘርፋ የጀመርኩት ዘለግ ባለው ዕይታዬ እርገት ይሁን። ኑሩልኝ።
ደህና ዋሉ። ቸር ሁኑልኝ። አሜን። ትህትናችሁ ቁሞ እያስተማረኝ ነው። ኑሩልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
14/06/024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።