"WORLDFIRST"
"WORLDFIRST"
የጨዋታ ሰዓት እረፍት እና ተጨማሪ ደቂቃወች ታክለው። 21.02 - 22.56 ቀን 14.06.2024
ዛሬ በጀርመኑ ሙኒክ አሪና ስኮትሾቹ እና ጀርመኖች ከምድብ #Aየ2024 የእግር ኳስ ውድድር የመክፈቻ ግጥሚያቸውን አካሄዱ። ቀዝቀዝ ብሎ የጀመረው ጨዋታ በጀርመኖች 4 ጎል በአንድ ቅጣት ምት 5 ለአንድ በሆነ ውጤት ጨዋታው ተጠናቋል። ጀርመኖች እግር ኳስን ከብሄራዊነት ጋር አዋህደው ስለሚዩት ልዩ የህሊና አቅም አይባቸዋለሁ።
ዛሬ ቀዝቀዝ ብሎ በተጀመረው እግር ኳስ ውድድር ስቲዲዮሙም አልሞላም ነበር። የባዬር ሙንሽንን የፍፃሜ ውድድር ያህል እንኳን ደምቆ አላዬሁትም። የሆነ ሆኖ የጀርመኖች ቀደምት ጎል ጠባቂ አማኑኤል ኖዬር፤ ቶኒ ሙለር ከነባሮቹ ተጫወቾች አይቻለሁ። አብዛኞቹግን አዲስ እና ወጣቶች ናቸው። አሰልጣኙ እራሱ ወጣት ናቸው አዲስም።
ጀርመኖች የመጀመሪያውን የጨዋት ክፍለ ጊዜ ሦስት ነጥብ አስቆጥረው ነበር የተጠናቀቀው። የቅጣት ምቱን ማግኜታቸው ብቻ ሳይሆን ስኮትሾች አንድ ተጨዋች በቀይ ካርድ ተቀጥቷል። ሁለተኛው ክፍለጊዜ አንድ ተጫወቻቸውን ስኮትሾች ሚስ ቢያደርጉም ለአንድ ጎል በቅተዋል።
ደጋፊወቻቸውም ትንሽ ተነቃቅተው ነበር በሁለተኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ጀርመኖች ሁለት ግብ በማስቆጠር 5 ለ 1በሆነ ውጤት ጨዋታው ተጠናቋል።
ጀርመኖች መጀመሪያ ዕድል ከቀናቸው ይጠነክራሉ። መጀመሪያ ጎል ከተቆጠረባቸው ግን ይዝላሉ። እንደ እረጅም ጊዜ ተከታታይ በዚህ ዙሪያ አሰልጣኞቻቸው ቢሠሩ መልካም ይመስለኛል። የመጀመሪያ ጎል ማስቆጠር ጥረት ማጠናከር ወይንም ጎል ከተቆጠረባቸው መጀመሪያ ላይ ሳይዝሉ ጠንክረው መቀጠል።
ዕውነት ለመናገር ያ ደማቁ የአውሮፓ እግር ኳስ ጨዋታ አይመስልም። የበረደው ነበር። ዓለም ትቅደም መፈክር ከሜዳው ያዬሁት ነው። ያድርገው ብያለሁኝ። ነገ ሲዊዝሻ ከኡንጋር ጋር አላት ይቅናት። አሜን።
ድንቡልቡል ብዙም አልተሰለቀችም። እናም ደስታዋ ምጥን ነው።
ሥርጉትሻ 14/06/2024 የነገ ሰው ይበለን አምላካችን። አሜን።
አፈሙዝ ጩኽት የማይሰማባት ዓለም ለቀጣዩ ትውልድ ማስረከብ እንደምን መታደል ነበር።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ