የሞዴል፤ ሞድሬተር ዳኛ እና የአዲስ ሃሳብ አፍላቂ የልዕልት ዬሃይዲ ዓለም እና ለአዲስ ትውልድ ግንባታ ያላት ልቅና።

 የሞዴል፤ ሞድሬተር ዳኛ እና የአዲስ ሃሳብ አፍላቂ የልዕልት ዬሃይዲ ዓለም እና ለአዲስ ትውልድ ግንባታ ያላት ልቅና።

" የሰው ልብ መንገድ ያዘጋጃል፦
እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።"
(ምሳሌ ፲፮ ቁ ፱)

May be an image of 3 peopleMay be an image of 1 person, blonde hair and textMay be an image of 8 people and overcoatMay be an image of 8 people and overcoatMay be an image of 8 people, television and text
ጤና ይስጥልኝ የማከብራችሁ የአገሬ ልጆች እንዴት አደራችሁ? ደህና ናችሁ ወይ። ትናንት 19ኛ ዓመቱን ያከበረው የጀርመን ምርጥ ሞዴሎች ውድድር የመጨረሻ ቀን ነበር። ብዙ የተማርኩበት፤ ሁለቱ መፃህፍቶቼ የተፃፋበት መሠረታዊ የመነሻ ሃሳብ ትውልድን ከዘመኑ ሥልጣኔ ጋር፤ መክሊቱ፤ ጥሪው ሜሴጁ ሳያልፍበት በጥዋቱ እንዴት ይገነባል የሚል ፍለጋዬ ዓለም ዓቀፍ የመክሊት ውድድሮችን እንድከታተል አስችሎኛል።

1) 6ኛ መጸሐፌ "የተስፋ በር" ልጆች እና ወላጆችን፤ ልጆቻችን እና ማህበረሰቡ፤ ልጆች እና ግሎባላይዜሽን፤ ልጆች እና መምህራን የመነሻ ሃሳብ የተካተተበት ነው።

2) 7ኛ መጽሐፌ "ርግብ በር" ማህበረሰብ እና ትዳር በትውልድ ግንባታ ላይ ምን ድርሻ አላቸው? ድርሻቸውን እንዲወጡ ዕድሎች እንዴት ማኔጅ ሊደረጉ ይገባል የሚል የመነሻ ሃሳብ ነው።

ሁለቱም ጀርመን አገር በታለንት፤ በሞድ፤ በሙዚቃ ውድድር ከማያቸው ክፍተቶች በአገሬ በኢትዮጵያ በማህበረሰብ አደራጅነቴ አያቸው በነበሩ ጥንካሬ እና ድክመቶች፤ እኔ አባቴ አበይ በጥዋቱ ወደ ጥበብ ያስገባኝ ሁኔታ፤ የእናቴ የእብዬ ክትትል በሞድ ዙሪያ ልምዴን ያጋራሁበትም ነው። ሌላው ቁጥቧ ሲዊዝስ በዚህ ዘርፍ ያላትን ተሳትፎ አክያበታለሁ።

ብዙውን የተስፋ ጎዳና ዳሜጅ በሚያደርገው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ህሊናን ላለማከራዬት በወሰድኩት እርምጃ ስቶር ያሞቃሉ። እና ለእኔ የኦስትራሽ በስሱ፤ የጀርመን በጉልሁ፤ የሲዊዝ በመጠኑ በዘርፋ የሚካሄዱ ውድድሮች አቅጄ የምከታተላቸው ናቸው። በገጠር በገበሬ መንደር፤ በከተማ በራሴ አስተዳደግ፤ በስደት በምኖርበት ያገኜኋቸው ተመክሮወች ተማክለው ነበር የተፃፋት።

በተለይ የጀርመን የሙዚቃ ኮከብ እና የጀርመን የሞድ ውድድር ለአራት ወር የሚዘልቅ የቲም ወርክ ስለሆነ ጥልቅ ግንዛቤ ይሰጣል። ኢትዮጵያም ሞዴል ጭምቷ መልካም እምታካሂደውን የአይዶል ውድድሮችን እምከታተለው ለዚህው ፐርፐዝ ነው።

እግርኳስም እንደ ሥነ ፁሁፍ ስለምወድ እከታተላለሁ።

የብቁዋ ጀግና ሴት ተጋድሎ ብዙ አፍርቷል። የአሜሪካ የታለንት ውድድርም ዳኛ ናት። ፈጠራዋ እጅግ ይደንቀኛል። ኮረናን እንደምን እንደታገለችው ሁሉ ይደንቀኛል።
የዘንድሮው ልዩ ነበር። ልዑል ነበረበት። መንትዮች ነበሩበት። ከሲሪያ ተሰዳ ጀርመን ያደገች ወጣት ነበረችበት። በማደጎ ከአፍሪካ የመጡ ልጆች ነበሩበት። ከህንድ ተባት ለመጀመሪያ ጊዜ ተወዳድሮበታል። ለመጀመሪያ ጊዜ ወጣት ወንዶችም የተወዳደሩበት ነው። ሌላው የጋብቻ ዋዜማ በተወዳዳሪወች ላይም ዬታዬበት ነው።

ሌላው ተወዳጁ የጀርመን የእግር ኳስ ህሊና ጭምቱ፤ የተረጋጋው ዘባስትያንም በዳኝነት ፋይናል ላይ ተገኝቷል። አሁን ወቅቱ የአውሮፓ የእግር ኳስ ጨዋታ ስለሆነ ኳስ ጨዋታ እና ሞድንም ትናንት አሳዬችን ጀግናዋ ወሮ ሃይዲ።

የገረመኝ ደማቸው የኛን ሃበሻ የሚመስሉ ሦስት ተወዳዳሪወችም ነበሩ። ክድጃን ጨምሮ። ድንቁ ነገር ባክ ስቴጅም ጠይም ዕንቁወች በጋራ ፕሮግራሙን መርተዋል። ዓለም ዓቀፍ ታዋቂ ሙዚቀኞች፤ ፎቶግራፈሮች፤ ተዋናዮች፤ የሞድ ፕሮዳክሽን ማናጀሮችም ተገኝተዋል።

ድንቅ የሚለኝ የመጀመሪያ ዕለት ሲመጡ እና ፋይናል የደረሱት ፈጽሞ አይገናኝም። አዲስ ሰው ታረጋቸዋለች። ትፈጥራቸዋለች። የእኔ እምሳሳላት ሞዴል ፋብያን እጅግ ቁጥብ ነበረች። ከአፍሪካ በማደጎ መጥታ ያደገች ናት።ፋይናል አደረሰቻት። የኤሊኮፍተር በረራ እና ሞድ፤ የመጨረሻ የከበር የሞድ ውድድር ላይ ብቁ ነበረች። መንትዮችን፤ ልዑሉ፤ ፋብያን በፍፁም ልቧ ትወዳቸውም ነበር።

ሦስቱ ደማቸው እኛን የሚመስሉት ሥነ ምግባራቸው፤ ሦሻል ልምዳቸው የሚደንቅ ነበር። ወንዱ ተሸላሚ ሆኗል። ሴቷ ባክ እስቴጅ ከልዑል ማርቢን ጋር የፕሮግራም መሪ። ጀሚ ሲገባ ያማትብ ነበር። እና አንተ ጠረንህ ከወዴት እልም ነበር። ሌላዋ አሸናፊ ሊም እንዲሁ ምግባሯ ልዩ ነበር። በውጤቱ እኔ ደስ ብሎኛል። ሽልማቱም ዝቀሽ ነው።

ሽልማቱ ብቻ ሳይሆን ለወጣቶች ያለው የተከፈተ እድል ይህ ነው አይባልም። ሃበሻ የሚመስለኝ አሸናፊው ሁሉንም ካስቲንግ ጠቅልሎታል ማለት ይቻላል። ቆፍጣና ብቻ ሳይሆን ለደራሽ አሳይሜንት የሚሰጠው ምላሽ አሳዳጊውን ይባርከው ያሰኛል።

የሚዲያ አቅማቸው ይፈተናል። ከሞድ ውድድር በፊት የነበራቸው ታሪክ ተጎርጉሮ ይፈተኑበታል። ከሆሊውድ ከፍ ያሉ ተዋናዮች መጥተው በደራሽ እስክርቢት ይሞገታሉ። ከስፔን እስከ ሎሳንጅለስ በሚኖራቸው ቆይታ ቻሌንጁም፤ ድሎቱም፤ ሙግቱም ቡፌ ነው።

ከሁሉ የምደነቅበት እናታዊ ፀጋዋ ነው የልዕልት ሃይዲ። ትሳሳላቸዋለች። ስጦታው በዓይነት ነው። ጠቡ ስታይሊንግ የፀጉር ቆረጣው ላይ ነው። ዘንድሮ የውሃ ውስጥ ፎቶ ላይም ስትሳተፍ አይቻታለሁ። ፕሮግራሙ ከ2,15 ጀምሮ ዘወትር ማታ ሃሙስ ሃሙስ ይካሄዳል። በአውሮፓ የእግር ኳስ ውድድር ምክንያት ማክሰኞም ውድድር ነበር።

ዘንድሮ የወጣት ወንዶች መጨመረ ቲሙን አጨምቶታል። ብዙ ዓይነት ፈተና አይ ነበር። የኢንተግሬሽን ችግር። ዘንድሮ በሰላም፤ በፍቅር፤ በመተሳሰብ መላዕካዊ መንፈስ ነው የተከወነው። አንድ ኮርስ ላይ ወንዶች በዛ ካሉ ቲሙ ሰላም ይሆናል። ዘንድሮም ይህን አይቻለሁ። የተረጋጋ ጊዜ ነበር።

በዬሳምንቱ ዳኞች ይለያያሉ። እንደሚያቀርቡት የሞድ ዓይነት፤ እንደ ሞትቢሽናቸው እንደ ሙያቸው። ንግሥት ሃይዲ የመሃል ዳኛ ናት። የልጆቿ ኑሮ ሉክሶስ ነው። ቲሙ ሰፊ ነው። ለትውልድ የሠራችው ተግባር ዕፁብ ነው። ከሁሉ ግርም የሚለኝ ለእኛ ቀለም ያላት ክብር፤ የምትሰጠው ዕውቅና እና ያላት ፍቅር ነው።

ትናንት ልክ 20.15 ተጀምሮ 23.23 ተፈጠመ። ብሩኳ ልዕልት ሃይዲ ዓራት ዓይናማ የምትባል ትጉህ ታታሪ ልዑቅ ጀግና ሴት ናት ለእኔ። የትውልድም ምሳሌ። ለስደተኞችም አዲስ ዕድል።

ድንቡልቡልም እዬመጣች ነው። ስለ እሷም በስሱ ይዘገባል።

ታሪኩን እለጥፋለሁ ልታዩት ትችላላችሁ። ህይወት ሁልጊዜ ውጥን ናት። ትሰፋ ትንሰራፋ ዘንድም ጥሪያዋን ልናደምጥ ይገባል። ጊዜን ማኔጅ አድርጎ ለእስትንፋስ ቀጣይነት ግሎባሉን በጎ ነገርም ማድመጥ ይገባል። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። ኑሩልኝ። አሜን።

ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
14/06/024

ፎቶ የታሪክ ልዑል ነው።
ፎቶ የሥልጣኔ አንባር ነው።
ፎቶ እኔን ገላጭ ነው።
ሞድ የደስታ ምንጭ ነው።

ሊንክ።

https://www.youtube.com/watch?v=1WzGS0H1H54
• Jermaine ist der Gewinner von Germany's Next Topmodel 2024 | GNTM 2024 ProSieben
https://www.youtube.com/watch?v=ZC3GyOMYJuU
• Lea ist die Gewinnerin von Germany's Next Topmodel 2024 | GNTM 2024 ProSieben
https://de.wikipedia.org/wiki/Germany%E2%80%99s_Next_Topmodel

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።