ፕ/ ዶር. ፍቅሬ ቶሎሳ።
ብሩክ ቀን – ሥርጉተ ሥላሴ „ … እኔ ግን እግዚአብሄርን እለምን ነበር፥ ነገሬንም ወደ እግዚአብሄር አቀርብ ነበር። ዬማይመረመረውን ታላቅ ነገርና የማይቋረጠውን ተአምራት ያደርጋል። …“ ( መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፭ ከቁጥር ፰ እስከ ፱ ) ይድረስ ለኢትዮጲያኒዝም አባት እና የአብሮነት ሐዋርያ ለሆኑት ሊቀ – ሊቃውንት ፕሮፌሰር ዶር . ፍቅሬ ቶለሳ – ባሉበት። ሊቀ – ሊቃውንት ፕሮፌሰር ዶር . ፍቅሬ ቶለሳ እንደምን ሰነበቱልን ፤ እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። „ የኦሮሞና የአማራ እውነተኛ የዘር ምንጭ “ በዚህ በአዲሱ መጸሐፍዎት ዙሪያ ከኢትዮዽያ ኃብታት ከሆኑት ሁለት ሊቀ – ሊቃናት ጋር ያደረጉትን ክርክር ግራ ቀኙን – ታደሜበታለሁ። ከሥር ዬሚታከሉ ዬአንባብያንን አስተያዬትንም በማከል ነበር – ዕድምታዬ። መጸሐፋን ባነበው ዬበለጠ ሊረዳኝ ይችል ዬነበረው በመጽሐፋ ውስጠት ዬግሌን ዕይታ በመንፈስ ሊያጎለብትልኝ ቢችልም፤ አደባባይ ወጥቼ ዬሃያሳን ሊቃናትን ዬሙያ ድርሻ መጋፋት ተገቢ አለመሆኑን ስለማምንበት ፤ እምለው አይኖረኝም ነበር። ስለዚህም ዛሬ ልጽፍ ላነሳሳኝ ጭብጥ „ የኦሮሞና የአማራ እውነተኛ የዘር ምንጭ “ መጸሐፍ አለማንበቤ ዬሚያጎድለውም ሆነ ዬሚሞላው ምንም አይነት አመክንዮ አይኖረውም። ጠብታ። ውስጤን ለውስጤ