ልጥፎች

ኧረ።

  ኧረ። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" እንዴት ሰነበታችሁ? እባካችሁ ለፖለቲካ መሪወች፤ ለተፅዕኖ ፈጣሪወች፦ ብላችሁ ማህበራዊ ኑሯችሁን አታውኩ። የውስጥ ሰላማችሁንም አትቀናቀኑ። # አናውቃቸውም።  መደገፍ መብት ነው፤ መሞገትም። ግን እነሱን አምናችሁ እና ተማምናችሁ ከጽኑ ወዳጃችሁ ጋር አትለያዩ። ትናንት ከብክበን መስክረንም ሌት ተቀን ተግተን መንበር ላይ ያወጣናቸው ዛሬ ኢትዮጵያን እስከመቀናቀን ደርሰዋል።  ማህፀንን እንደ ዱባ የሚቀረድድ መራር ሸክም። የሞግትናቸውንም // ከደገፍናቸው ጋር ስናነፃጽረው ግብረ መልሱ ከራሳችን ውጪ በፍፁም ልባችን ማንንም ማመን ምን ያህል ውስጥን እንደሚያቆስል እያዬሁ ነው።  ኧረ! ለሁላችን አምላካችን // አላሃችን ልብ ይስጠን። አሜን። ውዶቻችንም በማያዘልቅ አመክንዮ ብለን አንጣ። በተለይ የውስጥ ሰላማችን ለሌላ ሰብዕ ብለን አንጣ። #አንተዋወቅም ። እኛ ላዩን እነሱ ውስጡ ለውስጥ ሲጓጓዙ ነው የኖሩት።  ሥርጉትሻ024/07/02

ትዝብት።

  ትዝብት ።  "የቤትህ ቅናት በላኝ ።" አንድ ግንኙነት ዲስፒሊን ሊኖረው ይገባል። አንድ ተቋምም ዲስፕሊን ሊኖረው ይገባል። እንኳንስ የፖለቲካ ድርጅት። እኔ ዛሬ ጓዶቼን ባገኝ፤ ለዓይነ ሥጋ ቢያበቃኝ እንደምን ሐሤት ባገኜሁ። ቃል ኪዳኑ ሰው ሠራሽ አይደለም እና። በወል፤ በጋራ የተከወኑ ተግባራት ለጎርፍ ሲሸለሙ ስመለከት ገረመኝ። ታማኝነት፤ ኪዳን፤ ውል፤ ቃል በኢትዮጵያ የፖለቲካ፤ የማህበራዊ ኑሮ መና ወና ሆኑ።  በዚህ ውስጥ መሪነትን እሰቡት። ልሙጥ አልሆነባችሁም። የሚቀር ነገር የለም። የተዋጠ ቅቤ አይቀርም። ከምንጊዜም በላይ ክውን ብዬ በራሴ ራዕይ እና ግብ መትጋቴ የእኔ ሳይሆን የላይኛው እርዳታ መሆኑን ተገነዘብኩኝ። ተከርክሞ ክውን ብሎ ገድሞ መኖር በቢሊዮን ዶላር የማይገኝ ሥጦታ ሆኖ አገኜሁት።  ሰው ከሰው ጋር ሲኖር፤ ሲሰራ፤ ሲወዳጅ እኮ ብዙ በጣም ብዙ ነገር ሊታወቅ ይችላል። ያን ጊዜ ጠብቆ የጥቃት ሚሳኤል ማድረግ ነውር ነው። #መጠበቅ //መጠበቅ እንደምን ያቅት። "አቤቱ ለአንደቤቴ ጠባቂ አዘጋጅ።" አሁን ሚዲያ ላይ የሚገኝ ህዝብ እኮ ገብያ ማለት ነው። ይፈታል። እና የተቋምን ቃልኪዳን ማፍሰስ? ሥርጉ2024/07/02

ደራሲ ባለቅኔና ዲፕሎማቱ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ

ምስል
  ደራሲ ባለቅኔና ዲፕሎማቱ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ     በኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ታሪክ ታላቅና ግዙፍ አስተዋጽኦ ያላቸው ደራሲ፤ታሪክ አዋቂ፤የታወቁ ዲፕሎማት፤በቤተ ክህነት ትምህርትና በቋንቋ የተካኑ፤ ባለቅኔ፤ገጣሚ፤የዘመናቸውን ዕውቀት የቀሰሙ ምሁር፤ በአኗኗራቸው በምሳሌነት የሚታዩና ሠርተው የማይደክሙ ኢትዮጵያዊ ናቸው ፡፡እኒህ ሊቅ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ ይባላሉ፡፡ ከአባታቸው ከአቶ ወልደ ሥላሴና ከእናታቸው ወይዘሮ ወለተ ማርያም ዜና የተወለዱት ግንቦት 1 ቀን 1871 ዓ ም በቀድሞ አጠራሩ በመርሐ ቤቴ አውራጃ በታች ቤት ወረዳ ረመሸት ቀበሌ ደን አቦ ገዳም በተባለ ሥፍራ ሲሆን ያረፉት ደግሞ መስከረም 9 ቀን 1931 ዓ ም እንግሊዝ አገር ባዝ በተባለው ቦታ በስደት ላይ እያሉ ነው:: ብላቴን ጌታ ኅሩይ ለቤተ ሰቦቻቸው የመጀመሪያ ልጅ ሲሆኑ አባትና እናታቸው ከእርሳቸው ቀጥሎ በተከታታይ ሁለት ሴት ልጆችን ወልደዋል። እንጦጦ ራጉኤል ደብር መጥተው የመጻሕፍትን ትርጓሜ በዘመኑ ከነበሩት የደብሩ ሊቃውንት ዘንድ ተምረዋል። ብላቴን ጌታ ኅሩይ በትዳር ሕይወታቸውም መልካም አርዓያ ስለነበሩ ከባለቤታቸው ወይዘሮ ሐመረ እሸቴ ስድስት ልጆን ወልደዋል፡፡በርካታ የልጅ ልጆችንም አፍርተዋል፡፡ቤተሰባቸውንም በእግዚአብሔር ሕግ መሠረት በፍቅር ይመሩና ያስተዳድሩ ነበር፡፡በድርሰት ረገድ ከ21 በላይ የተደነቁ መጻሕፍትን ደርሰዋል፡፡ሥራዎቻቸው ሁሉ ትሕትናን፤ትክክለኛነትን፤ምግባረ ሠናይነትንና ሞራልን ከፍ አድርገው የሚያሳዩ ናቸው፡፡ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ከጻፉዋቸው መጻሕፍት ውስጥ ኢትዮጵያና መተማ የዓፄ ዮሐንስ ታሪክ ባጭሩ፤ ወዳጄ ልቤ ፤ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ፤ የልዕልት ወይዘሮ መነን መንገድ በኢሩሳሌምና በምስር፤ መጽሐፈ ቅኔ፤ ዋዜማ፤ በኢትዮጵ

ሰውነት ለኢትዮጵያ ተፈጥሯዋ እንጂ ባዕዷ አይደለም።

ምስል
  ሰውነት ለኢትዮጵያ ተፈጥሯዋ እንጂ ባዕዷ አይደለም።     "የቤትህ ቅናት በላኝ።" የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከቅንነት ጋር ተዋውቆ አያውቅም።   የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሰውኛም አይደለም። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ተፈጥሯዊም አይደለም። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ጭካኔን መርሁ ያደረገ ነው። ስለዚህ ዘላቂ መፍትሄ ያስፈልጋል።    ኢትዮጵያ ተፈጥሯዋ #ተፈጥሯዊነት ነው። ተፈጥሯዊነቷ ትርታዋ ነው። ኢትዮጵያን እያመሳት ያለ ፖለቲካዋ ነው። እግዚአብሄር አምላክ ተፈጥሯዋን ዕውቅና የሚሰጥ፤ አክብሮ ሊያስከብራት የሚችል መንፈስ በምድሯ ይፍጠር። አሜን።    ለእሱ የሚሳነው የለም እና። ጀርመን አንደኛውንም፤ ሁለተኛውንም የዓለም ጦርነት ተሳትፎው የጎላ ነበር። ዛሬ ግን በምድሩም በሰማዩም ሥልጣኔ አንቱ ነው። ፈጣን እና ታታሪ ህዝቧ መሪ ስላገኜ።    ጀርመን ዛሬ ከኃያሉ ጎን ተሰልፋል። ይህ የሆነው #በመሪወች #አቅም እና #ትጋት ነው። ከልዩነት አንድነትን የመረጠው ጠንካራው ህዝቧ እና የመሪወቿ #ጥበብ ለሰው ተርፎ ማደር ችለዋል። በጀርመን #ጥበብ እና #ጥበበኛ #አይታሠርም ።    ብልህ ሰው ከአለበት ተፈልጎ ልምዱን፦ ተመክሮውን እንዲያጋራ ይደረጋል። #ይሸለማል ። ዕውቅና ያገኛል። ታታሪው ህዝቡ ጀርመን ይቅደም ነው። እግር ኳስ #ጨዋታ ብቻ አይምሰላችሁ።    ታላቅ ብሄራዊ የትውልድ መገንቢያ ልዩ መንፈስ ነው ለጀርመኖች። ትርታቸው ነው።በእያንዳንዱ የተጫዋቾቻቸው ንቅናቄ አትኩሮታቸው #የድርሳን ያህል ነው። ይጥራሉ ያሳካሉ። ብርታታቸው ከጥረታቸው ጋር የተዋህደ ነው።    በሁሉም ዘርፍ ንቁ እና ብቁ። ቀልጣፋ እና ስኬታማ። ሥልጡን እና መኖርን የተጠበቡ።    ኢትዮጵያ ደግ ህዝብ ሰጥቷታል። ሁሉን ቻይ። ግን ከዘመን ዘመን ለበቂ ህክምና፤ ለበቂ መጠለያ፤ ለበ