ልጥፎች

ጥሞና ውሰዱ። እባካችሁን።

ምስል
  የአማራ ሊቃናት/ ሊሂቃንም ጥሞና ውሰዱ። እባካችሁን። የአማራን ትውልድ ዕውቅና ባልተሰጠው የዜግነት ፖለቲካ ጥፍርፍር አድርጋችሁ ለማሰር አትጣደፋ። እናንተ ለአማራ ተስፋ ስቃዩ ናችሁ። እግዚአብሔር ይስጥልኝ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 30/05/2022 አማራን እባካችሁ ተውት!

ለሴቶች ታስሮ መፈታት አዲስ ምዕራፍ ነው።

  ለሴቶች ታስሮ መፈታት አዲስ ምዕራፍ ነው። ለሴት ልጅ እስር ከባዱ መርጉ የህይወት ፈተና ነው። መአዚ እንደታሠረች ሰማሁኝ። ድንግል ትርዳት። አሜን። በእሷ ዙሪያ ያልገባሁበት ቤት አልነበረም። የእናቷ ልጅ እንኳን የእኔን ያህል ትደክማለች ብዬ አላስብም። አንድ ወዳጄ እያወያዬኝ መጸሐፋን ፃፍሽላት ያለኝን አስታውሳለሁኝ። የሌላ አገር ዜጎችም በእሷ የተግባር ማሳ ምሰጣቸው ልዩ ነበር። ባለሥልጣኖችም ሲፈቷት አክብረው ነበር የፈቷት። እንደ እሷ ታሥሮ እጅግ ተከብሮ ከእስር የተለቀቀ አልነበረም። ያ የብዙ ድካም ውጤት ነበር። ብዙ ያስከፋኝ ሰወች ይቅርታ ሁሉ ጠይቀውኛል። እሷ ተሸልማ ማዬት ሁሉ ምኞቴ ነበር። በጣም በትጋት፣ በተከታታይነት 24 ሰዓት ደክሜያለሁኝ። የሚጎድልበት ማህበረሰብ። የሚጎድልበት ፕሮጀክትም ስለአለ። አንድ ብቻዋን አትታሰርም። ብዙ ተስፋወች ይታሰራሉ። ወጣት አትሁኝ ማለት አልችልም። ወንጀል ነውና። ወጣት ሁኜ እያለሁ ነበር ጭምትነቴ፣ ቁጥብነቴ ተመዝኖ ወጣቶችን አደራጅ እንድሆን ያስደረገኝ። ስለዚህ የእኔ ብቻ የወጣትነት ዘመኔ ብቻም ሳይሆን የወጣቶችን ሥነ - ልቦና አውቀዋለሁ እና። አደራጃቸው ነበርኩ እና። የሆነ ሆኖ ድካምን ዕውቅና፣ ድካምን አትኩሮት መስጠት ከአንድ ፕሮፌሽናል ፖለቲከኛ የሚጠበቅ ነው። ሲኖር ብዙ ይኮናል። ከታሰሩ ሁሉም ይከረቸማል። ብዙ ነገር ይጎድልበታል። ብዙ በሮች ባለቤት ያጣሉ። ቢያንስ ያነን ማሰብ ይገባል። ድንግል ትርዳት። እግዚአብሔርም ያስፈታት። አሜን። እግዚአብሔር ይስጥልኝ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 30/05/2022 ርትህን ከእዮር።

ድሮን ታቀደለት።

ምስል
  ይህ መኖር ተቀንቶበት ዲሽቃ ታዘዘበት፣ ድሮን ታቀደለት። "ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።" (ዕንባቆም ፲፯ ቁጥር ፫)     ከ12 ዓመት በላይ የታገልኩበት መርህ ዓለም ዓቀፍ ይሁኑ ታላላቅ መንግሥታት ሥሜን የሚያውቁት ለድምጽ አልባ የኢትዮጵያ እናቶች ስጮህ ነው። ዛሬ ኦነግ እንዲህ ለሚንፈራሰስበት ሥልጣን በጣም የከበረ ተጋድሎ አድርጌበታለሁኝ። ተደማጭም ነበርኩኝ። የማዝነው የአማራ እናቶች እኔም ሆንኩኝ ሌሎች እኔን መሰል በተለያዬ ትግል እና ስልት መስዋዕት የከፈሉ ወገኖቼ ጥረት ፈሶ መቅረቱ ነው። ፈሶ መቅረቱ ብቻ አይደለም እኔን የሚያሳዝነኝ የአማራ እናት መከራ መቀጠሉ። ተገለውም፣ ተፈናቅለውም፣ በጎጃቸው ጥሬ ቆርጥመው ለማደር የልጆቻቸውም፣ የእነሱም ሰላም ከመሳሪያም ከባድ መሳሪያ ተደግኖ በባዕታቸው አሳራቸውን ያያሉ። ፍዳቸውን ይከፍላሉ። የአማራ ሊሂቃን የተደመሩም ይሁን ያልተደመሩ ቢያንስ የአማራ እናቶችን ስቃይ ባያበራክቱ ጥሩ ነው። ይህ ሁሉ መከራ የምትሸከም የአማራ እናት ናት። የአማራ እናት ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ እናት የማትታይ፣ ዕውቅና የማይሰጣት፣ ሞት የታወጀባት፣ ሃዘንተኛ ትሆን ዘንድ በፖሊሲ የሚሰራበት ጉዳይ ነው። እና ልጆቿን የዜግነት ፖለቲካ እያላችሁ 30 ዓመት ሙሉ አስፈጃችሁ። ቢያንስ አሁን ተዋት። እባካችሁ ተዋት። የአውሬው ጭካኔ ብቻ ሳይሆን ተስፋዋን የምትነጥቁት እናንተ መሆናችሁንም ዕወቁት። የማን ልጅ ተገደለ? የማን ልጅ ታሠረ? የማን ልጅ ታገተ? የማን ልጅ ተጨፈጨፈ? የማን ልጅ ከትምህርት ውጪ ሆነ? የማን ልጅ ጫካ ለጫካ ማሰነ? እዮዋት እሙኃይን። ፍርድ ለራስ ነውና። #ህሊናችሁን ጠይቁ ስንት ተስፋ እንደምትቀዱ? ስንት ተስፋ እንደምትገድሉ። ተው ያልኩት ለዚህ ነበር። የገጠሩን ኑሮ አታውቁትም እና። የ

ድካሙ ሳይሆን የሰለቸኝ #ህሊናችሁን አቃቂሩ ነው።

ምስል
        ድካሙ ሳይሆን የሰለቸኝ #ህሊናችሁን አቃቂሩ ነው። ዝም ማለት ይቻላል። ሳልናገር፣ ሳላሳስብ የጎደለ ነገር የለምና። እኔን ማድመጥ ለተሳነው የኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ፖለቲከኛ በልኩ መቆጠብ በእጅ ያለ ነገር ነው። የትኛው መሃያዬ፣ የትኛው የምረዳው እንዳይቀር? እኔ ዘመኔን በሙሉ በፖለቲካ ተግባር ነው የኖርኩት። ለዛውም እራሴን ጎድቼ። ከአለ አንድ አይዞሽ ባይ፣ ካለ ብጣቂ ምስጋና። እዬታገትኩኝ። ማዕቀብ እዬተጣለብኝ። እዬተሳደድኩኝ። ፌስቡክ በምክንያት ነው የጀመርኩት። ልሰራበትም አልነበረም። እኔ የሦስት ዓመት ታጋይ አይደለሁም። እኔ ግርባው ኢህአዴግም መስኪን ይጥራት፣ ፈቅዳ ትሂድ እሱ አልነበረም አመክንዮ። በዚህ ወጀብ ጊዜ ምን ልትሆን ባህርዳር ሄደች ነው ሃሳቤ። ከዛ በተረፈ ሠርታለች፣ ደክማለች ልትሸለም ሲገባ ስለምን ታሠረች ነው። ለዚህ ነው የሄደችው፣ ለዛ ነው የሄደችው የእኔ ጉዳይ አይደለም። ሁሉን ሚዲያም አላዳምጥም። ጊዜውም የለም። እሱ ብቻ ሳይሆን እኔ በምመለከትበት አቅጣጫ አይደለም ሰው ያለው። የሆነ ሆኖ የፖለቲካ ትግል ይቅርብኝ የምትሉት ብዙ ነገሮች አሉበት። እናቴ ትቅርብኝ ከማለት በላይ #መስዋዕትነት የለም። እኔ ሁሉ በወረፋ አገር ሲገባ ተጠይቄያለሁ። አልፈቀድኩትም። "ሁሉ ተፈቅዶልኛል፣ ሁሉ ግን አይጠቅምም" ጊዜን ማስተዋል ይጠይቃል። እሳት እዬነደደ ልቀቀል፣ የመጣ ይምጣ አይባልም። ለዛውም ትዳር፣ ልጆች ያሉት ሰው። መስኪ ጎጃም ባህርዳር በዚህ ጦርነት ለታወጀበት ጊዜ መሄዷን አልፈልገውም። እራስን ማዳን ይገባል። ባትሄድ አያስሯትም፣ ያስሯታል አይደለም። ወጀብን ዝቅ ብሎ ማሳለፍ ይገባል። ጥበብ ይጠይቃል። መቅደም ይጠይቃል። ስልት ይጠይቃል። እለፈኝ ማለት ይጠይቃል። መስኪን እግዚአብሔር አውጥቷታል ነው የምለው።

የአማራ ዘመናት ጦርነት ተከፍቶባቸዋል። ፋኖ የአማራ የተፈጥሮ መከላከያ ኃይል ነው።

ምስል
  የአማራ ዘመናት ጦርነት ተከፍቶባቸዋል። ፋኖ የአማራ የተፈጥሮ መከላከያ ኃይል ነው። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" እንዴት ነን? እንዴት ይዞናል የጦርነት ውሎው? የአማራ ልጅ ስለምን ተወለክክ ነው የኦነግ ጦርነት? እሱ በሰራት፣ ባበጃት፣ ባሳመራት አገር ለምን ተፈጥረህ ተገኜህ ነው። ስለምን አገር እንዲህ በቻርተር የምንቀባረርበት ቤተ መንግሥት አደራጅተህ ጠበቅህ ነው ግብግቡ። አማራ ባይፈጠር ኢትዮጵያ ምን ትመስል ነበር? አማራ ባይኖር ዘመናቱ ምን ይሆኑ ነበር። ከአማራ ጋር የቀደሙ ማህበረሰቦች አሉ። በአማራ ላይ ያለው ውርጅብኝ ግን መስፈሪያ የለውም። ይህ ሲሰላ የአማራ ሕዝብ ረቂቅ መንፈሳዊ ፀጋ አላኃዊ፣ እግዚአብሔራዊ መሆኑ በዝምታ በማሳልፋቸው ቀኖች ጠረጴዛዬ ላይ ቁጭ አድርጌ የማወያያቸው በትረ ጉዳዮች ናቸው። አማራነት ንባቡ፣ ትርጉሙ፣ ሚስጢሩ ጊዜ ተሰጥቶ ሊጠና የሚገባው የዘመናችን ክስተት ነው። አማራነት ፊኖሚናል የመሆን አቅሙ ግርማ ሞገስ አግኝቷል። የአቶ ጃዋር ቃለምልልስ ጭንቅ ጥብብ የሚለው የአማራ አቅም መጎልበት፣ መፋፋት፣ እንደ ችብኃ መለምለም ስቃዩ፣ ውጋቱ፣ ረፍት ያሳጣው ሆኗል። ጨምቶ ከርሞ የወጣበት ተልዕኮ መሳሪያውን ብታስፈቱት ህሊናውን ማስፈታት ትጥቅ ይከብዳል ይላል። እሱ አያውቀውም። የአማራ ልጅ በሰላም ጊዜም፣ በጦርነት ጊዜም ምንጊዜም ህሊናው ትጥቅ ፈቶ እንደማያውቅ። የአማራ ልጅ ሲፈጠር ኃላፊነት ይዞ ይወለዳል። እራሱን፣ አካባቢውን ለመጠበቅ። ይህ አማራ ከተፈጠረበት ዘመን ጀምሮ ያለ፣ የነበረ ዕውነት ነው። እኔ ግንቦት 5/ 2010 አብይ ሆይ እኔም ዜጋ ከሆንኩ ብዬ ከ20 ገፅ በላይ ስጽፍ የአማራን የመንፈስ፣ የአካል ትጥቅ ትውፊታዊ ስለሆነ እንዳይነካኩት በትህትና አስገንዝቤያለሁኝ። ሌላም በዚህ ጭብጤ ላይ በእያንዳንዱ ቀበሌ

ዕውቅና

  ዕውቅናን በኮንፊደንስ ውስጥ ማኔጅ ሲደረግ #ማንጠራራት ትናንሽ ዬአንባገነን ችግኞችን ማብቀል ይሆናል። ዕውቅና በራሱ፤ ተፅዕኖ ፈጣሪነት በራሱ የአስተዳደር ብልህነትን አያጎናጽፍም። ቅብዓ በፈጣሪ ክህሎትም በድርጊታዊ ተሳትፎ ይነጥራል። በሥም ብቻ ብቃትም ቅባዕም አይገኝም። መመኜት ይቻላል። ምኞቱ ግን የሞገድ ፋንታዚ ሆኖ ይቀራል። ሥርጉ 2024/05/30

የናጠው

  ቀን የበደለው የለም። ቀኑን በዳይ አስፈሪ የሚያደርገው ፖለቲካው ነው። ስለሆነም ፖለቲካው ከአስፈሪነቱ ጭካኔ ጋር መፋታት ይኖርበታል። ስጋት የናጠው ህዝብ የሥነ - ልቦና ተጠቂ ይሆናል። ሥርጉ2024/05/30

ና!

 ጥሞና እባክህ ና! ሥርጉትሻ2024/05/30

ባለፈም

 ከእራስ ጋር እርቀ ሰላም ሳይደረግ ቤተሰብ ይመሰረታል። ባለፈም ህዝብ መሪነትም ይወሰዳል። መጀመሪያ እኔ እና እኔ በጥሞና ቁጭ ብለን ተነጋግረን እንፈራረም። ሥርጉትሻ2024/05/30

ዕለታት ሁሉ ውብ ናቸው

  እንዴት አደራችሁ? ዕለታት ሁሉ ውብ ናቸው። የምናከፋቸው እኛው ነን። ከሁሉ የሚደንቀኝ ግን ቅን ሰው ያገኜሁበት ዕለት ነው። ቅኖች ያላቸውን ሁሉ ያለገደብ ይሰጣሉ። ቅኖች ልግሥናቸው ከፀጋ ስጦታቸው ነውና ዳር ድንበር የለው። ሥርጉትሻ 2024/05/30

ክብሮቼ ቅንነትን እናክብር፨

 

አንድ አገር ጥበብነን ካሰረ ዓይኑን ግርዶሽ ይዞታል ማለት ነው

ምስል
      አንድ አገር ጥበብነን ካሰረ ዓይኑን ግርዶሽ ይዞታል ማለት ነው። ጥበብ እኮ የተሰወረን ክሱት የምታደርግ። ጠማማን አቆላምጣ የምታስተካክል። ዘባጣን አባብላ የምታርቅ የህሊና ጋራጅ ናት ላወቀበት። ግን ተፈራች። እስቲ ግርማ ሌሊቱን አምላካችን ይባርክልን። አሜን ደህና እደሩልኝ። ሁሉንም አስተያዬት አይቼዋለሁኝ። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። ሥርጉ2024/05/29

ትጉህ

ምስል
 

እንዴት አደራችሁ? ዕለታት ሁሉ ውብ ናቸው።

  እንዴት አደራችሁ? ዕለታት ሁሉ ውብ ናቸው። የምናከፋቸው እኛው ነን። ከሁሉ የሚደንቀኝ ግን ቅን ሰው ያገኜሁበት ዕለት ነው። ቅኖች ያላቸውን ሁሉ ያለገደብ ይሰጣሉ። ቅኖች ልግሥናቸው ከፀጋ ስጦታቸው ነውና ዳር ድንበር የለው። ሥርጉትሻ 2024/05/30

ከእራስ ጋር እርቀ ሰላም ሳይደረግ ቤተሰብ ይመሰረታል።

  ከእራስ ጋር እርቀ ሰላም ሳይደረግ ቤተሰብ ይመሰረታል። ባለፈም ህዝብ መሪነትም ይወሰዳል። መጀመሪያ እኔ እና እኔ በጥሞና ቁጭ ብለን ተነጋግረን እንፈራረም። ሥርጉትሻ2024/05/30

ጥሞና እባክህ ና!

 ጥሞና እባክህ ና! ሥርጉትሻ2024/05/30

ቀን የበደለው የለም

  ቀን የበደለው የለም። ቀኑን በዳይ አስፈሪ የሚያደርገው ፖለቲካው ነው። ስለሆነም ፖለቲካው ከአስፈሪነቱ ጭካኔ ጋር መፋታት ይኖርበታል። ስጋት የናጠው ህዝብ የሥነ - ልቦና ተጠቂ ይሆናል። ሥርጉ2024/05/30   ቀን የበደለው የለም። ቀኑን በዳይ አስፈሪ የሚያደርገው ፖለቲካው ነው። ስለሆነም ፖለቲካው ከአስፈሪነቱ ጭካኔ ጋር መፋታት ይኖርበታል። ስጋት የናጠው ህዝብ የሥነ - ልቦና ተጠቂ ይሆናል። ሥርጉ2024/05/30

ውቦቼ እንዴት ናችሁ ፈውስ ይህውላችሁ። "በቀላሉ ክብደት መቀነስ! ከሀኪም በላይ ሰውነትን ማድመጥ! ከአለም ሲስተም ማምለጥ || ገነት አህፈሮም | Many..."

ምስል

ኢትዮጵያ የሥርዓት ለውጥ ብቻ ሳይሆን የአስተሳሰብ ለውጥም ያስፈልጋታል፨ አጽናኝ ፖለቲካ ትሻለችና፨

ምስል

ውቦች ቅን ቀን ይስጣችሁ። አሜን።

 ውቦች ቅን ቀን ይስጣችሁ። አሜን። ቸር ዋሉ። አሜን ሥርጉትሻ።