ልጥፎች

🔴ቲክቶክ ተጥለቀለቀ Dagne Walle - Wond Lij Korete _ ዳኜ ዋለ _ ወንድ ልጅ ቆረጠ - New ...

ምስል

Dagne Walle Wond Lij Korete ዳኜ ዋለ ወንድ ልጅ ቆረጠ New Ethiopian Music ...

ምስል

Dagne Walle - Wond Lij Korete | - New Eithopian Music 2024 | (Official V...

ምስል

Dagne Walle - Wond Lij Korete | ዳኜ ዋለ _ ወንድ ልጅ ቆረጠ - New Ethiopian Music...

ምስል

New Epic Dagne Walle - Wond Lij Korete | ዳኜ ዋለ _ ወንድ ልጅ ቆረጠ - 2024 Ethio...

ምስል

Why Ethiopia Is Great :TEDDY AFRO - ቤዛ (ኅብረ ዝማሬ) | BEZA - New 2024] GHAN...

ምስል

Epic Africa Hip Hop Teddy Yo - Yileyal / Ghanaians React /Ethiopia 2024

ምስል

ቅኔው ጎጃም የትህትናው ውሃ ልክ በትሁቱ ሃብታሙ ይሄነው መስፈር ይቻላል።

ምስል
  ቅኔው ጎጃም የትህትናው ውሃ ልክ በትሁቱ ሃብታሙ ይሄነው መስፈር ይቻላል።   "አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁ።"   ሃብትሽን የመሰለ ወጣት ማዬቴን እግዚአብሄርን አመሰግንኃለሁ ብል የተገባ ነው። እኔ የሚጨንቀኝ የትውልዱ ጉዳይ ነው። ዓለም እራሷ ታስፈራኛለች። ምክንያቴ አሉታዊ ነገሮች ጉልበት ስለሚያገኙ። የሆነ ሆኖ ሃብትሽ የጋራጅ ሰራተኛ ነው። እንደ ዋዛ ፋና ላምሮት ተወዳደረ። እናማ አራተኛ ወጥቶ ተሸለመ።   አሁን ፋና ላምሮት የ፲፫ኛ፦ ዬ ፲፬ኛ፦ የ ፲፭ኛ ዙር አሸናፊወችን እና በዩዙሩ ብቃት አሳይተው ግን በዕለት ፐርፎርማንስ ዕድል ያልቀናቸውን አክሎ ለአሸናፊወች አሸናፊ እያወዳደረ ነው።   እኔ ከቀን አንድ ጀምሮ ሃብትሽን ሳዬው ትህትናው መሰጠኝ። ስለሆነም ተግቼ እከታተለዋለሁኝ። ዕውነት ለመናገር መከታተል ከጀመርኩ ጀምሮ በማያቸው ተወዳዳሪወች የሙዚቃ ብቃት ሳይሆን በሰብዕና ውቅራቸው ላይ በአትኩሮት እከታተላለሁኝ። እናም እረካለሁኝ። አሁን የዙር ፲፭ አሸናፊ ሄኖክ ብርሃኑ እርጋታው ይመስጠኛል። ፋክት ፈላጊነቱም ይደንቀኛል። መሰናዶው ፋክት ፍለጋ ላይ ነውና። የወደፊት የፋክት ሙዚቀኛ መሠረት ጣይም ይሆናል ብዬ አስባለሁ።   ዛሬ እምጽፈው ስለ ሃብትሽ ምክንያቴ በወጣት ጉዳይ ላይ ማስታወቂያ የሚሠሩ፤ በፊልም ፕሮዳክሽን ውስጥ የምስጉን ወጣት ካራክተር ላላቸው ወገኖቼ ሃብትሽ ትክክለኛ ወጣት መሆኑን ዘለግ አድርጌ በትሁት መንፈስ ለማሳሰብ ነው። ቅኔው ጎጃም ሁሉንም የሰጠው ነውና ለትህትናም ይህን የመሰለ ብሩህ ተስፋ ወጣትንም ያፈራል። መመካት ተገቢ ባይሆንም ተስፋዬ ግን ፋፍቷል።    ይህ ወጣት እኔ እንደማስበው በሥራ አካባቢው፤ ለጓደኞቹም ትህትናን በገፍ እንደሚመግብ ተስፋዬ ሙሉዑ ነው። የፋና ላምሮት ዳኞች ትሁት ናቸው የሚሰጡትን ማስተ

ባላገሩ ምርጥ ኮሌጅ የኢትዮጵያ አዲስ ትውልድ አናጢ። ዋግ ኽምራም ወጉ ደረሰው።

ምስል
  ባላገሩ ምርጥ ኮሌጅ የኢትዮጵያ አዲስ ትውልድ አናጢ። ዋግ ኽምራም ወጉ ደረሰው።   የባላገሩ ምርጥ ለእኔ ኮሌጅ ነው። ለዛውም የሁለመና። ብቁ ዜጋን ለማፍራት የወላጅን፤ የአገርን፤ የዜግነትን ኃላፊነት ፈቅዶ ተረክቦ የሚተጋ ድንቅዬ ተቋም። ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ወዘተረፈ ችግር ምንጩ የተቋም ምስረታ፤ ዝልቀት ጉዳይ ነው። የመጣ ቢመጣ፤ የሄደ ቢሄድ ተቋም ከተገነባ ህዝብ አይንገላታም። ሰላሙን አያጣም። ተስፋው አይፈናቀልም።   "አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁኝ።"       ባላገሩ ምርጥ ተግባሬ ብሎ ለተነሳበት ተልዕኮ ወጀቡን፤ ጎርፋን፤ ማዕበሉን ታግሦ ለአመታት የተጋበትን ዘር አሰበለ። ባላገሩ ምርጥ ዓውድዓመታትን ተነጣጥሎ አያከብርም። ሙሉ ቤተሰቡ በአንድ ማዕድ ክብብ ብለው ያሳላፋሉ። ይመስጡኛል። ባላገሩ ምርጥ የእነ ተሎ ተሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥን ብሂል ያደመጠ የኢትዮጵያ ጌጥ ተቋም ነው። ባላገሩ ምርጥ እንደ ቅኔወቹ ሙያ በልብን መስጥሮ ብቃትን በጥረት፤ በክህሎት በትዕግስት ያሸነፈ ጀግና ተቋም ነው። እኔ ባላገሩን ምርጥ ሳይሰለቸኝ ተስፋን ሰንቄ ተስፋዬን ሙሉ ለሙሉ እማገኝበት ተቋም ስለሆነ ውስጤ አድርጌ እከታተለዋለሁኝ።   ባላገሩ ምርት ስኬት የሰላማዊ ጥረት ውጤት ስለመሆኑ ትቤት ሆኖ አሳይቷል። ባላገሩ ምርጥ ሩህሩህ ስለሆነ በግብረ ሰናይ ተቋማትም ይሳተፋል። አጤ ደግዬ።   የባላገሩ ምርጥ ሞደሬተር ረዱ ልዩ ናት። ገበሬም፤ ወጣትም፤ ሴትም ባጠቃላይ የማህበረሰብ አደራጅ ስነበርኩኝ ቃናዋ የሚናፍቀኝ አገርኛ ተፈጥሮኛ አቀራረብ ይመስጠኛል ብቻ ከምል አልጠግበውም። ማንጠግቦሽ ናት። ፀጉሯ ውበቱ ከነተፈጥሮው ነው። አለባበሷ ተፈጥሮ። የአነጋገር ዘይቤዋ ተፈጥሮ። ለእሷ ስል ምነው ኢቤንት በኖረኝ እስክል ድረስ ትስበኛለች። ብቁ ለኢትዮጵያ ተፈ

የአቸፈሯ ልበ ሙሉ ወጣት። ልዕልት #ፏዬ!

ምስል
    የአቸፈሯ ልበ ሙሉ ወጣት። ልዕልት #ፏዬ !   NBC የኢትዮጵያው ለ፲፯ ቀናት ተከታታይ የሙዚቃ ውድድር ነበረው። ይህቺ ወጣትም ተሳታፊ ነበረች። ትውልድ እነፃን በሚመለከት የሲዊዝ፤ የጀርመን የኢትዮጵያን የወጣቶች የመክሊት፤ የተስጥዖ ውድድር ጊዜ መድቤ እከታተላለሁ። ሁለት መፃህፍት የፃፍኩትም መነሻዬ ይኽው ነው። ይመስለናል በአስተዳደግ ላይ ተስጥዖን ፈልጎ በማግኜት ሆነ በቲም ወርክ ይሆን ኃላፊነት እና ተጠያቂነትን ኮትኩቶ ማሳደግ የኢትዮጵውያን ብቻ ድክመት። እኛ እንሻላለን በዘርፋ።    የሆነ ሁኖ በዚህች ድንቅ ወጣት ያዬሁት ወደ ላይ ያላሻቀበ፤ ወደ ታችም ያልዘገጠ በራስ የመተማመን አቅም ለትውልድ ግንባታ ልዩ አቅም ይሆናል ብዬ ነው እማምነው። ልትደገፍ፤ ልትታገዝ ይገባል። ቀለሟ ይስባል። የሳቅ ልዕልት ናት። ፏ ያለች ቃናዋ የሚስብ ለዘርፋ የተፈጠረች ድንቅዬ ናት። ደግፏት።   በውድድሩ ሁለተኛ ነው የወጣችሁ። አቅሟ ግን ከምትገምቱት በላይ ነው። አርቲስት መሲን እንደምን ከቦታዋ ሂዳ ጋብዛ መልሳ በክብር እንደምን ወደ ቦታዋ እንደመለሰቻት ሳይ እኔ አሳዳጊሽን ይባርከው ብያለሁ። እኔ የሙዚቃ ሰው አይደለሁም። አይደለም በአሁኑ ዘመን ያለውን በእኔ ዘመን ያለውንም ብትጠይቁኝ አላውቀው።    እኔ እምከታተለው ሰብዕናቸውን በተሰጣቸው መክሊት ላይ ምን አቅም አላቸው፤ በራስ የመተማመን አቅማቸው ምን ያህል ነው የሚለውን ነው እምከታተለው። በሁለት ምክንያት። አንደኛው ነገ ኢትዮጵያ የእነሱ ናት፤ ሁለተኛው እነሱ እራሳቸው የሚተኩት ትውልድ አላቸውና በሚገባ እከታተላለሁኝ። የውጪ አገሩን ጭምር እከታተላለሁ። ዛሬ ዛሬ ደከመኝ እንጂ አስተያዬትም እልክ ነበር። የሆነ ሆኑ ይህቺ ቀንበጥ ሁለመናዋ ዕንቁ ነው። ወድጃታለሁኝ። በዚህ ሁሉ ችግር ማህል ተፈጥሯዊ የራስ መተማመ

በፍፁም እንዲህ አልጠበኩም ነበር! ዶክተር ብቻ አይደለም! በአሜሪካ የዶክተር ህይወት እንዴት ነው? #usa#ame..."ቅኔው፤ ድጓው፤ ተደሟዊው ዶር. ይሳህቅ መሃመድ አደም የግዕዝን ቁጥር በሉላዊ ደረጃ ብራንድ ያደረጉ ምጥቅ የማስተዋል ጀግናዬ።

ምስል
ቅኔው፤ ድጓው፤ ተደሟዊው ዶር. ይሳህቅ መሃመድ አደም የግዕዝን ቁጥር በሉላዊ ደረጃ ብራንድ ያደረጉ ምጥቅ የማስተዋል ጀግናዬ። ካሰብኩት ሼር ለማድረግ ቆዬው። የባተሌ ነገር በዛብኝ እና ሳልችል ሰነበትኩኝ። ግን የእኔ ክብሮች እንዴት ሰነበታችሁልኝ? ከመጋቢት 10/ 2010 እስከ ዛሬዋ ዕለተ ሰንበት 2016 ዓም ድረስ ፲፩ ምዕራፎችን አዬን። ፲፪ኛውም ተጀምሯል። የኛ ቤት ታዳሚው በደራሽ ዜናወች ስለባተለ ተግ አደረኩት አዲሱን ምዕራፌ። አጤ ቲክቶክም መፈንቅለ በአጤ ፌቡ እያካሄደ ነው። የጤና ያድርግለት ብቻ አጤ ቲክቶክ። እዬገሰገሰ ነው። ለነገሩ ወጣቶቹ ለአወንታዊ የተሰለፋት ይስባሉ። ሁሉም ቦታ ለመሳተፍ ጊዜውም ድካሙም ሆነ እና ብዙም አላተኩርም ቲክቶክ ላይ ሰሞኑን በአርቲስት ዳኜ ምክንያት እኔም ትንሽ ሰሞኑን ሼር አድርጌያለሁ። ደስ የሚሉ ወጣቶች ናቸው። ወኔ!!!!! #ጉዳዬ ። "አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁ።" የዶር ይሳህቅ ሥም የእስልምና ነው። ተግባራቸው ደግሞ ቀደምቷን የኢትዮጵያ ክብር ምራኝ ያለ አንቱ ነው። ለብዙ የእስልምና እምነት አዋቂወች ግዕዝን አጥኑት ሚስጢር ይገለጥላችሁ ዘንድ ስል ኑሬያለሁ በመድረክ ዙሪያ ላሉት። እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል ሰው ግን አያስተውለውም የሚለው ቃለ ወንጌል ተስተውሎ አገኜሁት። እኒህ ታላቅ ሰው የኢትዮጵያን ቀደምት ጥሪት ብቻ ሳይሆን የፐርስሽንም የሌሎችንም የሰዓት ብራንዳቸው ለማድረግ ቆርጠዋል። ለእኔ አናባቢም ተነባቢም ሆነው አግኝቻቸዋለሁኝ። እናታችን ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለእኒህ አራት ዓይናማ ትጉህ ዕውቅና ሰጥታ እንድታከብራቸው፤ እንድትሸልምቸው ስል በትህትና አሳስባለሁኝ። በሀገረ አሜሪካ የምትገኙ የተዋህዶ ልጆች፤ ኢትዮጵያን ውስጣችሁ ያደረጋችሁ ልዩወቼም ለእኒህ ፍፁም ቅን የ

ኢትዮጵያ የኩንትራት ኦብጀክት አይለችም ወይንም በቦንዳ የምትመተር ነዶ አይለችም ፨ ኢትዮጵያ የቅልሞሽ፤ የገበጣ፥ ...

ምስል

ክብረ ሰው ሲፈጠር ለመልካምነት ውስጠ ብርኃን ሆኖ ነው። ክብረ ሰው ከክፋ ነገር ጋር ፈቅዶ ሲዋህድ ውስጠ ጽልመት ...

ምስል

Extrajudicial Killings Leave 66 Dead in Ethiopia, Group Says

  Extrajudicial Killings Leave 66 Dead in Ethiopia, Group Says   https://www.bloomberg.com/news/articles/2024-02-13/extrajudicial-killings-leave-66-dead-in-ethiopia-group-says