በፍፁም እንዲህ አልጠበኩም ነበር! ዶክተር ብቻ አይደለም! በአሜሪካ የዶክተር ህይወት እንዴት ነው? #usa#ame..."ቅኔው፤ ድጓው፤ ተደሟዊው ዶር. ይሳህቅ መሃመድ አደም የግዕዝን ቁጥር በሉላዊ ደረጃ ብራንድ ያደረጉ ምጥቅ የማስተዋል ጀግናዬ።

ቅኔው፤ ድጓው፤ ተደሟዊው ዶር. ይሳህቅ መሃመድ አደም የግዕዝን ቁጥር በሉላዊ ደረጃ ብራንድ ያደረጉ ምጥቅ የማስተዋል ጀግናዬ።
ካሰብኩት ሼር ለማድረግ ቆዬው። የባተሌ ነገር በዛብኝ እና ሳልችል ሰነበትኩኝ። ግን የእኔ ክብሮች እንዴት ሰነበታችሁልኝ? ከመጋቢት 10/ 2010 እስከ ዛሬዋ ዕለተ ሰንበት 2016 ዓም ድረስ ፲፩ ምዕራፎችን አዬን። ፲፪ኛውም ተጀምሯል።
የኛ ቤት ታዳሚው በደራሽ ዜናወች ስለባተለ ተግ አደረኩት አዲሱን ምዕራፌ። አጤ ቲክቶክም መፈንቅለ በአጤ ፌቡ እያካሄደ ነው። የጤና ያድርግለት ብቻ አጤ ቲክቶክ። እዬገሰገሰ ነው። ለነገሩ ወጣቶቹ ለአወንታዊ የተሰለፋት ይስባሉ። ሁሉም ቦታ ለመሳተፍ ጊዜውም ድካሙም ሆነ እና ብዙም አላተኩርም ቲክቶክ ላይ ሰሞኑን በአርቲስት ዳኜ ምክንያት እኔም ትንሽ ሰሞኑን ሼር አድርጌያለሁ። ደስ የሚሉ ወጣቶች ናቸው። ወኔ!!!!!
"አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁ።"
የዶር ይሳህቅ ሥም የእስልምና ነው። ተግባራቸው ደግሞ ቀደምቷን የኢትዮጵያ ክብር ምራኝ ያለ አንቱ ነው። ለብዙ የእስልምና እምነት አዋቂወች ግዕዝን አጥኑት ሚስጢር ይገለጥላችሁ ዘንድ ስል ኑሬያለሁ በመድረክ ዙሪያ ላሉት።
እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል ሰው ግን አያስተውለውም የሚለው ቃለ ወንጌል ተስተውሎ አገኜሁት። እኒህ ታላቅ ሰው የኢትዮጵያን ቀደምት ጥሪት ብቻ ሳይሆን የፐርስሽንም የሌሎችንም የሰዓት ብራንዳቸው ለማድረግ ቆርጠዋል። ለእኔ አናባቢም ተነባቢም ሆነው አግኝቻቸዋለሁኝ።
እናታችን ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለእኒህ አራት ዓይናማ ትጉህ ዕውቅና ሰጥታ እንድታከብራቸው፤ እንድትሸልምቸው ስል በትህትና አሳስባለሁኝ። በሀገረ አሜሪካ የምትገኙ የተዋህዶ ልጆች፤ ኢትዮጵያን ውስጣችሁ ያደረጋችሁ ልዩወቼም ለእኒህ ፍፁም ቅን የአንድነት አንበል አክብሮታችሁን የምትገልፁበት ኢቤንት ብታሰናዱ መልካም ነው።
በጥሩ ምግባሩ የሚታወቀው ዓለም ዓቀፍ የስሜን አሜሪካ ፌስቲባል አሰናጆችም ዘንድሮ የባላገሩ ምርጦችን ለማስተናገድ ቢያቅድም ለእኒህ ዕንቁም ክብሩ ናቸው እና ዕውቅና ባይነፍጋቸው ስል አሳስባለሁ።
ኢትዮጵያ ታሸንፋለች ሲባል በስማ በለው አይደለም። እእ። መንፈሯ ማግኔት ነው። ይስባል። ይመስጣል። ለማዕረጉ፤ ለሞገሱ ለራሱ አይሰንፍም ነው። መገለጫው በብዙ መልኩ ነው። የኢትዮጵያዊነት ኃያል ቅዱስ መንፈስ ርቁቁ ነውና።
ዶር ይሳህቅ መሃመድ እናታቸውን መስጥረው በልባቸው ስለ ሰነቁ እሪዝቅ የሚዝቁበትን ቅዱስ መንፈስ ታጠቁ። ምርቃታቸው አፈራ። እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ መክሊት፤ መልዕክት ጥሪ ይዞ ይወለዳል የምለው ፍልስፍና አለኝ። ዶር ይሳቅ መልዕክታቸውን፤ መክሊታቸውን ጥሪያቸውን ያላፈሰሱ አንቱ ኢትዮጵያዊ ናቸው ለእኔ።
ጥረታቸውን የህይወታቸውን ጉዞ ከማራኪ ወግ ኮምኩም። ኢኒስተግራማቸውን ፎሎው አድርጉ በትህትና ነው ጥያቄዬ፤ አሜሪካም ኢትዮጵያም ያላችሁ ወገኖቼ የግዕዝ ቁጥር ያለበትን ሰዓት ገዝታችሁ ሽክ በሉ።
የገረመኝን አንድ ነገር ሹክ ልበላችሁ። ዓራት ዓይናማ ትጉህ ብቻ ሳይሆኑ የወጣላቸው ለጋስም ናቸው። ስስት የሌለባቸው ዓይነ ሙሉ። ቃላ ምልልሱን እህቴ አሜሪካ እኔ ሲዊዝ ሁለታችንም እኩል ተከታትለነው የገረመን ማዕዶት ልግስናቸው እና ቅንነታቸው ነው። ቅኖች አወንታዊም ናቸውና።
እህቴ እምትከታተለው እንዲህ ዓይነቱን ነው። እኔ አዳመጥኩት ስል ደስታዋ ወደር የለውም። ምክንያቱም ሙሉ ዕድሜዬ፤ ሙሉ ጊዚዬ ለተከፋት ስለማተኩር በሁሉም መስክ እንደተጎዳሁ ታውቃለች። ለዚህ ነው ለዬት ያሉ ጉዳዮች አዳምጫለሁ ስላት ፍንክንክ፤ ፍልቅልቅ የምትለው። በውነቱ ኢትዮጵያን ውስጣቸው ያደረጉም እንደ ብላቴ ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ውስጤም፤ ክብሬም፤ ማዕረግ እና ሞገሴም ናቸው። በውነቱ የእናታችን ደህንነት ማገር እና ወጋግራ እንደዚህ ዓይነት የተግባር አዛውንቶች ናቸው። መዳኛችንም ፈውሳችንም።
ጉዳዩ የንግድ ጉዳይ አይደለም። መነሻውን ያወቀ የመድረሻው አጤ ነውና። ስለሆነም አሜሪካን አገር ብዙ የሚታትሩ ኢትዮጵያዊ ተቋማት እናመሰግንኃለን ቢሏቸው ፈቃዴ ነው። ልባሙ ጀርመንማ ሃይድልበርግ ዩንቨርስቲ፤ ሃንቡርግ ዩንቨርስቲ፤ በርሊን ፍሪ ዩንቨርስቲ ልጆቻቸውን በግዕዝ ያስመርቃሉ። ግዕዝ እና የዩንቨርስ ሚስጢር ውህድ ናቸው ለእኔ።
በተረፈ ጋዜጠኛ ግዛን አመሰግናለሁ።
በፍፁም እንዲህ አልጠበኩም ነበር! ዶክተር ብቻ አይደለም! በአሜሪካ የዶክተር ህይወት እንዴት ነው? #usa#america#watch#lifestyle#ishac
ይሳህቅ መሃመድ
ኢኒስተግራም ፔጅ ነው።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
2024/10/03
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።