የአቸፈሯ ልበ ሙሉ ወጣት። ልዕልት #ፏዬ!

 

 
የአቸፈሯ ልበ ሙሉ ወጣት። ልዕልት #ፏዬ!
 
NBC የኢትዮጵያው ለ፲፯ ቀናት ተከታታይ የሙዚቃ ውድድር ነበረው። ይህቺ ወጣትም ተሳታፊ ነበረች። ትውልድ እነፃን በሚመለከት የሲዊዝ፤ የጀርመን የኢትዮጵያን የወጣቶች የመክሊት፤ የተስጥዖ ውድድር ጊዜ መድቤ እከታተላለሁ። ሁለት መፃህፍት የፃፍኩትም መነሻዬ ይኽው ነው። ይመስለናል በአስተዳደግ ላይ ተስጥዖን ፈልጎ በማግኜት ሆነ በቲም ወርክ ይሆን ኃላፊነት እና ተጠያቂነትን ኮትኩቶ ማሳደግ የኢትዮጵውያን ብቻ ድክመት። እኛ እንሻላለን በዘርፋ። 
 
የሆነ ሁኖ በዚህች ድንቅ ወጣት ያዬሁት ወደ ላይ ያላሻቀበ፤ ወደ ታችም ያልዘገጠ በራስ የመተማመን አቅም ለትውልድ ግንባታ ልዩ አቅም ይሆናል ብዬ ነው እማምነው። ልትደገፍ፤ ልትታገዝ ይገባል። ቀለሟ ይስባል። የሳቅ ልዕልት ናት። ፏ ያለች ቃናዋ የሚስብ ለዘርፋ የተፈጠረች ድንቅዬ ናት። ደግፏት።
 
በውድድሩ ሁለተኛ ነው የወጣችሁ። አቅሟ ግን ከምትገምቱት በላይ ነው። አርቲስት መሲን እንደምን ከቦታዋ ሂዳ ጋብዛ መልሳ በክብር እንደምን ወደ ቦታዋ እንደመለሰቻት ሳይ እኔ አሳዳጊሽን ይባርከው ብያለሁ። እኔ የሙዚቃ ሰው አይደለሁም። አይደለም በአሁኑ ዘመን ያለውን በእኔ ዘመን ያለውንም ብትጠይቁኝ አላውቀው። 
 
እኔ እምከታተለው ሰብዕናቸውን በተሰጣቸው መክሊት ላይ ምን አቅም አላቸው፤ በራስ የመተማመን አቅማቸው ምን ያህል ነው የሚለውን ነው እምከታተለው። በሁለት ምክንያት። አንደኛው ነገ ኢትዮጵያ የእነሱ ናት፤ ሁለተኛው እነሱ እራሳቸው የሚተኩት ትውልድ አላቸውና በሚገባ እከታተላለሁኝ። የውጪ አገሩን ጭምር እከታተላለሁ። ዛሬ ዛሬ ደከመኝ እንጂ አስተያዬትም እልክ ነበር። የሆነ ሆኑ ይህቺ ቀንበጥ ሁለመናዋ ዕንቁ ነው። ወድጃታለሁኝ። በዚህ ሁሉ ችግር ማህል ተፈጥሯዊ የራስ መተማመን አቅም በዚህ ልክ ጎልቶ ማዬቴ አስደስቶኛል። በርችልኝ የእኔ ልዕልት። #ሁነኛ!
 
ክብሮቼ ወጣት አደራጅም ስለነበርኩ ለወጣቶቼ እሳሳለሁኝ።
 
"አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁ።"
• ጥበብ እና ትውልዱ። ጥበብና በራስ የመተማመን የአቅም መቅኖ። አዜብ ዳኜ
ድምጻዊት አዜብ ዳኘው ከሞሰብ ባንድ ጋር ገራሚ ድምጽ ። Amazing Singer Azeb Dagnew With Moseb Band
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
2024/03/10
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።