ባላገሩ ምርጥ ኮሌጅ የኢትዮጵያ አዲስ ትውልድ አናጢ። ዋግ ኽምራም ወጉ ደረሰው።

 

ባላገሩ ምርጥ ኮሌጅ የኢትዮጵያ አዲስ ትውልድ አናጢ። ዋግ ኽምራም ወጉ ደረሰው።
 
የባላገሩ ምርጥ ለእኔ ኮሌጅ ነው። ለዛውም የሁለመና። ብቁ ዜጋን ለማፍራት የወላጅን፤ የአገርን፤ የዜግነትን ኃላፊነት ፈቅዶ ተረክቦ የሚተጋ ድንቅዬ ተቋም። ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ወዘተረፈ ችግር ምንጩ የተቋም ምስረታ፤ ዝልቀት ጉዳይ ነው። የመጣ ቢመጣ፤ የሄደ ቢሄድ ተቋም ከተገነባ ህዝብ አይንገላታም። ሰላሙን አያጣም። ተስፋው አይፈናቀልም።
 
"አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁኝ።"
 
 May be an image of 10 people, trumpet and textMay be an image of 1 person, trumpet and textMay be an image of 1 person and textMay be an image of 1 person, trumpet and textMay be an image of 1 person and text
 
ባላገሩ ምርጥ ተግባሬ ብሎ ለተነሳበት ተልዕኮ ወጀቡን፤ ጎርፋን፤ ማዕበሉን ታግሦ ለአመታት የተጋበትን ዘር አሰበለ። ባላገሩ ምርጥ ዓውድዓመታትን ተነጣጥሎ አያከብርም። ሙሉ ቤተሰቡ በአንድ ማዕድ ክብብ ብለው ያሳላፋሉ። ይመስጡኛል።
ባላገሩ ምርጥ የእነ ተሎ ተሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥን ብሂል ያደመጠ የኢትዮጵያ ጌጥ ተቋም ነው። ባላገሩ ምርጥ እንደ ቅኔወቹ ሙያ በልብን መስጥሮ ብቃትን በጥረት፤ በክህሎት በትዕግስት ያሸነፈ ጀግና ተቋም ነው። እኔ ባላገሩን ምርጥ ሳይሰለቸኝ ተስፋን ሰንቄ ተስፋዬን ሙሉ ለሙሉ እማገኝበት ተቋም ስለሆነ ውስጤ አድርጌ እከታተለዋለሁኝ።
 
ባላገሩ ምርት ስኬት የሰላማዊ ጥረት ውጤት ስለመሆኑ ትቤት ሆኖ አሳይቷል። ባላገሩ ምርጥ ሩህሩህ ስለሆነ በግብረ ሰናይ ተቋማትም ይሳተፋል። አጤ ደግዬ።
 
የባላገሩ ምርጥ ሞደሬተር ረዱ ልዩ ናት። ገበሬም፤ ወጣትም፤ ሴትም ባጠቃላይ የማህበረሰብ አደራጅ ስነበርኩኝ ቃናዋ የሚናፍቀኝ አገርኛ ተፈጥሮኛ አቀራረብ ይመስጠኛል ብቻ ከምል አልጠግበውም። ማንጠግቦሽ ናት። ፀጉሯ ውበቱ ከነተፈጥሮው ነው። አለባበሷ ተፈጥሮ። የአነጋገር ዘይቤዋ ተፈጥሮ። ለእሷ ስል ምነው ኢቤንት በኖረኝ እስክል ድረስ ትስበኛለች። ብቁ ለኢትዮጵያ ተፈጥሮ ብቁ ሞደሬተር ናት።
የዳኝነት ውሎ ጠበቅ፤ ጠንከር ያለም አለበት። ያው ዳኝነትም ትማሩበታላችሁ እንደማለት። ለዚህ ዝምተኛው ሶፊ ከጠንካራ ዳኛወች ውስጥ ይመደባል። በዳኝነቱ ውስጥ ድልድይም እናትም፤ እንደ አባትም ገፀ ባህሬ አይቻሎለሁ። ሦስትም አንድም። 
 
በመጨረሻ ውጤት ወላጆቹ የቤተ ክርስትያን ዘማሪ፤ እሱም የቤተክርስቲያን ዘማሪነቱ ይቆዬኝ ያለው የአክሊል ሆኗል። ያልተጠበቀ ውጤት ነበር። ዳኞች ተፈትነውበታል ብዬ አስባለሁ። አክሊል በራስ የመተማመን አቅሙ ልዩ ነበር። እኔ ብሩኬ ይሆናል ብዬ ነበር እማስበው። ምክንያቱም የዘራውም ያበቀለውም፤ ያሰበለውም ባላገሩ ስለሆነ ለሞዴል እሱ ይሆናል ብዬ ነበር። የሚደንቀው የመጨረሻ መሰናዶውን ሲያቀርብ ለአሳደገኝ የኢትዮጵያ ህዝብ እና የገበሬ ክብር ስል ብሎ በባዶ እግሩ ነበር ፕረዘንቴሽኑ። ይህ ልቅና እና ልዕልና በዚህ ዕድሜ??? አስሉት እሰቡት። የሚናፍቀኝ ትውልድ ይህ ነው።
 
ሦስተኛ የወጡት ሁለቱ ናቸው። የከሚሴው ስሚዙ እና የከፍቾው ቅዱሱ። አወን ባላገሩ ምርጥ አስተዳደር ጭንቀቱን ያሳያል። ሁለት ተወዳዳሪወች ሦስተኛ ወጡ። ለሦስተኛ የተመደበው ግማሽ ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር ስለነበር ለሁለት ተከፈለ። ስሚዙ ከፋው አልተቀበለውም። የእሱ ድርሻ ለግብረ ሰናይ ድርጅት ተሰጠ የሚል ዜና አዳምጫለሁኝ።
 
ስሚዙ ወላጅ እናቱ ክብርት የሙዚቃ ተስጥዖ ያላቸው የክሊኒክ ጽዳት ሠራተኛ ሆነው ያሳደጉት ስለመሆኑ ከታሪኩ አዳምጫለሁኝ። ከዚህ ሌላ የስሚዙ ቤተሰቦች እስልምና እና ተዋህዶ ሃይማኖትን ይከተላሉ። ተከባብረው በአህቲ ልቦና የሚኖሩ ልዩ አብነት የሆኑ ናቸው። በዕለቱም አበባ መስለው ተገኝተው ነበር። ስሚዙ ጥሎ ሲወጣም አይተዋል።
 
ስሚዙ ወጣት ነው። ወጣትነት ሁላችንም ስላለፍንበት ወጣት አትሁኑ ማለት አይቻልም። ወጣትነት በብዙ ይፈተናል። እኔ ወጣት እያለሁ የወጣት አደራጅ ስለነበርኩ በስሚዙ እርምጃ አልደነገጥኩም። ወጣትነት እንዲህም፤ እንዲያም መሆኑን ስለማውቅ። የሙያ አባታቸው ድንቁ አቶ አብርኃም ወልዴ የደከመበት እንዲህ ባይሆን ምኞቴ ነበር። ደስታው ሙሉ ቢሆን። 
 
ሌላው ባላገሩ ምርጥ አስተዳደር ልቅና የማስተዋል ደረጃ አወዳድሮ አልበተናቸውም። የጤና እክል ላላቸው ልዩ ዕውቅና፤ ልዩ አክብሮት፤ ልዩ ሽልማት ሰጥቷል። በተጨማሪም ከምርጦች ጋር ፲፪ ሁነው ካሴት እንዲያዘጋጁ ዕድል ከፍቷል። ይህ ብቻ አይደለም በ2024 በአሜሪካ የስፖርት ፌስቲባል አንደኛ የወጣው ሙዚቀኛ አክሊሉ አስፋውን የክብር እንግዳ ሲያደርግ ፲፩ ደግሞ ተጋባዥ አድርጓል። ተቋም መሪ ሲያገኝ እንዲህ ይመስላልና።
 
እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ሰብለ ህይወት የፀጋዬ ራዲዮ እና የከበቡሽ ሚዲያ ዋና አዘጋጅ ለባላገሩ ምርጥ ቲም፤ ለድንቁ አቶ አብርኃም ወልዴ ያለኝን ትሁት አክብሮት፤ ሞንሞን ያለ ምስጋና አቀርባለሁ። ተመስገንም ብያለሁ። ትውልድ እንዲህ ስክን ባለ አያያዝ እና ብልኃት ይበጃል። አብነትም ሽልማትም። 
 
ዳኞችን የፈተነው የተወዳዳሪዎች ድንቅ አቀራረብ | የፍጻሜ ውድድር በቀጥታ ስርጭት ከሚሊኒየም አዳራሽ @BalageruTV
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
2024/03/10
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።