ቅኔው ጎጃም የትህትናው ውሃ ልክ በትሁቱ ሃብታሙ ይሄነው መስፈር ይቻላል።

 

ቅኔው ጎጃም የትህትናው ውሃ ልክ በትሁቱ ሃብታሙ ይሄነው መስፈር ይቻላል።
 
"አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁ።"
 May be an image of 1 person and text
ሃብትሽን የመሰለ ወጣት ማዬቴን እግዚአብሄርን አመሰግንኃለሁ ብል የተገባ ነው። እኔ የሚጨንቀኝ የትውልዱ ጉዳይ ነው። ዓለም እራሷ ታስፈራኛለች። ምክንያቴ አሉታዊ ነገሮች ጉልበት ስለሚያገኙ። የሆነ ሆኖ ሃብትሽ የጋራጅ ሰራተኛ ነው። እንደ ዋዛ ፋና ላምሮት ተወዳደረ። እናማ አራተኛ ወጥቶ ተሸለመ።
 
አሁን ፋና ላምሮት የ፲፫ኛ፦ ዬ ፲፬ኛ፦ የ ፲፭ኛ ዙር አሸናፊወችን እና በዩዙሩ ብቃት አሳይተው ግን በዕለት ፐርፎርማንስ ዕድል ያልቀናቸውን አክሎ ለአሸናፊወች አሸናፊ እያወዳደረ ነው።
 
እኔ ከቀን አንድ ጀምሮ ሃብትሽን ሳዬው ትህትናው መሰጠኝ። ስለሆነም ተግቼ እከታተለዋለሁኝ። ዕውነት ለመናገር መከታተል ከጀመርኩ ጀምሮ በማያቸው ተወዳዳሪወች የሙዚቃ ብቃት ሳይሆን በሰብዕና ውቅራቸው ላይ በአትኩሮት እከታተላለሁኝ። እናም እረካለሁኝ። አሁን የዙር ፲፭ አሸናፊ ሄኖክ ብርሃኑ እርጋታው ይመስጠኛል። ፋክት ፈላጊነቱም ይደንቀኛል። መሰናዶው ፋክት ፍለጋ ላይ ነውና። የወደፊት የፋክት ሙዚቀኛ መሠረት ጣይም ይሆናል ብዬ አስባለሁ።
 
ዛሬ እምጽፈው ስለ ሃብትሽ ምክንያቴ በወጣት ጉዳይ ላይ ማስታወቂያ የሚሠሩ፤ በፊልም ፕሮዳክሽን ውስጥ የምስጉን ወጣት ካራክተር ላላቸው ወገኖቼ ሃብትሽ ትክክለኛ ወጣት መሆኑን ዘለግ አድርጌ በትሁት መንፈስ ለማሳሰብ ነው። ቅኔው ጎጃም ሁሉንም የሰጠው ነውና ለትህትናም ይህን የመሰለ ብሩህ ተስፋ ወጣትንም ያፈራል። መመካት ተገቢ ባይሆንም ተስፋዬ ግን ፋፍቷል። 
 
ይህ ወጣት እኔ እንደማስበው በሥራ አካባቢው፤ ለጓደኞቹም ትህትናን በገፍ እንደሚመግብ ተስፋዬ ሙሉዑ ነው። የፋና ላምሮት ዳኞች ትሁት ናቸው የሚሰጡትን ማስተካካያም ያደምጣል። ከትህትናው በተጨማሪም ሃብትሽ ብቁ አድማጭም ነው። እንዲህ ዓይነት ወጣቶችን ለፖለቲካ ፍጆታ ሳይሻሙ ከዛ ለላቀ የትውልድ የትውልድ ግንባታ ማዋል ብልህነት ይመስለኛል። ነፃ ሆኖ ፀጋውን ለትውልድ ያጋባ ዘንድ አደራ ፖለቲከኞች ተሻምታችሁ ተስፋዬን እንዳታደርቁት በትህትና አሳስባለሁ።
 
ትሁት፤ ትህትና በራሱ የተፈጥሯዊነት አንኳር ማገር ስለሆነ ለበለጠ ኃላፊነት ማሰቡ ይበጃል። ፖለቲካ ስንቱን ቡቃያ አሳሮ፤ አብልዞ አስቀርቷል። በተረፈ በሰለሞን እልፍኝም ታላላቅ የጥበብ ሰወች አላችሁ እና ለትህትና ትሁት ወጣት ሃብታሙ ይሄነው ይሄውላችሁ።
በነገራችን ጎጃምና ሥም አወጣጥ ቅኔ ከቤቱ ልበለው። በዚህ አጋጣሚ ሃብትሽን ላስተዋወቀኝ በመንፈስ ለፋና ላምሮትም ለምስጋና ቆጥቋጣ አይደለሁም እና አመሰግናለሁ። አደራ እምለው ፋና ላምሮት ከፖለቲካ ጋር እንዳታለካልኩት። አደራ። ተልዕኮው ይበልዛል ይማርታል ይፈልሳልም። እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
 
ስሜት አይጠናም ብላለች የፋና ላምሮቷ ማህል ዳኛ ብሌኗ። ወድጀላታለሁ አገላለፆዋን። ልስልስ ያለች የመሐል ዳኛ ናት። በነገራችን ላይ ዳኞች ያስተምራሉ በብዙ። እኔ ለመማርም ነው እምከታተለው። 
 
ፋና ላምሮት ፏፏቴ የሆነች የሳቅ ልዕልት አዲስ ሞደሬተር ሰላሜን ጨምሯል። ቤቱ ሙሉ ሳቅ ነው። ለተኛ ቀን ሰላሜ ፈውሱ ናት።
አዱኛወቼ በሉ ደህና ዋሉ፤ መሸቢያ ማዕልትም።
 
ዕለቱ በዚህ ይቋጭ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
2024/03/10
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።