ጥንካሬ + ስኬት= ድንቅነት። "ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሪፐብሊካን ፓርቲ እጩ አቶ አምሳሉ ፀጋዬ ካሳው BBC"
ጥንካሬ + ስኬት= ድንቅነት። https://www.bbc.com/amharic/articles/cr7v49kxg24o ባሕር ዳር የተወለዱት ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሪፐብሊካን እጩ በኮሎራዶ ግዛት የከተማ ምክር ቤት ምርጫ አሸነፉ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሪፐብሊካን ፓርቲ እጩ አቶ አምሳሉ ፀጋዬ ካሳው 18 ታህሳስ 2024 ትውልደ ኢትዮጵያዊ-አሜሪካዊው አቶ አምሳሉ ፀጋዬ ካሳው በኮሎራዶ አገረ ግዛት፣ የአውሮራ ከተማ ምክር ቤት ምርጫን ከትላንት በስትያ አሸንፈዋል። ይህም በኮሎራዶ አገረ ግዛት የመጀመርያው ትውልደ ኢትዮጵያዊያዊ ተመራጭ እንዲሁም የመጀመሪያው አፍሪካዊ ስደተኛ የምክር ቤት አባል ያደርጋቸዋል። የተካሄደው ምርጫ የማሟያ ሲሆን አቶ አምሳሉ ለአንድ ዓመት የሚያገለግሉ ይሆናል። የተመረጡበትን አራት ዓመት ሳያጠናቅቁ ከኃላፊነት የለቀቁት የምክር ቤት አባል ፕሮ ተም ደስተን ዘፋነክን ተክተው ይሠራሉ። የአውሮራ ከተማ ምክር ቤት ከ37 ተወዳዳሪዎች መካከል ሦስት እጩዎችን ለመጨረሻ ዙር ውድድር አቅርቧል። ሦስቱ እጩዎች ዳንኤል ሌሞን፣ ጆናታን መክሚለን እና አምሳሉ ካሳው በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ ምልልስ ተደርጎላቸዋል። የአውሮራ ከተማ ከንቲባ ማይክ ኮፍማን ካቀረቧቸው እጩዎች መካከል እንደሆኑ አቶ አምሳሉ ተናግረዋል። ቃለ ምልልሱን ጨምሮ ከማኅበረሰቡ አስተያየት የመቀበልና ሌሎችም ሂደቶች ሁለት ወር ገደማ ወስደዋል። ድምጽ ሰጥተው አሸናፊውን የለዩትም የከተማዋ ምክር ቤት አባላት ናቸው። 'ዘ ዴንቨር ጋዜት' ባወጣው ዘገባ መሠረት፣ ከ10 የምክር ቤቱ አባላት 6ቱ በሰጡት ድጋፍ አቶ አምሳሉ አሸናፊ ሆነዋል። የተመረጡበትን አራት ዓመት ሳያጠናቅቁ ከኃላፊነት የለቀቁትን የምክር ቤት አባል ተክተው ለአንድ ዓመት ከሠሩ በኋላ በቀጣይ ምርጫ እ...