"የአሜሪካ ትራንስፖርት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ የገንዘብ ቅጣት አስተላለፈ" BBC.

 

ኦኦ።
 
"የአሜሪካ ትራንስፖርት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ የገንዘብ ቅጣት አስተላለፈ"
BBC.
"የዩናይትድ ስቴትስ ትራንስፖርት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ኢቲሀድ ኤርዌይስ ሕግ በመጣሳቸው በገንዘብ እንዲቀጡ ወስኗል።
ሚኒስቴሩ ባለፈው ሐሙስ ባወጣው መግለጫ መሠረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሜሪካው ዩናይትድ ኤርላይንስ መለያ (ኮድ) በመብረሩ 425 ሺህ ዶላር እንዲቀጣ ተወስኗል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶቹ ኤቲሀድ አየር መንገድ ደግሞ ጄትብሉ በተባለው የአሜሪካ አየር መንገድ መለያ ቁጥር በመብረሩ 400 ሺህ ዶላር ተቀጥቷል።
ሚኒስቴሩ በድረ-ገፁ ባወጣው መረጃ እንዳለው ሁለቱ አየር መንገዶች፤ በፌዴራል አቪዬሽን ባለሥልጣን (ኤፍኤኤ) የአሜሪካ አየር መንገዶች እንዳይበሩ በተከለከሉባቸው የአየር ክልሎች በመብረራቸው ነው ሕግ የጣሱት።
ሁለቱ አየር መንገዶች ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸውም ተዘግቧል።
አቪዬሽን ኮንሲዩመር ፕሮቴክሽን የተባለው የዩናይትድ ስቴትስ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ቢሮ ባደረገው ምርመራ ከአውሮፓውያኑ የካቲት 2020 እስካ ታኅሣሥ 2022 ባለው ጊዜ ነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጥፋቱን ፈፅሟል የተባለው።
በዚህ ጊዜ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዩናይትድ ኤርላይንስን ኮድ ተጠቅሞ ከኢትዮጵያ ጂቡቲ በርካታ በረራዎችን አድርጓል፤ ይህ የአየር ክልል ደግሞ የአሜሪካ አየር መንገዶች እንዳይበሩበት በፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር ክልከላ የተደረገበት ነው ይላል።
የአፍሪካ ግዙፉ አየር መንገድ ይህንን ድርጊት የፈፀመው ከዩናይትድ ስቴትስ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ፈቃድ ውጭ መሆኑን መግለጫው ያትታል።
ቅጣቱን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢቢሲ ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።"

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።