ልጥፎች

ቸኮለ።

ምስል
        አሳዛኝ ክስተት። ለቤተሰብ መጽናናትን እመኛለሁኝ። እንዲህ ዓይነት ህልፈት ሰቅጣጭ ነው። ነፍስ ይማር። ቸኮለ። አበባ እንዲህ በጥዋቱ ሲረግፍ ሃዘኑ መራራ ነው። ወጣትነት ተስፋው ምኞቱ በአጭር ተቀጬ። ሥርጉ13/03/2014

ማህበራዊ ሚዲያ አጽናኝ ተቋም ነው። Die Soziale Medien sind ein Trost Institution. Die Akzeptanz zu akzeptieren ist die Kunst, weise zu leben.

ምስል

ዘለግ ያለ ሙግት ከዶር ገዱ አንዳርጋቸው ጋር። ዕውን ዶር ገዱ አንዳርጋቸው ጠሚር አብይ አህመድን ጠቅላይ ሚር ከመሆናቸው በፊት #አያውቋቸውም ነበርን? ኮሚኩ ድራማ። ተያያዥ ጉዳዮችንም አነሳለሁኝ። የእሳቸውን ጉዳይም በዝምታ ነበር ስታደም የባጀሁት። ዛሬ ግን ይደባበስ። በእኔ ቤት እንክህ እንክህ አይታሰብም እና።

ምስል
  ዕውን ዶር ገዱ አንዳርጋቸው ጠሚር አብይ አህመድን ጠቅላይ ሚር ከመሆናቸው በፊት #አያውቋቸውም ነበርን? ኮሚኩ ድራማ። ተያያዥ ጉዳዮችንም አነሳለሁኝ። የእሳቸውን ጉዳይም በዝምታ ነበር ስታደም የባጀሁት። ዛሬ ግን ይደባበስ። በእኔ ቤት እንክህ እንክህ አይታሰብም እና።    "አቤቱ አድነኝ፤ ደግ ሰውአልቋልና፥ ከሰው ልጆችም መተማመን ጎድሏልና።" (መዝሙር ፲፩ ቁጥር ፩)     https://www.youtube.com/watch?v=maffafwButk Anchor Media '' ትልቁ ጥፋታችን ስልጣኑን ለአብይ አህመድ መስጠታችን ነው።'' ዶ/ር ገዱ አንዳርጋቸው   እንዴት ዋላችሁ አመሻችሁም ማህበረ ቅንነት። ደህና ናችሁ ወይ????    ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን በቀደመው ጊዜ የአማራ ክልልን በቁንጮነት ይመሩ ከነበሩት፤ "በሱሴ" ኦሮማራ ዘመን ቲም መሪነት፤ ቀን ቀና ሲልም የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ የነበሩት፤ ቀን ደፋ ሲልም የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ የደህንነት አማካሪ የነበሩት፤ ቀን ሲያነክስም ከሁሉም የሥልጣን ኃላፊነቶች ጋር ፍች የፈፀሙት ዶር ገዱ አንዳርጋቸው ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ክፍል ፩ አዳመጥኩት። ክፍል ሁለት መጠበቅ አላስፈለገኝም። ሳዳምጣቸው ነውና የባጀሁት። አዲስ ነገር የለውም።    ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን አቅም ባለው ሁኔታ አልሞገታቸውም። ምክንያት እሱ #ተስፋ ለሚያደርግበት አዲስ የለውጥ ዋዜማ አጓጓዥ በመንግሥት ሥርዓት ውስጥ ጠቀም ያለ ልምድ ያላቸውን፤ በውጭ የዲፕሎማቱ መድረክም ከሁሉም የተሻለ አጋጣሚ ተፈጥሮላቸው ከነበሩ ፖለቲከኛ የሚገኘውን ተመክሮ ሥራ ላይ ለማዋል ታስቦ ይመስላል ውይይቱ #የቤተ - #ዘመድ ዓይነት ይመስል ነበር - ለእኔ።   ዶር ገዱ ...

የህወሃት መራሹ የኢህአዴግ መኮነን ሜጄ አበበ ተ/ ኃይማኖት ኢትዮኤርትራን በሚመለከት ያነሱት ሃሳብ በሳል ዕይታ ነው።

  የህወሃት መራሹ የኢህአዴግ መኮነን ሜጄ አበበ ተ/ ኃይማኖት ያነሱት ሃሳብ በሳል ዕይታ ነው።    "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   ማህበረ ቅንነት እንዴት አደራችሁልኝ? እምዬ ኢትዮጵያስ? አባ ቅንዬ አማራስ እንዴት ናችሁ። ከሪፖርተር ያገኜሁት የህወሃት መራሹ የኢህአዴጉ መኮነን ሜ/ጄ አበበ ተ/ ኃይማኖት ብሄራዊ፤ አህጉራዊ፤ ግሎባል ሁኔታወችን ያገናዘበ #በሳል ዕይታ በሚመለከት በዝምታ ባጅቼ፦ ግን እኔ አስቀድሜ የፃፍኩበት ቢሆንም፤ ሃሳቤን፦ ዕይታዬን የሚያጠናክርልኝ ስለሆነ ለሪፈረንስ ይረዳ ዘንድ ሙሉው መንፈስ ከሥር ይገኛል የሪፖርተር ዘገባ።   ኢትዮጵያ እንዲህ ዓይነት በሳል ዕይታን፤ አስቀድመው ማዬት የሚችሉ ሊቃናት ያስፈልጓታል። ሰሚ ከተገኜ። እኔ በፌድራሉ እና በህወሃት ጦርነትም ጉዳቱን ከመዘገብ ውጪ ምንም አቅም አላዋጣሁም። ለአማራ ታጋዮችም አታበረታቱ፦ ትርፍ የለውም ብዬ ሞግቻለሁኝ።    የሆነ ሆኖ ከዬትኛውም ዞግ ይሁን መንፈሱ ጤናማ፤ መጪውን ዕድል የሚወስኑ ጉዳዮችን በአሰተውሎት የሚያነብ፤ የሚተረጉም እንዲህ #የሚያመሳጥር አቅም ያለው ዕይታ #ሊደመጥ ይገባል። ለጤነኛ ኃሳብ ድንበር እና ወሰን አበጅቶ ዕቀባ ማድረግ ብልህነት አይደለም።   ከቀደመው አሳቤ እማክልበት እኔ ስፈራ የነበረው የኔቶ እና የራሽያ ፍጥጫን ነበር። ሦስተኛ ዓለም ጦርነትን አማጭ ይሆናል ብዬ ስሰጋ የነበርኩት። አሁን ተመስገን ነው። ፍጥጫው ቢኖርም ውጥረቱን ሊያመጣጥን ወይንም ሊመክት የሚችል አቅም አለ። #ትራንፒዝም ። በሌላ በኩል ይህ የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ጉዳይ መነሻው ወደብ፤ የባህር በር የይገባኛል ጉዳይ ይምሰል እንጂ፦ በውስጡ ብዙ የታመቁ፤ #የታመሉም ፍላጎቶች አሉበት። ይህን የአቶ ሽመልስ አብዲሳን ...