ልጥፎች

Don't kill knowledge Don't kill wisdom. 12.02.2025

ምስል
« #Healing Hands Should Never Be Silenced by Guns.” « #Protect Physicians, Protect Humanity.” « # ሀኪም ህይወት እያተረፈ ፣ህይወቱን መነጠቅ የለበትም » « #Protect Physicians, Protect the Right to Heal.” « #No Physician Should be killed While Saving Others.” ! « #Stop the Violence Against Those Who Heal.” « #Physicians Deserve Safety, Not Bullets.” « #Stop Killing the Healers of Humanity.” « #Protect the Hands That Heal, Not the Hands That Kill.” “ #No Conflict Justifies the Killing of a Physician.” “ #Defend the defenders of health.” « #Doctors need protection not persecution.”  

ዕውቀት አትግደሉ። ዊዝደም አትግደሉ። "In Memoriam Dr Andualem Dagne" (1988 - 2025)

ምስል
  ·        ዕውቀት አትግደሉ። ዊዝደም አትግደሉ። In Memoriam: Dr. Andualem Dagne (1988-2025)              ቅንብር - ማዕደኛ።   "የቤትህ ቅናት በላኝ።" (1)    የሰማዕቱ፤ ምሩቁ ረ/ ፕሮፌሰር ዶር. አንዷአለም ዳኜ ድምጽ፤ (2)    የባህርዳር ዩንቨርስቲ ድምጽ፤     (3)    የቢቢሲ ዘገባ፤ https://www.bbc.com/amharic/articles/c8r51pk1m5do «የሕክምና ማኅበረሰቡን ያስደነገጠው የዶ / ር አንዱዓለም ዳኜ ግድያ»   (4)    አድምጬ የማልጠግባቸው የዶር ወዳጄነህ ይስማኽነ የሚሊዮኖች ድምጽ፤ (5)      ከፌስቡክ ጓደኞቼ ያገኜኋቸው መሳጭ ፎቶወች - ለዝክረነት፤ (6)    ከሁለገቡ የጥበብ ቀንዲል ከአርቲስት ሰውመሆን ይስማው «የፍቅር እስከ መቃብር» ዕንቁ ተውኔት ክሊፕ ዜማ   - በስሱ፤ (7)      የሥርጉትሻ አጭር ግጥም ተካተዋል። ውስጤን በሃዘን በናጠው የጭካኔ ማዕበል ብዙ ጽፌያለሁኝ፤ እንዳይበዛ በማሰብ ቆራጣዋ ሥነ - ግጥም ብቻ ቀርቧል። ሃዘኑ የሁላችንም ነው፤ ኢትዮጵያን፤ አህጉራችን ጨምሮ፤ ሁላችንንም እግዚአብሄር ያጽናን። አሜን። አልማዞቻችነን ፈጣሪ ይጠብቅልን። አሜን። ·        ሁሉንም መረጃወች በስብስብ...

ቻትጂፒቲን 'ያስናቀው' ዲፕሲክ እንዴት በኢትዮጵያ ቋንቋዎች 'ጎበዝ' ሆነ? ዓለምን ያስደነገጠበት ምሥጢርስ ምንድን ነው? BBC

    ቻትጂፒቲን 'ያስናቀው' ዲፕሲክ እንዴት በኢትዮጵያ ቋንቋዎች 'ጎበዝ' ሆነ? ዓለምን ያስደነገጠበት ምሥጢርስ ምንድን ነው? https://www.bbc.com/amharic/articles/cn0190den9lo   31 ጥር 2025 የአሜሪካው የቴክኖሎጂ መንደር ሲልከን ቫሊ ከዚህ በኋላ 'ማንም አይደርስብንም' የሚል አይመስልም። ዲፕሲክ 'ድምጹን አጥፍቶ' በድንገት ገበያውን አናውጦታል። ከሳምንታት በፊት ነበር የቻይናው ሰው ሠራሽ አስተውሎት (አርቴፍሻል ኢንተለጀንስ) ተቋም ዲፕሲክ-አር1 (DeepSeek-R1) ቻትቦትን የለቀቀው። መተግበሪያው ለአገልግሎት ከበቃ በኋላ ማሻሻያ ተደርጎበት ባለንበት ሳምንት ያልተጠበቀ የቴክኖሎጂ 'አብዮት' ፈንድቷል። የአሜሪካን የስቶክ ገበያ የሚቆጣጠሩት ግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋማት ገበያቸው ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ አሽቆልቁሏል። ለምዕራባውያን የቴክኖሎጂ ተቋማት ቻትቦቱ ከቻይና ብቅ ማለቱ የበለጠ አስደንግጧቸዋል፤ አስፈርቷቸዋልም። የቻትቦቱ ፈጣሪ ቻይናዊው ሊያንግ ዌንፌግ እምብዛም ቃለ ምልልስ ባይሰጥም፣ ባለፈው ዓመት ባደረገው አንድ ቃለ ምልልስ "ቻይና በኤአይ ሁሌም ተከታይ አትሆንም" ማለቱ ተዘግቧል። ከሁለት ዓመት በፊት ዓለምን ጉድ ያስባለው ቻትጂፒቲ ቀንደኛ ተቀናቃኝ ገጥሞታል። ከቻትጂፒቲ ጀርባ ያለውን ኦፕንኤአይ የሚመራው ሳም አልትማን ሳይቀር በዲፕሲክ ተገርሟል። "በጣም አስደናቂ ሞዴል ነው። በተለይ ደግሞ ከወጣበት ገንዘብ አንጻር" ብሏል። በሌላ በኩል ኦፕንኤአይ "ቻይና ያሉ ተፎካካሪዎቼ የእኔን መተግበሪያ ተጠቅመው የተሻሻለ መተግበሪያ ሠርተዋል" ሲል ቅሬታውን አሰምቷል። የሰው ሠራሽ አስተውሎት ዘርፉን የሚመሩ ተቋማት ዓለ...