ዕውቀት አትግደሉ። ዊዝደም አትግደሉ። "In Memoriam Dr Andualem Dagne" (1988 - 2025)

 

·       ዕውቀት አትግደሉ። ዊዝደም አትግደሉ። In Memoriam: Dr. Andualem Dagne (1988-2025)

             ቅንብር - ማዕደኛ።

 

"የቤትህ ቅናት በላኝ።"

(1)   የሰማዕቱ፤ ምሩቁ ረ/ ፕሮፌሰር ዶር. አንዷአለም ዳኜ ድምጽ፤

(2)   የባህርዳር ዩንቨርስቲ ድምጽ፤   

(3)   የቢቢሲ ዘገባ፤

https://www.bbc.com/amharic/articles/c8r51pk1m5do

«የሕክምና ማኅበረሰቡን ያስደነገጠው የዶ/ አንዱዓለም ዳኜ ግድያ»

 

(4)   አድምጬ የማልጠግባቸው የዶር ወዳጄነህ ይስማኽነ የሚሊዮኖች ድምጽ፤

(5)    ከፌስቡክ ጓደኞቼ ያገኜኋቸው መሳጭ ፎቶወች - ለዝክረነት፤

(6)   ከሁለገቡ የጥበብ ቀንዲል ከአርቲስት ሰውመሆን ይስማው «የፍቅር እስከ መቃብር» ዕንቁ ተውኔት ክሊፕ ዜማ  - በስሱ፤

(7)    የሥርጉትሻ አጭር ግጥም ተካተዋል። ውስጤን በሃዘን በናጠው የጭካኔ ማዕበል ብዙ ጽፌያለሁኝ፤ እንዳይበዛ በማሰብ ቆራጣዋ ሥነ - ግጥም ብቻ ቀርቧል። ሃዘኑ የሁላችንም ነው፤ ኢትዮጵያን፤ አህጉራችን ጨምሮ፤ ሁላችንንም እግዚአብሄር ያጽናን። አሜን። አልማዞቻችነን ፈጣሪ ይጠብቅልን። አሜን።

·       ሁሉንም መረጃወች በስብስብ መልክ «#መራራ ስንብት። እንደ አልባሌ #ዕውቀት ለባሩድ??? #ልቅና ለበቀል??? ከሚለው መጣጥፌ ሥር ታገኙታላችሁ። (ፌስቡኬ፤ ኤክስ አካውንቴ፤ ብሎጌ፤ በዝክረ - ፎቶ እና በድምጽ የተራውን ዩቱብ ቻናሌ ላይ ይገኛል።)»

 https://www.youtube.com/watch?v=1aPYMMwEapI

 

ዕውቀት አትግደሉ። ዊዝደም አትግደሉ። "In Memoriam Dr Andualem Dagne" (1988 - 2025)

·       የቀረኝ መረጃውን ለሚመለከተው አካል ማድረስ ብቻ ነው። ቅዱስ ሩፋኤላውያን እየታደኑ ሲገደሉ የጤና ግድያ ዘመቻ፤ የዊዝደም ገደላ ዘመቻ ነውና ብዕር በሰላማዊ መንገድ ሊታገል ይገባል። ውስጥ ሲራቆት ዝምታ ይከረፋልና።

·       እያሰገረ የሚመጣውን የዕውቀት ግድያ፤ የአማራ ህዝብን የቤተሰብ ብተና፤ የአማራ ልጅ ትምህር ምን ያደርግልኛል? ይል ዘንድ ሙሉ 6 ዐመት የቀጠለው ትምህርት ላይ ያነጣጠረ ዲስክርምኔሽን፤ በቀላዊው ስልቱ ሊበጣጠስ ይገባል። ከውስጣችን እንሰበው ከ20/30 ዓመታት በኋላ። ድንቁርና ይናኛል። ፕሮጀክቱ ይህ ነው።

·       በአማራ ክልል ከማዕከላዊ ጎንደር 80ሺህ ህዝብ ሲፈናቀል፤ ልጆች ሙሉ ዐመቱን አልተማሩም ነበር። ከሃረመያ ዩንቨርስቲ የቀጠለው ማፈናቀል 3,000 የዩንቨርስቲ ተማሪወች ተፈናቅለው ነበር፤ በደንቢደሎ 18 ተማሪወች እገታ ስወራ እና በኦሮምያ ክልል ብቻ 45,000 ሺህ የዩንቨርስቲ ተማሪወች በተጨማሪነት መፈናቀላቸው በወቅቱ ተዘግቧል። በአማራ ክልል በጎጃም 12,993 የ12ኛ ክፍል ተማሪወች የፈተና እገዳ እስከ 5,000000 ተማሪ በጦርነት ሰበብ ከመደበኛ ትምህርት ውጪ መሆን፤ ውስጥ ውስጡን ደግሞ ቀድመው የተማሩ የአማራ ሊሂቃን ምንጠራ - በጭካኔ መግደል - መረሸን፤ እናትነትን አስመንኗል። አዲስ ቡቃያ እንዳይወጣ መቀጣጫ ማበጀት ብቻ ሳይሆን፤ ያሰበለውንም ምንጠራ። ሚዛን ሊወጣለት የማይችል የዕውቀት ፀርነት። ዓለም አልፋበት የማታውቀው በትምህርት ላይ ያነጣጠረ ንጹህ ጆኖሳይድ፤

·       ይህ እንግዲህ በመላ ኦሮምያ፤ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የኗሪ አማራወች የጀምላ ግድያ፥ ስወራ፥ እገታ፤ ማፈናቀል ከአማራ ልጆች የመማር ዕድል መጨንገፍ ጋር ሲይካተት፤ ፓን አፍሪካኒዝምን፤ ግሎባሊዝምን ያቀፈ ሰላማዊ ንቅናቄ ይጠይቃል። መከራው በጭልፋ ተሳትፎ የሚሆን አይደለም።

 

ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።

ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።

ኑሩልኝ። አሜን።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።

 የሃዘን ዳርቻ ያድርግልን። አሜን።

ሥርጉተ©ሥላሴ።

Sergute©Selassie

11.02.2025

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?