የአቶ ታየ ደንዳአ (#ታየይዚም) #የግሉኮስ (ትንፋሽ ቀጥል) ስርጭት ዕውነትን #ያፈልቃል።

 

• የአቶ ታየ ደንዳአ (#ታየይዚም) #የግሉኮስ (ትንፋሽ ቀጥል) ስርጭት ዕውነትን #ያፈልቃል። ለትውልድም ፈውስ ይሆናል።
የዶር ሚልኬሳ ሚዳጋ ቃለ ምልልስ በሆርን ኮንቨርሴሽን በአስፈለገኝ ነጥብ ብቻ። ተጨመሪም ተያያዥ ጉዳዮችን አክላለሁኝ።
 
 "የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
ማህበረ ቅንነት አብይዝምን በምዕራፍ ከፋፍየ ነው የተከታተልኩት። እንሆ ምዕራፍ ፲፭ በአብይዝም በራሱ የውስጥ ጠረኖች በአካሎቹ ምስክርነት ይጠናቀቃል። በጣም ዘለግ ባሉ ጹሁፎች ነው አብረን ምዕራፍ ፲፭ የቆየነው። እግዚአብሄር ይመስገን። አሜን። ጃዋሪዝም በሚገባ ተሞግቶበታል። ጥሞና ጊዜውን የጃዋርዚምን አድንቄ ወደ ፖለቲካው መለስ ሲል ግን በሙግት ነበር አቀባበል ያደረኩልት።
 
ከፍ ብ ሎ መታየት እራስ ባበጁት፤ በተረጉሙት የላቀ ተግባር እንጂ ቅኖች በእግዚአብሄር፤ በአላህ አቅም እርዳታ እጅግ ጥልቅ በሆነ ሚስጢር የተከወነን የዘመን ስኬት ደራሽነት፤ ቅጽበታዊነት፤ የመረረ ጥላቻ፤ ግብታዊነት እንዳልጎበኜው በሚገባ በህይወት እያለሁ መግለጥ ስላለብኝ ነበር "ካልኩሌተሩ፤ ሞተሩ አንተ አይደለህም" ማለት ይገባ ስለነበረ ጃዋሪዝም የተሞገተው። 
 
ይህን ካለ አቶ ጃዋር መሃመድ (ሃጂ )መንፈቅ ሊሆነው ነው። ከቻለ ለምን ይህን ያህል ጊዜ ፈጀበት ሜዳውም ፈረሱም ተሰናድቶ እየጠበቀው አይደል? ካለስኩን ዊዝደም የሚሳካ ህልም ኑሮ አያውቅም። ለዛውም የመንግሥት ለውጥ። ወደፊትም አይኖርም። በዊዝደም በተበጀች ፈላስፊት ኢትዮጵያ ላይ ተቀምጦ ሲረማመዱበት የነበሩት ማህበረ ኦነጎች ኢትዮጵያዊነት ልቅናውም ልዕልናውም በዘመናችን ዲካ የለሽ እንደሆን ተከታታይነት እንዳለውም ማመሳጠር ይገባ ስለነበር ነው የተሞገተው።
 
በሚዲያ እንደ ቄጤማ የሚነሰነስ ክብር እና ሙገሳ ያላበቀለን ሰብዕናወች፦ በሳይለንት ማጆሪቲው ውስጥ መኖራችን በልኩ መታወቅ ስላለበት ጀዋሪዝም ተከብሮ ተሞገተ። ኮርን ኮንቨርሴሽን ስለቀጣይ ጉዞ አቶ ታየ ምን አመላከተ? ያላሰበበት አጀንዳ ነበር። በተገባው ልክ የምስክርነቱን ሚስጢራዊ ይዘት ተነቅሶ ስለተፃፈ አሁን ሁለት ፕሮግራም ከዶር ሚልኬሳ ሚደጋ ጋር ሠራበት።
 
አዲስ ኮንፓስ ሚዲያም ታዬየዚም የሰሞናት አጀንዳ ሆኖ እንደሚያከትም ነበር ግምቱ። እእ። በአማራ ጥላቻ ቤተኛ የሆነው ሁሉ፤ የአማራ ሊቃናት ወደፊት ሲመጡ ለሚባቡ ሁሉ እማትንቁት፤ እማታቃልሉት ልቅና በልዕልና ከአማራ ሊሂቃንም እንዳለ ዘመን ይኽው እንዲህ ያመሳጥራል። የማስተዋል ክህሎት ላለው። 
 
የኔወቹ የፔጄ ታዳሚወች ቀጣዩ ምዕራፍ ፲፮ እርጋታ እና ማስተዋል፤ ጥሞና እና ሰዋዊነት + ተፈጥሯዊነት፤ ሚዛናዊነት- በርጋታ - ኢትዮጵያ እና የፖለቲካ ኢሊቶቿ ምን እና ምን እንደሆኑ፦ ለውስጤ ተደራሽ የሚሆኑትን ብቻ ጊዜ ሰጥቼ እማዳምጣቸውን፤ በሰላማዊ የብዕር ቅን ሙግት ብቻ ይቀጥላል። የሚመሰገኑትም ይመሰገናሉ።
 
እኔ ከሌላው የሚዲያም፤ የፖለቲካም ሰብዕና የምለየው የምሰስተው ምንም አቅም ስሌለኝ ነው። ለሚከበረው፤ ለተገበረ እመሰክራለሁ። ግን አሽኮኮ አድርገን ከእስር ያስፈታናቸው፤ ለሽልማትም ያበቃናቸው ግን የማይደረስባቸው ተራራ ናቸው። በቃላቸው ስለ አንድ ዕንቁ ኢትዮጵያዊ ቀርቶ ስለ እራሷም ኢትዮጵያ አጀንዳችን አይደለችም በአደባባይ ሲሉ ለግሎባሉ ማህበረሰብ ሰማን። በዓመቱ ደግሞ የአድዋ ድል አከባበር የክብር እንግዳ??? 
 
የሆነ ሆኖ ቀጣዩ ምዕራፍ ፲፮ ………
 
የታሰሩ ወገኖቼ ይፈቱ!
ፖለቲካዊ ሴራ ይቁም!
ጥላቻ ይወገድ - ከምድራችን! ይቅርታ እና ምህረት ይለምልም!
ጦርነት በአገር ውስጥም በውጭም ፈጽሞ አያስፈልገነም!
ኢትዮጵያኒዝም - አይገለል!
ቅንነት ይመራን ዘንድ እንፍቀድ!
 
የትኛውንም ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ መደገፍም፤ አብሮ መሥራት፤ ማመስገን፤ በአንፃሩም መሞገትም መብት ስለመሆናቸው እንቀበል!
ወዘተ በሚሉ በኽረ ጉዳዮች ምዕራፍ ፲፮ ከጥሞና መልስ እቀጥላለሁኝ። ወጣትነቴም ስለተጠናቀቀ በልኩ መሆን ይገባል። በሰጨኝ ዋዜማ ላይ ነበር ለሁለት ዓመታት። አሁን ሙሉ ለሙሉ ይሰናበታል። እረፍት፤ ጥሞና፥ በቂ የማድመጥ ጊዜ ያስፈልጋል። ይህን በየምዕራፎቹ አድርጊያለሁኝ። 
 
በእኔ የትግል አሻራ ትርጉም የሚሰጡኝ አዳዲስ ክስተቶች ሲፈጠሩ ነው የጀመርኩት ምዕራፍ ተጠናቆ አዲስ ምዕራፍ የሚታጨው። የአቶ ታየ የሰሞናቱ ገሃዳዊ በሰኔ መታየት ለገዢው ብልጽግና አዲስ ምዕራፍ ነው። ክስተትም ነው ለእኔ።
 
…… በጥልቀት ሳጠናቸው የነበሩ፤ የፃፍኩባቸው፤ የሞገትኩባቸው በኽረ አመክንዮወች ውበት ጨምሮልኛል። ስለሆነም ነባሩን ምዕራፍ ፲፭ ተጠናቆ ምዕራፍ ፲፮ ለመጀመር መጠሞን ግድ ሆነ። በኢትዮጵያ ፖለቲካ የጥሞና ጊዜ የለም። ተንደርድሮ ወደ ሥራ ነው። ስኬቱም መንደርደር የሆነው ለዚህ ነው። 
 
ከአቶ ጃዋር መሃመድ (ሃጂ) በስተቀር ማንም የኢትዮጵያ ፖለቲከኛ ይሁን የሚዲያ ሰው ከእስር ሲፈታ፤ ከበረከተ ተግባር በኋላም ጥሞና አስበውት አያውቁም። ለዚህ ነው መውደቅ ብቻ ስንቅ የሆነው። ሲነግሯቸውም አይሰሙም። ይንቁናል። ለዘመናት የህወሃት እስር በማን ቁልፍ ፍቺ እንዳገኜ አላህ እግዚአብሄር ያውቀዋል። ሙሉ ፲፭ ዓመት የታገለልህን የአንድ ደቂቃ ጆሮ ለመስጠት ጋዳ ነው። ትዕግሥት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል። ክውን ሽክፍ ጥንቅቅ ብለን የተቀመጥነውም ለዚህ ነው።
 
የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ከዲሲ ይሁን ከአውሮፓ ትጋታቸው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው ወዲያውኑ በፖለቲካ ጉዳይ ቤታቸው ሳይገቡ ወደ ቢሮ፤ ከእስር ሲፈቱም እዛው እስር ቤቱ ደጃፍ ሆነው ከፖለቲካዊ ተግባር ጋር ይለካለካሉ። የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ሆኑ የሚዲያ ሰወች ያደክማሉ። አሁን በተከታታይ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን በግለትም፤ በቅርበትም በአካል ፊት ለፊት እያወያዩ ነው። ቸር ፐርሰኑ እሳቸው ናቸው። ሲያጠናቅቁ ጥሞና የለም። ምን አልባትም በረራ። 
 
በእኔ ህይወት ግን እንደዛ አይደለም። እራሴን እማርምበት፤ እምገመግምበት፤ እምማርበትም የጊዜ ሰሌዳ አለው። ፋታ፤ ትንፋሽ መሰብሰብ የዮጋ ትምህርት ምሰሶ ነው። ያው እኔ የተለያዩ ሙያወች ዲስፕሊን ምርኮኛ ስለሆንኩ ዮጋ፤ ዳንስ፤ ቲያትር ሙዚቃ ኮርሶችን በስሱ ሞካክሬያቸዋለሁኝ። የቲያትር ፕለይ አፃፃፍ ኢትዮጵያ እያለሁም ኮርሱን ወስጄ ነበር። ድርጊቱን በእምየ ሲዊዝ ጸደቀ። አንድ ቀን ፖስት አደርግላችሁ ይሆናል። 
 
የሆነ ሆኖ የዮጋ እርጋታ ይመስጠኛል። የመመሰጥ አርቱ እና የቲሙ ንጹህ ግንኙነት ይማርከኛል። እሱን መንገድ እወደዋለሁኝ። ስለሆነም በአዲሱ ምዕራፍ ከጥሞና በኋላ በምዕራፍ ፲፮ እስክንገናኝ ድረስ ማህበረ ቅንነት ደህና ሁኑልኝ። አሜን። ምዕራፍ ፲፭ በዚህ የታየይዚም ግሉኮስ ዕርዕሰ ጉዳይ ይጠናቀቃል።
 
ተዚህ ላይ ተዋህዶ የሱባኤ ጊዜ አላት። ለዛ የሚመጥን አቅም ስለለኝ ነው እሱን የምዘለው። እንጂ የእምየ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅድስና ዶግማ፤ ብሩክ ቀኖና እዮራዊ መሆኑን አጥቼው አይደለም። ኑሬበታለሁም። የተፈጠርኩበት ቤተ - መላከብርኃናትም ይህን ያጠየቀ የቅኔ ቤት ነው። የቤተሰባችን ትውፊት እና ትሩፋት "መሬትን ቀስ አድርጋችሁ እርገጧት" ነው ይትባህሉ፤ የልደትም ለነድያን ድንኳን ተጥሎ ፆም ይፈቱ ዘንድ በብርንዶ፤ በጥብስ ርህርህናን፤ አዛኝነትን፤ አጽናኝነት በተግባር አይቼ ነው ያደኩት። 
 
ወደ ቀደመው የምዕራፍ ፲፭ የማጠናቀቂያ ጹሁፌ ሃሳብ ስመለስ ትንሽ #ከበድበድ ያለ ጊዜ እየመጣ ያለ ይመስለኛል። ነው አላልኩም። ይመስለኛል ነው። የአማራ ቀሪ ሊቃናት ሙሁራኑ ተራቸውን እየጠበቁ ኢመርጀንሲ ሩም እንዳሉ ተሰማኝ። ፈጣሪ // አላህ ይጠብቃቸው። አሜን። እነሱም ይህ በሰፈር አስቦ የመለያየት፤ አቅምን ባሊህ ያለማለት፤ የማግለል ባህሪያቸው ፈጣሪ ይመልሳቸው። አሜን። ከህወሃት ጋር በውህደት የሰራ፤ ከኦነግ ጋር በውስጥነት ማህበረተኛን ሲያደንቁ፤ ሲያከብሩ የራሳቸውን ግርማ እና ሞገስ እንዳላይህ ብለውም ነው። ለዚህ ነው ስኬቱ ሰማይ ደጅ የሆነው። ተስፋውም እንዲሁ ………
 
"ጊዜውን እስክታገኝ ድረስ ነገርህን ሠውር፥ ብዙ ሰወች ጥበብህን ይናገራሉ።"
(መጽሐፈ ሲራክ ፩ ቁጥር፳፫) 
 
EMS "የታየ ደንድአ #ኑዛዜ" የሚል እርዕስ ሰጥቶ አይቻለሁኝ። እንደምን ይህን ማለት እንዳስቻላቸው ባይገባኝም፤ ለእኔ "ኑዛዜ" አይደለም። EMS ያሰበበት ዕርዕስም አይመስለኝም። የአቶ ታየ ደንድአ መግለጫ ከኑዛዜ ጋር ንክኬ የሌለው #ንጥር ምስክርነት ነው ብየ ነው እማምነው። በተጨማሪ የአንድ የፖለቲካ ድርጅት የትውልድ ተስፋነት ምሰሶወች ጥንቃቄ እንደሚያስፈልጋቸውም ጽንሰ ሃሳቡ የገለፃው ያስረዳል። እኔ በአንድ ወቅት ኦሮማራ እንደጀመረ የአቦይ ንዛዜ ብየ ጽፌ ነበር።
 
 የዛ ጭብጥ አቅምን ለዘመኑ ፖለቲካ ባህሬ መሸለም የተገባ አይመስለኝም። እራስን፦ መላ ቤተሰብን፦ ኑሮን፤ ድሎትን፤ የአገልግሎት ዘመንን፤ የተጋድሎ ውድ ሰብዕና ለሰማዕትነት የተሰጠበት ጉዳይ ኢኤምኤሶች ቅርቃር ውስጥ ወይንም ታዛ ላይ ነው የወሸቁት። ያሳዝናል። ቢሪያሙት ምኞቴ ነው። ዕርዕስ አቦሰጥ አይደለም። ዕርዕስ ፋስ ሊሆን ይችላል። ዕርዕስ አቅጣጫ ቀያሽ ሊሆን ይችላል። ዕርዕስ የሚሊዮኖች አዳኝም ሊሆን ይቻላል። ዕርዕስ መልካም ዕድል አመንጪም ሊሆን ይችላል። 
 
ስለዚህ የተለመደው ተለምዶ አዋጭ አይመስለኝም። ለጦርነት ጊዜ አወንታዊ ፕሮፖጋንዳ ሊያስፈልግ ይችላል። ለሰከነ የምዕራፍ ከፋች የዘመን የፖለቲካ ባህሬ ግን ፕሮፖጋንዳዊ ስልት አይረዳም። ፕሮፖጋንዳም፤ የዕርዕስ የአሰጣጥ ብልህነትም ኮርስ አላቸው። እራሱ የዕርዕሱ ቀለም አፃፃፍ በኢትዮጵያ ፖለቲካ፤ ማህበራዊ ህይወት ሚዲያ ላይ ጥንቃቄ ይሻል። ቀይ ቀለም የደም፤ የአደጋ ጊዜ ጡሩንባ ሊሆን ይችላል። እርዕስ የሚፃፍባቸው የቀለማት ድምጽም ጥንቃቄ ያስፈልጋቸዋል እያልኩ ነው። 
 
ወደ ቀደመው ስመለስ "ሚስጢር ሆኖ እንዳይቀር" ሲሉ አቶ ታየ ደንድአ እኮ ልንገልጸው የማንችል የፋክት ፕላኔት ነው - ለእኔ። ኢትዮጵያ ብለህ፤ አፋር ካልክ፤ ጋንቤላ ብለህ ኢትዮጵያ ካልክ፤ ኢትዮጵያ ብለህ #አማራ የማትልበት ዘመን መወጠኑ እጅግ አሳሳቢ የዘመን ግርሻ ነው። ሌላው "ኑዛዜ" የሚለው ኃይለ ቃል እጅግ ከባድ መቃብር ሲሆን #ሞርትም ነው። መራራ ስንብትን መናፈቅ ለምን? በዚህ መልክ የታየይዚምን ደፋር ጭብጥ ማኮሰስ ይሁን፤ ማግነን ወይንም ማግለል የተገባ አይመስለኝም። በፖለቲካ ድርጅት ተሳትፏቸው ለጋ ናቸው አቶ ታየ። ግን ብልጽግና ሰነዱ ላይ ያለው ጭብጥ ድርጊት ላይ የመዋል አቅሙ ዝበት መኖሩን ከውስጣቸው አሳዝኗቸዋል። 
 
ይህ ደግሞ በፖለቲካ ህይወት ውስጥ የሚገጥሙ የኢንትሪግ ናዳወችን ካለመልመድ የመነጬ ነው። የተቀበሉትን በቦታው ሲያጡት የሰጣችሁኝን ቆጥራችሁ አሳዩኝ ነው ጉዳዩ። ይህ ለገባው መንፈስ የተኖረበትን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ትብትብ የጎሼ ጉዞ የሚሞግት፤ እንዲጠራም የሚያግዝ ነው። ለራሱም ለብልጽግናም ጠቃሚ ቴትራሳይክል ነው። ብልጽግና ኢንፌክሽን እየናጠው ስለሆነ። ገና በለጋ ዕድሜው እንዳይሰናበት ታየይዚም ህይወቱን የብልጽግናን አብረው ኑረውበት መከፋታቸውን ገልጸው ዳገቶችን የሚያሳይ ሃሳብ አቅርበዋል።
 
በአቶ ታየ ደንዳ ቤት ሌላ የፖለቲካ ድርጅት ሥልጣኑን ቢይዝ በብልጽግና ያዩት ግዙፍ ግድፈቶች ላይከሰት እንደሚችል ገምተው ይሆናል። ነገር ግን ግርፋ ማሌሊታዊ፤ ስታሊናዊ፤ ማኦያዊ የሆኑት ሁሉ የኢትዮጵያን በትረ ሥልጣን ቢረከቡ አፈፃጸሙ ቢለያይ እንጅ #የደም ዓይነቱ ተመሳሳይ ነው። በግል፤ በነፃ ለምናገለግለው እኮ በአድማ ሲያዋክቡን ውለው ነው የሚያድሩት። ከዘመን ጋርም እርቀ ሰላም የላቸውም።
ሌላው ቀርቶ ከሶሻሊስቱ ርዕዮት ወጣን፤ ንኪኪ የለንም ቀኝ ወይንም ግራ ሊብራሊዝም መስመራችን ያሉት እኮ ተመልሰው እዛው ነው ተነክረው የሚገኙት።
 
 የሆነ ሆኖ ዕውነትን ፍለጋ፤ መርኽን ምራኝ ማለት እንደ "ኑዛዜ" ሊታይ አይገባም ባይ ነኝ። ትንሽ ጠለቅ ያሉ የፖለቲካ ቻሌንጆች ሲገጥሙ ለሚዲያ መክሰስ ከመቸኮል፤ ይህ የደጋፊ ሽሚያ፤ የሽልንግ ፋክክርን ተወት አድርጎ ጊዜ ሰጥ ዕድሎችን አገላብጦ ማየት እና ጥሞና ወስዶ መመርመር ይገባል። ስንት ጊዜ እንጨንግፍ???? ትውልድም ወጀብ በየጊዜው እየናጠው እስከመቼ? ለዛውም ለዚህ ቆራጣ የመኖር ኩንትራት። ሞትን ተሸክመን እየኖርን አንድ ቀን ለህዝብ ፍሰኃ መሆን አለመቻል?
 
ስለሆነም አቶ ታየ ደንድአ ቤታ ውስጥ ቁጭ ብለው በተረጋጋ መንፈስ፤ የሰከኑ ጭብጦችን ያነሱበት ሁነት " ኑዛዜ " በሚል ሊሸነገል የሚገባ ነው ብየ አላምንም። ከአገላለጽ ጀምሮ የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስትንፋስ ነክቷቸው የማያውቅቱን የገዘፋ የአገላለጽ ዘይቤወችን ነበር የተጠቀሙት። ከዚህ ቀደም ነቅሼ አውጥቼ ስለፃፍኩበት ወደዛ ልመለስ አልችልም። 
 
"ፖለቲካ ፍቅር አይደለም" "ሙስና ቀይ ምንጣፍ ተነጥፎለታል" "በሃሳብ ብልጽግና በድርጊት ብልግና" በጣም ጥልቀት ያላቸው፦ ገዢውን ብልጽግና ብቻ ሳይሆን ሆ! ብለን የተቀበልነውን ኦሮማራ እና ስኬቱን በአደብ ጥሞና እናደርግበት ዘንድ በኽረ ሃሳብ ነው ያቀረቡት። ሁላችንንም የሚሞግቱ ክስተታዊ ጭብጦችን ነበር ያነሱት። እንዲህ አቃለህ ወይንም አጣጥለህ የምታልፈው የስንዝሮ ጉዳይ አይመስለኝም። ይመለከተኛል የሚል ሁሉ ደግሞ ቢያደምጠው ምርጫየ ነው። 
 
#የታይዚም ነገረ ግሉኮስ። የአዳዲስ ትኩረት ትንፋሽ ቀጥል ቅየሳ።
 
ዘመን ግራ ተጋብቶት ባጀ። አጀንዳም ተጎምዶበት። ዘመን እሩሁ ተንጠልጥሎ ከራረመ- ትንፋሽ አጥሮት። ከአብይዝም ጋር አብሮ የቆየው፤ በኋላ መጣያ የሆነውም ከፋኝ ሲል ድምጡን አጥፍቶ መቀመጥ ወይ መሰደድ ውሳኔ ሆኖ ባጄ። አሳቸው ዘመን፥ አሳቻ ድርጊቶቹን እየቀለበ በአሳቻው መሪ አማካኝነትም ጉዞውን ቀጠለ።
 
 ድብብቆሹ - ድንቡልቡል ሲያሰኜውም - ጠፍጣጣ ሲለውም - ደፍጣጣ ሲሆንም፤ ወይንም ጠራጠሮ ወይንም ልሙጥ ሆኖ መነሻ እና መድረሻው ውል ጠፍቶ ብልጭ ያለች ትንፋሽ ከተገኜች ሙሉ አቅም በገፍ በጉጉት ሲፈስ ባጄ። 
 
እንሆ አቶ ታየ ደንድአ ግሎኮሱን እያደሉ ከዚህም፤ ከዚያም አቅም፤ ቁርጠኝነት አቅቶት የነበረው ትንፋሽ ተደላድሎ "#እኔም" ይህን፤ "እኛም" ያነን እናውቃለን በማለት የዘመኑን የፖለቲካ ባህሪ ዳፍንትነት ገለጥለጥ እያደረጉ ጧፍ መለኮስ ተጀማምሯል። በውነቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ባልቦላ አጀንዳ ቀያሽ አይደለም። ድግግሞሹ በበረከተ አጀንዳ ነው ተውሎ የሚታደረው። በእነዛው በለመድናቸው የፖለቲካ ተንታኞች እና ፖለቲከኞች። አድማጮቻችን እኛ እንደ ሽንብራ ቂጣ እየተገለባበጥን ይሰለቹናል አይባልም። ለአጀንዳ አልቦሹ ዘመን አጀንዳ ቀርጸውለታል አቶ ታዬ። አቅም መግበውለታል። ይህ የሚረዳው ……
 
1) ዕውነትን ፍለጋ የዕውነት ማህበርተኞች ይተጋሉ።
2) ክንብንብም ያሰኜው አሳቻው የዘመን እጮኞቹ መዝነው ልኩን እንዲያሳውቁት አዲስ ጎዳና ይከፈታል።
3) የሰው ህይወት የኢንሴክት ያህል በማይታይባት ፈላስፊት ኢትዮጵያ እና የፖለቲካ ሊቃናቶቿ ሳይታወቅባቸው ወልጋዳውን ጉዞ ስጥ ከሚሉት #ተግ ሊሉ ይችላሉ። ፈጣሪን ከተማጸኑም ከክፋ ሃሳባቸው ጋር ሊፋቱ ይችላሉ። ለእግዚአብሄር ምን ይሳነዋል? ለአላህ ምን ይከብደዋል? አይደገመኝ ጭካኔ፤ አረማዊነት ሊሉ ይችላሉ። በኢትዮጵያናችን ተፈጥሯዊነት እና ሰዋዊነት ሊጸድቁ ይችላሉ በፊርማ።
 
4) የታፈኑ ትንፋሾች እንደ ዶር ሚልኬሳ ሚደጋ መሰል ሰብዕናወች እራሳቸውን ወቅሰው መተንፈስ ይጀምራሉ። ፋክክሩም ይደራል። ላቂያ ካለ መለካካት ተፈጥሯዊ ነውና። የታየዚም መታየት በተለይ በአማራወች ለመደመጥ ጥቂት መንገድ መከፈት "እኔስ" የሚል ሁነት ፈጥሯል። አቶ ጃዋር መሃመድ (ሃጂ) ሲታሰር እሱን ለመሆን ልጅ አናንያ ባጉም ባጉም ሲል ነበር። ሌሎችም እንዲሁ።
 
የሆነ ሆኖ በደልን ከፍተን እንፈትሽ ዘንድ። ድንብልብል ያለብንን ዘመን በሰውኛ መንፈስ እንመረምር ዘንድ ነው #ግሉኮሱ የሚያስፈልገው ተዚህ ላይ ነው። ታየይዚም ሠራሽ ግሉኮስ ሥራውን በጥራት እና በብቃት #አና እያለው ነውና። "እኔም ይህን አውቃለሁ" በማለት ዕውነትን በልኩ ለልኩ መስጠት ለዘመኑ ይሁን ለትውልዱ ዕንቁ ስጦታ ነውና።
 
5) በኢትዮጵያ ፖለቲካ እንደ ባህል የተያዘው "የጥላቻ" ዶክተሪንም ዘመን በቃህ! ብሎ ሊያሰናብተው ይችላል።
6) በማናውቃቸው የአገራችን ቋንቋወች ያሉ ጭብጦች ተቀብረው እንዳይቀሩ አዲስ ትጉኃን ሊፈጠሩ ይችላሉ። እስከዛሬ በዘርፋ ያልተጉት ብቅ እያሉ ነው። ከ፯ ዓመታት መቀበር በኋላ። የአማራ ስቃይ??? የሆነ ሆኖ ተዘግይቶም ቢሆን ይህም ሌላ ዕድል ነው። ቋንቋውን እየቻሉ የተደበቁት ግን ኢትዮጵያ ታዝንባቸዋለች። በተለይ የአማራ ልጆች። ስቃይን ሴብ ማድረጊያ ነውና ልግመቱ። 
 
መዳንን ለማዳን መትጋት ብሄራዊ ግዴት ስለሆነ። የአቶ ታየ ደንድአ ቃለ - ምልልስ መነቃቃት እንደፈጠረም አስባለሁኝ። ሆርን ኮንቨርሴሽን የሚመሰገነው ተዚህ ላይ ነው። በስማ በለው፤ በስሚ ስሚ ሳይሆን ረጋ ባለ አጭር እና ግልጽ የአጠያየቅ ዘይቤ በአማርኛ ቋንቋ ለኦዲየንስ እኩል ተደራሽ ማድረጉ ያስመሰግነዋል።
 
#ጥቂት ተጨማሪ ሃሳብ።
 
ዶር ሚልኬሳ ሚደጋ ከሆርን ኮንቨርሴሽን ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ የአቶ ታየ ግሉኮስ አቅም ፈጥሮ፤ ነፍስ ዘርቶ፤ ነፍስ ለመታደግ መንገድ መጀመሩን አመላክቷል። 5 ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ፤ በጠቅላላም ጊዜው ስንት ጊዜ ታየ እንዳሉ እኔ የቁጥር ተማሪ ስላልሆንኩ ቁጠሩት እና ድረሱበት። "እሱም አንስቶኛል" ቤተ ታየ ነኝ ሲሉም ዶሩ አዳምጫለሁ። የታየይዝም ፊርማ የሚፈለግበት ጊዜ ሊመጣ ይሆን? የታይይዝም ትውልድ በኦሮምያ ይፈጠር ይሆን? ታየይዚም መታጫ ለመሆን ስለበቃ። የአቅሙ የመደመጥ ፍሰት የሚስጢር ባለውሉ አማራዬ! ዶር ሚልኬሳ ሚደጋ በዘመነ ኦሮማራ በአማራ ማስ ሚዲያ በቃለ ምልልሱ ቲም ከአዳመጥኳቸው በኋላ፦ ተከታትያቸው አላውቅም።
ተጨማሪ አቅም ለክህደት ፖለቲካ ማቃጠል አያስፈልግም ነበር።
 
 ኦሮሞራ የአማራ ስቃይ አምራች ሞተር ሆኖ ነው ያገኘሁት። እሳቸውም እኛን ተከታትለውን እንደማያውቁ ከገለፃቸው ተረድቻለሁ። "አብይን በዚህ ልክ የሞገተው የለም። አረመኔ ያለው የለም" ባይ ናቸው። ኢትዮጵያን ለመምራት አቅም የሚያዋጣ ሁሉ ያለውን የትግል ዘርፍ ሁሉ በጥሞና መከታተል ይገባል።
 
የኦህዴድ ጠቅልሎ ቤተ - መግሥት የከተመው በአንድ አካል ጥንካሬ አይደለም። ወይንም በህወሃት በረከት አይደለም። ሥሙን እማናውቀው በነበረው ኦህዴድ ጥንካሬ እና ብርታትም አይደለም። አልነበረምም። ወ/ሮ ታደሉን ልጃቸውን ገድሎ ከልጃቸው ሬሳ አስቀምጦ የደበደበ ጨካኝ የዞግ ድርጅት የፍትህ ሐዋርያ አድርጎ ለመቀበል የማይታሰብ ነበር። ሺወች የኦሮሞ ልጆች የኢህአዴግ መራሹ ህወሃት ተጠቂ ነበሩ። አካላቸውን፤ መኖራቸውን አጥተዋል። ግን የዛሬው የሽመሊዝም ዝምንም ከበደል ላይ በደልም ነው።
 
የአባዱላይዝም ህወሃትን የሰለቀጠው ኦህዴድ ለበትረ ሥልጣን የበቃው በግርፍ ፖለቲካ አይደለም። በአልቦካ ጭቃ ምርጊት አይደለም - አልነበረም። ያን ኦሮማራ ለድል ያበቃ አቅም፦ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን እና አመራራቸውን አክብሮ፥ በሰጨኝ ሳይል ከአቶ ታዬ በፊት በቀደመ ሁኔታ ሞግቷል። ይህን ፖለቲከኛው ዶር ሚልኬሳ ሚደጋ አያውቁም። ያ አቅም ከጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ አሊ ባልታቀደ የውጭ ጉዞ እንዲባትሉ አድርጓል። ለዛውም ጉቦ ይዘው። ሌላም፤ ሌላም። 
 
በተመድ የወቅቱ ጉባኤ ሰብዕናቸው ብቻ ይገነባ ዘንድ አንድ ልዑክ ልከው ነበር። የአውሮፓ ህብረት ፕሬዚዳንትን ጋብዘው በሳቸው ሹፌርነት ኢትዮጵያን አስጎብኝተዋል። አንድ ማነፃጸሪያ ዕውነት ተዚህ ላይ ላቅርብ። ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ኮሽ ባለች ቁጥር ኮሽታዋን ለማድመጥ ቆቅ ናቸው። ሰሞኑን አውሮፓ ላይ ነበሩ። 
 
ጣሊያንም፤ ፈረንሳይም አጀንዳቸው አልነበሩም። ባቲካን አዲስ መሪ ፈጣሪ ስለፈቀደላት ያን ለማግኜት መናጆ አገራት አስፈለጋቸው። ለባቲካን እጅ መንሻ ይዘው ሲሄዱ፦ ለፈረንሳይ እና ለጣሊያን ግን ባዶ እጃቸውን ነበር የሄዱት። የጉዞ ክታባቸው ባቲካን ብቻ ነበር። ለዚህ ነው ጠቅላይ ሚር አብይን አቃላችሁ ከማየት በልካቸው ገምታችሁ ተነሱ የምላቸው የተቃዋሚ ሃሳብ አራማጆችን። 
 
እኔ በሄሮድስ፤ በጲላጦስ፤ በፈርኦን፤ በሙሶሎኒ፤ በጋዳፊ ወዘተ ዘመን የሆኑትን አስብ እና ይህ የአሳቻ መሪ ዘመን በኢትዮጵያ አቻውን ማግኜት አልቻልኩም። ለዚህ ነው ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን አሳቻ፤ የአመራር ዘመናቸውንም አሳቻ የምለው። በህወሃት ዘመን የፊት ረድፍ ሞጋቹ ነበርኩኝ። ግን ህወሃት በመኖሪያ አፓርትመንቴ ድረስ ዘልቆ አሰቃይቶኝ አያውቅም። በስሱ ለዛውም አክብሬ፤ የተሰሩ ነገሮችን ሳላጣጥል የሚሞገተው አብይዝም ግን እጅግ ነው የሚያሰቃየኝ። ተሰድጄም። ፈርቼ አይደለም በትህትና እና በአክብሮት እምሞግተው። ዕድሜ የኔታ ስለሆነኝ ነው። 
 
ኢትዮጵያ ደውየ ቤተሰቦቼን አግኝቼ አላውቅም። እንዲህ ያለ ሥር የሰደደ የሰው ልጅ የስደት ሰቆቃ አመራር በየትኛውም አገር ፖለቲካ የማይፈጸም ነው። በጣም ጎምዛዛ የሆኑ ጉዳዮች ናቸው ያሉት። ይገርመኛል አቅለውም፤ አግለውም የሚያዮዋቸው ሰብዕናወች፤ እጅግ አሳንሰው አብይዝምን ገለባ አድርገው የሚያዩ ሚዲያወችም ይገርሙኛል። ኢህአፓ የጠቅላይ ሚር አብይን ግብዣ ሳይጎበኝ፤ የስብሰባ ታዳሚነት ሳያጠናቅቅ እና ጥሪያቸውን ረግጦ ሲወጣ ገርሞኝ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ በኢህአፓ ላይ ጹሁፍ የፃፍኩት። ወደፊት ኢህአፓ የሚከፍለውን ተጨማሪ መስዋዕትነትም አስልቼ። የኢትዮጵያ መሪ በሙያቸው ሰላይም ናቸው። 
 
የሆነ ሆኖ ሳይለንት ማጆሪቲው ባለ አቅም ነው። አቅሙን ግን አያክለፈልፈውም። በፍፁም። ተዚህ ላይ ተጨማሪ ሃሳብ ላንሳ ……
ስለ አማራ ህዝብ በጦርነቱ መድቀቅ፤ በጦርነቱ የአማራ ህዝብ እና የጸጥታ አቅሙ ውስጥ በአደባባይ የሚሰጡት የዶር አብይ አወንታዊ ምስክርነት እና በድርጊት አልገናኝ ሲል፥ የአማራ የጸጥታ ኃይል አቤቶ የኤርትራ መንግሥት፤ አቤቶ አብይዝም፤ አቤቶ ህወሃቲዝም ያልተጠየቁበትን የአማራ የጸጥታ ኃይል በጦርነቱ ወቅት በነበረው ተሳትፎ በሦስት ወንጀል ብቻውን ተነጥሎ በዓለም አደባባይ ሲከሰስ፤ ሦስቱ ባለአቅሞች ግን በጦር ወንጀል ብቻ ተጠያቂ ይሆናሉ ሲባል፦ ያን ሰብሮ ገብቶ እርማት እንዲወሰድበት፤ ነገረ "ምዕራብ ትግራይ" አገላለጽም እንዲስተካከል፤ የአፋር እና የአማራ ህዝብ በህወሃት የደረሰበት ውድመት የትግራይ ህዝብ ከደረሰበት ሰቆቃ ጋር እኩል ሊታይ እንደሚገባ የተደረገው አቤቱ ዊዝደም የተገበረው ነው።
 
የአማራ ልጆች አቅማችን ይፈለጋል ግን ለቀጣይ ስቃይ እና መከራ። የውጮቹ አይፈረድባቸውም። ሙሉ መረጃ የላቸውም። በጦርነቱ ጊዜ ወደ አገር ሲገቡ ስለ አማራ ህዝብ የሚሰጣቸው መረጃ መራራ ነው። ይህን እናውቃለን። ስለሆነም ትግራይን ብቻ አይተው እንዲመለሱ ስለሚደረግ ከመረጃ ውጭ ነበሩ። ይህን እኔ አውቃለሁኝ። የአቶ ታየ የወሎ ስቃይ እና መከራ ሲገልጹ ፕሮፖጋንዲስት ለእኔ አላስፈለገኝም። ቀጥ ብሎ ወደ ልቤ ገባ። አረጋገጠልኝ። ቀድሜም ጽፌበታለሁኝ። 
 
የሆነ ሆኖ ህወሃትም ጉዞየ የፃድቅ ነው ብሎ ሲፏልል ተግ እንዲል፤ ሚዛን በግሎባል ደረጃ እንዲጠበቅ ያደረገው ጭምቱ አቅም፤ ብልህነትን የዋጠ ስልት ነው። እና ዶር ሚልኬሳ ሚደጋ አዕምሯቸውን ወደ ሁሉም አቅጣጫ ልከው ቢመዝኑ መልካም ነው እላለሁኝ በአጋጣሚ አጋጣሚ ካገናኜን ዘንዳ። 
 
በሌላ በኩል ይህ ቃለ ምልልስ ሆርን ኮንቨርሴሽን ከዶር ሚልኬሳ ሚዲጋ ጋር ያደረገው ሁለት ክፍል ተጨማሪ ሦስተኛ ተቆርጦ የወጣውም እኮ እኛ ባስተዋልነው ሚዛን አበጥረን አንጠርጥረን ጭብጡን ስላስረዳን ስለፃፍንበት ነው። ከዛ ጹሁፍ በፊት አንከር ሚዲያ ቃለ ምልልስ ከዶር ሚልኬሳ ሚደጋ ጋር አላደረገም። አንከር ትልቅ ጆሮ፤ ትልቅ አፍንጫ ስላለው አብይዝምን ለመታገል ይጠቅማል ባለው ሁሉ ቀዳሚ አልነበረውም። አሁን ግን ተቀደመ። ቅኑ አማራ ብልህነቱን ፈንጠቅ ሲያደርግ ሰፊ መንገድ ቧም ፏም ይላል። 
 
በተጨማሪም ማህበረ ኦነግ፤ የኦሮሞ ፖለቲካ እና ሚዲያወቻቸው ከእንግዲህ የአማራ አቅም አያስፈልገነም ብለው ደምድመው ነበር። ከታየይዝም መታየት እና መደመጥ በኋላ ግን እነሱን ማድመጥ አማራ ጀመረ ብለው ያሰቡ ይመስላሉ። ከዛ በፊት በሆርን ኮንቨርሴሽን በአማርኛም ቋንቋ ቢሆን አድማጫቸውን ይመዝኑት። እኔ ገብቼ አስሼዋለሁኝ። አይመጣጠንም። 
 
አቶ ታዬ ደንዳአ መጀመሪያ ሲታሰሩ የነበረውንም ግብረ ምላሽ በተለይ የአማራን፤ ጭምቱን የሳይለንት ማጆሪቲውን ፀጥታም ይለኩት። ያ የዝምታ ዲሞንስትሬሽን ነበር። ምን ለማለት ነው ይሄ? ተሳትፎ አንከር ሚዲያ ቀስቅሶን ወይንም አቅጣጫ ሰጥቶን አይደለም አሁን ጆሮ የሰጠነው። አንከርማ መጀመሪያ አቶ ታየ ደንድአ ሲታሰሩም፦ ሲፈቱም በልኩ ተግቶበታል። ለእኛ የሚሆን፤ ወደ ውስጣችን የደረሰ፤ እኛ ስንሞግት ከቆየነበት ጭብጥ ጋር የለብታ ግንኙነት ስላልነበረው አልተሳተፍነም። በዜናነት ከመቀበል ውጪ አቅም በፍፁም አላባከነም። ተሳትፏችን ምንም ነው የነበረው። እኔ እራሴ በአደብ ነው የተከታተልኩት። አልፃፍኩበትም። አልተማገድኩበትም።
 
አይተናል እኮ የአቶ በቀለ ገርባን ሰብዕና፤ የአቶ ለማ መገርሳን (ዶር) የሱሴ መንገድ እና ሰብዕና፤ የጠቅላይ ሚኒስተርነት ይሁንታ ለዶር አብይ አህመድ፤ የጣና ኬኛን ጉዳይ፤ የዶክተር መራራ ጉዴናን የድርጅታቸውን ተሳትፎ እገተና እስር፥ የሬቻ ጭፍጨፋ ወገን ብለን በውጪው ዓለም ክብር እንዲያገኝ በማድረግ እኛ አማራወች ለፈጸምነው ትጋት ምላሹ የሰላ ፋስ፤ ንቀት፤ ስላቅ እና ጭካኔ ነው የተጋበዝነው። ሁለት ሙሉ ዓመት ደግሞ ድሮን። 
 
አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፤ አቶ ለማ መገርሳ የዶክትሬት ዕድሉ በኦሮማራ ነበር። ሌላም ሦስተኛ አቶ ወደ ዶክተሬትነት ሆላንድ እንዳሉ አዳምጫለሁኝ። ቲም ዶር አንባቸው ግን አፈር። ከመሳደድ ውጪ እኛ ጠብታ አልደረሰንም። የሬቻ ጭፍጨፋ፤ የዶር መራራ ጉዴና ከእስር ሲፈቱ በዲፕሎማሲው ማህበረሰብ የነበራቸው የከበረ አቀባበል፤ የአማራ ልጆች የእጅ ሥራ ነው። የነገረ ቆሼም አደጋ ያገኜው የዲፕሎማሲ አጋርም እንዲሁ። እነሱ የኦሮሞ የፖለቲካ ሊቃናት ኢትዮጵያንዚም በውስጣቸው ተጠይፈው ሲሸነግሉን፤ እኛ ግን ሁሉን እረስተን አመናቸው። ግን በደሉን።
 
እኛ በቅንነት ስንሞግት ሺ ተቀናቃኝ እያፈራን፤ መኖራችን ቀራንዮ አድርገን ነው። ያ ለኢትዮጵያ የየትኛውም ድርጅት ፖለቲከኞች የወንዝ ዳር አሽዋ ነው። በባዶ እግር በነፋሻው የወንዝ ዳር የሚዝናኑበት። በነፃ ነዋ የሚታደሉት። ጠቅላይ ሚር አብይ ልሙጥ በነበረው ዘመናቸው ለመንበር ያበቃው የእኛ ብዕር ምስክርነት ነበር። 
 
ግን ቅኑ አማራ በወል ተቀጠቀጠበት። ፊትለፊት ወጥተው የሞገቱ የአማራ ልጆች እናቶችም ድምጽ በሌለው መሳሪያ በአንድ ዓመት ውስጥ ተመስጥሮ እንጂ ሰማዕትነት ተቀብለውበታል። በአንድ ዓመት የስንት ፖለቲከኞች እናት በሥጋ ተለዩ? ዘመን ይፍታው።
 
የሆነ ሆኖ ያን ጊዜ አቶ አብይ ሳሉም፤ ዶር ሳሉም ጉጉል ላይ ምን ያህል ፈላጊ እንደነበራቸው በወቅቱ እኔ ቼክ ሳደርገው ነበር። ከዜሮ ወደ ሄሮ ያሸጋገረው የአማራ ልጆች ሙሉ ድጋፍ ነበር። የማይታወቁ ስለነበሩም ቲሙ ተቀባይነት ያገኜው በአማራ ልጆች ተግባር ነው። የማሳመን አቅም። ጠቅላይ ሚር መብይ አህመድ ከሄሮ ወደ ዜሮም ያወረደው ያ ቅን አቅም ተከፍቶ ነው። በፊት በነጣ፤ አሁን ደግሞ አብይዝም በገፍ በዶላር ክፍያ ደጋፊ እየተሸማመተ መሆኑን እናውቃለን። በነፃ ገብያው በዛ በህወሃቲዝም ዘመን መኖራቸው የማይታወቁ ሰብዕናወች ዛሬ መስካሪ፤ ዘካሪ ተንታይ ተብለው ከአንጋፋ ጋዜጠኛ ጋር ሲወያዩ ሳይ ይገርመኛል። መስኪ ትንታጓ ጸሐፊ ግን ካቴና ላይ።
 
የሆነ ሆኖ እኛ ኢትዮጵያዊ አማራወች ለኦሮማራ የከፈልነው ገድላዊ ስኬት ለኦሮሞ ሊቃናት፤ ለማህበረ ኦነግ ይሁን ለቤተ - ብልጽግና እነሱ ከዜሮ በታች ነበር የሚዩት። ክብር፤ ሞገስ ቀርቶ ግድያ፤ መስቃ፤ መገለል ነበር የ7 ዓመቱ የኦሮሞ የፖለቲካ ኢሊት ምላሽ። በጣም በእርግጠኝነት የምገልጸው የትኛውም ማህበረሰብ በሚያደርገው ተጋድሎ ከኢትዮጵያዊ አማራወች አቅም፤ ከሳይለንት ማጆሪቲው ቅን ድጋፍ ውጪ ለስኬት አይበቃም። ለዚህ ነው ጃዋሪዝም በነቁጥ ሁሉ እየወጣ ሲፎካክር እስኪ አድርገህ አሳየን በሞቴ የምለው። እንደማይሆን፤ እንደማይሳካም ስለማወቅ። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ራዕይ ዊዝደምን ንቆ ስለሚነሳ።
 
የሚገርመኝ የአማራ ኢሊቶችም ይህን ይዘሉታል። ይንቁናል። አያዳምጡንም። ያገሉናል። እኛም በዝምታችን ውስጥ መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ እንላቸዋለን። እግዚአብሄር አላህ የሰው ልጅን የፈጠረው ለምስጋና ብቻ ነው። ምስጋና አይከፈልበትም። አንድም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሊቅ፤ ወይንም ሚዲያ ይህን ሲያደርግ አልመለከትም። ለዚህ ነው በዘመናችን ያሉ ክፍተቶችን በተለይ በዚህ ሁለት ዓመታት ካለ ውዳሴ ከንቱ የሚችሉትን ነገር ከመሞካከር ተግ ብለው፤ ሊቀ - ትጉኃን በዝምታ ላይ የሚገኙት። 
 
የአሁኑስ ዕንቁ የአማራ አቅም አፈሰን ማን ይሆን "ካልኩሌተር ማህንዲስ" ነኝ ብሎ የሚወጣው? ተኮፋሹ?? በሚል አብይዝምንም፤ ህወሃቲዝምን፤ ተቃዋሚ ኃይሎችንም ጨምተን ግራ ቀኙ ሲፎካከሩም፤ የማን ደም ፈሰሰ ሲባባሉም እየተከታተልን ያለነው። ለኦሮሞ ፖለቲካ በግሌ የማቀርበው ዕውን ለኦሮሞ ህዝብ ከቆማችሁ በዘርፋ በኢትዮጵያዊነት የተሠሩ ተግባራትን የማድነቅ አቅም ፊደል ብትቆጥሩ እላለሁኝ። ፊደል የሚለውን ቃል የምትወዱት አይመስለኝም። አማራ የሚለውን ኃይለ ቃል ስለሚጎናጸፍ። 
 
የሆነ ሆኖ እኔ ለ17 ዓመታት በክስ በተሞሸረ የጸጋዬ ድህረ ገጽ እና የጸጋየ ራዲዮ ስንት ፍዳ እና መከራ ሳሳልፍ አንድም የኦሮሞ ልጅ ከጎኔ ተሰልፎ አያውቅም። "ብልጽግና የማነው ብለው ሲጠይቋችሁ የኦሮሞ ነው በሉት ሲሉ በባሌው ጉብኝታቸው ዶር አብይ ገልጸዋል።"
ይህንን ያሉት ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ቢሆን ውስጤ ለኦሮሞ ህዝብ ፍትህ፤ ነፃነት፤ እኩልነት፤ ክብር ነው ካሉ ይህን የአንዲት ሴት ባተሌ ተግባር ለምን መንግሥታቸው ዕውቅና አልሰጠውም??? የኦሮሞ ሊቃናትስ ለምን ይህን ዕውነት አይደፍሩትም???? ዕውን የኦሮሞ ፖለቲካ ለኦሮሞ ህዝብ ወይንስ ክብር ከሆነ? ለግል የሰብዕና የድሎት ኑሮ በየዘመኑ ህዝብ የሚገበረው ለማን? ስለምንስ??? ለኦሮሞ ህዝብ አለመሆኑ እኔ በደንብ ይገባኛል።
 
በውነቱ የኦሮሞ የፖለቲካ ሊቃናት ከኢትዮጵያዊው ይሉንታ ጋር ዕውነትን ብትመሳጠሩ ይበጃል። ተለያይተን የማንለያይ ነን እና። አባ ቅንየ አማራ፤ ገራገሩ አማራ እየተጠላም፤ እየተወገዘም፤ እየተገደለም፥ እየተቃለለም ዕውነት ብልጭ ስትል አይለግምም። የአማራ ህዝብ እግዚአብሄር ከፈጠረው ቸርነትም፤ አማኑኤል ከመረቀለት ቅንነትም በላይ ቸር እና ቅን ህዝብ ነው። ከመቼ ወዲህ አንከር ሚዲያ ዶር. ሚልኬሳ ሚደጋ ጋር ለቃለ ምልልስ ተቀመጠ? የሆርን ኮንቨርሴሽን አወያይስ መቼ ያቀርብ ይሆን?? 
 
የሆነ ሆኖ አቶ ታየ በዘመነ አብይዝም ለሁለተኛ ጊዜ ነው የታሠሩት። የሰሞኑ የትግል ወላፈን ኦሮማራ ትንሳኤን ከመሻት ከሆነ ባይታሰብ መልካም ነው። ወዘተረፈ ጅልነት ስሌለ። ዕውነትን ለማብራት ከሆነ ግን ይኽው እኔም እየፃፍኩበት ነው። 
 
ለአቶ በቀለ ገርባ አማራ ተገብሯል። "ለዝም አንልም የኢትዮጵያ የእስልምና ንቅናቄም" ከእኔ በላይ ፊት ለፊት ወጥቶ የሞገተ የለም። በአቴ ጎንደረም በአደባባይ ወጥቶ ተጋፍጧል። በዘመነ አብይዝም ተከሳሹ፤ መስጊድ ላይ ችግር ፈጣሪ ተብሎ ልዑክ ሁሉ ተልኳል። እቴጌ ጎንደር ተብጠልጥላለች። ያ ግሎባል ዘመን ከዘመን የቀጠለው የቅኒት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልዑቅ ፵፭ ቀን ሱባኤ አብይዝምን አስደንግጦት። 
 
በመከራ ጊዜ አገር ውስጥም፤ ውጪም ከዕንባቸው ጋር እኩል ቁመን ግን ውግዘት። በጥቅሉ ሳየው አማራ እጁ አመድ አፋሽ ነው። አቶ ሳዲቅ ያልነበረችውን፤ ትውር ያላለችውን ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳን ሲያመሰግን አይቻለሁኝ። ያን ደግሞ አብይዝም የምርጫ ቦርድ ሹመኛ በማድረግ ዕውቅናውን አጽድቆታል። በእሷም፤ በብላቴ ሎሬት ጸጋየ ገብረመድህን ትጋቴ ተከሳሿ ደግሞ እኔ ነኝ። ተከስሼ ነበር። የኦሮሞ ፖለቲካ ጫፍጫፋን አይሂድ። አመክንዮን አጥንቶ መነሳት ለትውልድ ጠቃሚ ጉዞ ነው። ታሪክም የሚሠራው በዕውነት እና በመርኽ እንጂ በጥላቻ ግርዶሽ አይደለም። 
 
የሆነ ሆኖ ዶር ሚልኬሳ ሚደጋን ትናንት በ25/06/2025 ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ያዳመጥኳቸው። ወደ 26 ደቂቃ ብቻ ያለውን ነው ቆርጬ ዕድምታውን ብቻ ነበር ያቀረብኩት። ለአማራ ፖለቲካ፤ ለይስሙላ ለሚያዘው ኢትዮጵያኒዝምም ጠቃሚ ይሆናል ብየ እማስበውን ብቻ ነው እኔ ያቀረብኩት። አቶ ታየ ደንድአ በሌላ ኃይል ገፊነት ነው፤ ሌሎችን ጠይቀን ሊያረጋግጡልን አልቻሉም ያሉትን ማህበረ - ብልጽግናን ተረጋጉ "እኔም እማውቀውን ልግለጽ" ብለዋል ዶር ሚልኬሳ ሚደጋ። ከመቅረት ዘግይቶም ቢሆን መገኜት መልካም ነው።
#ምን አሉ ዶር ሚልኬሳ ሚደጋስ? መንፈሱን ብቻ ነው። ዝርዝሩን ሊንኩን ለጥፌያለሁ።
 
1) የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ የአማራ ጥላቻ "#ዲፕ" ነው ሲሉ በአጽህኖት ገልጸዋል። ይገርማል። ያን ሁሉ የአማራ መታመንን አከሰሉት ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ። ግዛን፤ ንዳን ሺህ ዓመት ንገሥልኝ ብሎ ቸሩ አማራ አልይህ፤ "ፍረስ፥ ልናድህ" የጤና አይደለም። የአማራ ልጆች ሙሉ ይሁንታ ባይኖር በፍጹም የኢህዴግ ሪኮሞንዴሽኑ ጠቅላይ ሚኒስተርነት አይጸድቅም ነበር። ያን የመሰለ የክብር ተክሊል ባለቤት ሊሆኑም አይችሉም ነበር ዶር አብይ አህመድ። ያን ጊዜ ከኢህአዴግ የወጣ ግራጫማ ጢስ ያድነናል ብለን ማመናችን ጅልነታችን ልክ አልነበረው። ድጋፋ የአማራ ግሎባል፤ ፍጹም ንጹህ እና ድንግል ነበር። 
 
2) "አቶ የኋንስ ቧያለውን በሚመለከት እኔ ከአብይ ጋር በነበረኝ ኮንቨርሴሽን "#አማራ አማራ #እያለ ነው። አሳየዋለሁ አብይ ብሎኛል።" ይህን ሲሰሙ ዶሩ እራሳቸውን እንዳዘጋጁ ሁሉ፤ ለወንድማቸው፤ ለጓዳቸው፤ ለባልደረባቸው ለአቶ የኋንስ ቧ ያለው ሹክ ቢሏቸው ኖሮ፤ አቶ የኋንስ ቧ ያለው መተንፈስ የሚችሉበትን መስመር መተለም ይችሉ ነበር። አቶ የኋንስ ቧ ያለው እኮ የአማራ ወጣቶችን እኛ እንሻላችሁአለን፤ ድርጅት አያስፈልጋችሁም ሲሉ ነበር ለደቡብ ጎንደር ወጣቶች። እኔ በወቅቱ ሞግቻቸዋለሁኝ።
 
እንዲህም ሆኖ በጠቅላይ ሚር አብይ ዘንድ በጥርስ ተይዘው እንደ ነበር ዶር ሚልኬሳ ሚደጋ ገለጹት። በቀጣይ የአቶ የኋንስ ቧ ያለው ነፍስም ድንግል ትድረስላቸው። … እንጂ በቀላሉ የሚለቀቁ አይመስለኝም። ግን አቶ ቹቹ አለባቸው ጽኑው የብልጥግና ደጋፊ ኢትዮጵያ ናቸውን??? "#ጠላት" ብሎ ፈርጆታል "አብይ" ብለዋል አቶ ታየ ደንድዓ።" በአንድም በሌላም በነቂስ የአማራ ሊቃናት የቅደም ተከተል ጉዳይ ካልሆነ፥ በሰማሁት ልክ #ኢመርጀንሲ #ሩም እንዳሉ ነው የሚገባኝ። ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ሁሉን አሉታዊ ነገር የሚከውኑት ከአማራ ጥላቻ የተነሳ ስለመሆኑ ባልደረቦቻቸው መስክረዋል።
 
3) "በአማራ ላይ ለማደርገው ሁሉ #ሴሌ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ነው። ከ55ቱ የኦዴፓ ማዕከላዊ ኮሜቴ አካላት ይልቅ እሱ ይበልጥብኛል። ሁላችሁም ብትጨፈለቁ አማራን ለመግዛት ያስቻለኝ ሚስጢረኛየ ዲያቆን ዳንኤልን አታክሉም ብሎናል አብይ። ከወረዳ፤ ከዞን፤ ከክልል ያሉ የኦሮሞ አመራሮች ዲያቆን ዳንኤልን አስመልክቶ ስለሚቀርበው ጥያቄ መልስ ሲሰጥ።" 
 
በዚህ አያያዝ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ውስጧን ለፈተና በመግለጥ የዲያቆኑ ድርሻ ሰፊ መሆኑ ይረዳኛል። ይህን ዶር ምልኬሳ ሚደጋ ዕይታ ሳይሆኑ እኔው ነኝ ስጋቴን የምገልጸው። ከሆነው በላይ የነገው ከባድ ይመስለኛል። በእኔ ዕይታ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በማህበራዊ ሚዲያ ከሚጭራቸው ይልቅ ውስጥነቱ ዲካ የለሽ ቤርሙዳ ትርያንግል ሆኖ ነው የተሰማኝ። እኔ እማስበው ደጋፊ፤ የቅርበት የተለመደ ጉዳይ እንጂ እንዲህ የጭካኔ ሞተር መሆኑን ጭራሽ በዚህ ልክ አማራን ለመበቀል ታጥቆ መነሳቱን አስቤ አላውቅም። ሞግቼው ሁሉ አላውቅም። የአማራ የመከራ ናዳነት የሚጠቅም አይመስለኝም ለልጁም ለቤተሰቡም። ልጅም ትዳርም አለና። ቢያንስ??? አንተ የምለው የቤተ ጥበብ ቤተኛ ስለሆነ ነው።
 
4) የቲም አንባቸውን ጉዳይ፤ የአዲስ አበባን ፭ ሰማዕታት አስመልክቶ አቶ ታየን የሆርን ኮንቨርሴሽን ጠያቂ ቢጠይቃቸው ኑሮ ላልኩት፤ ዶር ሚልኬሳ ሚደጋ አንዱን ገልጠውታል "የሰኔ ፲፭ቱ 2011 የአማራ ሊቃናት ሲያልቁ "አማራወች እርስ በእርሳቸው #ተፋጁ፤ ተገዳደሉ፥ ጎንደሮችን ወሎዮወች ገደሉ፤ ጎጃሜወች ተጠቀሙ ብላችሁ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ፤ ፌስቡክ ላይ ፃፋ ተብሎ ትዕዛዝ ተሰጥቷል። ዶክመንቱን ያቀረበችው አዳነች ናት። እኔ ግን ትክክል ስላልነበረ የአመራሩ አካል ሆኜ ምንም አልፃፍኩም። ሃዘን አልነበረም። ጽህፈት ቤቱ በሙሉ በዚህ የፌስታ ስሜት ውስጥ ነበር።" ብለዋል። ማህከነ!
 
ህም! የገረመኝ የዶር አንባቸው ባለቤት ከንቲባ ወሮ አዳነች አበቤ በቅርብ ክትትል እንደሚያደርጉላቸው አንድ ቃለ ምልልስ አዳምጫለሁኝ። በተጣበበ ጊዜ ሁሉ በአካል እየተገኙ እንደሚጠይቋቸው ገልጠዋል። እና ከንቲባ አዳነች ምን ነክቷቸው ይሆን የአማራ ክልል ሊቃናት በዛ ናዳ ሲያልቁ፤ አካላቸው መሆናቸውን ረስተው እንደ ፌስታ ኦዴፓወች እያዩ፥ በምን ሞራል ከንቲባ ወሮ አዳነች አበቤ የዶር አንባቸው ቤተሰብ ልዩ ተንከባካቢ ሊሆኑ እንደቻሉ አልገባኝም። እንዲገባኝም አልፈቅድም። ዕንባ፤ ሃዘን፤ ሞት መራራ ስንብት ነው።
 
 መዘባበቻ፤ መቀላለጃ ሊሆን ከቶም አይገባም ነበር። እሰይ ስለቴ ሰመረም አያሰኝም። ኦሮማራ ባይኖር ቲም አንባቸው ህይወታቸው ይቀጥልም ነበር ማለት ነው ዕድምታው። በተለይ ሴቶች ከዚህ መሰል ኢ- ሰዋዊ ድርጊት እና ኢንትሪጋዊ የሽንገላ ዕሳቤ ልንወጣ ይገባል ባይ ነኝ። እናትነት እዮራዊ ጸጋ ነውና! እናትነት ይከበር ከእነ ምግባሩ። 
 
5) " ብልጽግና የሚመሠረተው አንደኛው ምክንያት #አማራን #ለመግዛት ነው። #አይገባችሁም ወይ? ተብለናል። መደበኛ አካሉ በተሰበሰበበት። " በቃ! የብልጽግና ዓላማ እና ግብ፤ የአዲሱ ለውጥ ራዕይ እና ተስፋ፤ የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ወደ ሥልጣን መምጣት ሊያሳካው ያቀደው ነገር አማራን ማፍረስ፤ ቅሪት አካል ከተረፈም ፍርስራሹን መግዛት እና ማስገበር መሆኑን ነው ዶር ሚልኬሳ ሚደጋ ደግመው፤ ደጋግመው ያስረዱት። እግዚኦ!
 
6) ሁለተኛው የተነገረን ኦዴፓ ፈርሶ ብልጽግና የሚመሰረተው "የብሄር ፖለቲካ ሙሰኛ ስለሆነ፤ ከሙስና ኢትዮጵያን ለመገላገል ብልጽግናን መፍጠር ያስፈልጋል ብለውናል። እኔ ግን የማውቀው ጓደኛየ" ይላሉ ዶር ሚልኬሳ ሚደጋ፤ አዲስ አበባ የሚኖር ተሳስተው እንደሆን አላውቅም ሚሊዮነር ሳይሆን "ቪሊየነር" ሆኗል በአንድ ዓመት ነው ያሉት።"
 
ሆርን ኮንቨርሴሽን ሚዲያው በሆነ የፖለቲካ ድርጅት የሚመራ አለመሆኑን ተረድቻለሁኝ። የፊት /// የኋላ የሚለው ነገር የለውም። ቀድሞ ተሰናድቶ ከተወያዮች ጋር መመካክር፤ በድርጅታዊ ሥራ ተኳኩሎ፤ በሜካፕ ቁንጅት ያለ ውይይት፤ ሬድሜድ የሚመስል መንገድ የተከተለ አይመስለኝም። ያዝልቅለት። አሜን።
 
ይህ በኢትዮጵያ የሚዲያ ታሪክ የመጀመሪያ ይመስለኛል። ተወያዮቹ ሲናገሩ ሁልጊዜ አወያዩ ይደነግጣል። "ግን እንዴት? ግን ለምን? በእርግጥ እንዲህ ብሎ ነገራችሁ" ይላል። ይህ ንጽህና ለሚዲያ ዕድገት እጅግ አስፈላጊ ነው። በጣም። ለትውልድም የኔታነት ነው። ከቀጠለበት። ሳንሱርድ ያልነካው፤ ጫና አልቦሽ ውይይት ነው ለአምስተኛ ጊዜ ያዳመጥኩት። ብዙ የኮስሜቲክ መውደቅ መነሳትም የለም። የአቶ ታየ ደንድአን ክፍል አንድን ደግሜ፤ ሦስቱን አንዳንድ ጊዜ አዳምጬ ነበር። ይህ የዶር ሚልኬሳ ሲታከል አምስተኛየ ሆነ። ክፍል ሁለት አሁን አየር ላይ እንደሆነ ተመልክቻለሁኝ ከዶር ሚልኬሳ ጋር። 
 
#ዘለግ ያለ መቋጫ።
 
የፈላስፊት ኢትዮጵያ የሃይማኖት አባቶች ሌላ ሥራ ላይ ከሚያተኩሩ እንዲህ በጥላቻ የሚቀዝፍ መንፈስ ከኢትዮጵያ ይርቅ ዘንድ በርትተው ሊጸልዩ ይገባል ባይ ነኝ። ተራ ፋክክር፤ የተለመደ መጎሻሻም፤ የተዋህደን መመቀኛኜት፤ የኖረብን ሴራዊነት አይደለም። እኔን የገባኝ አዲስ የማይታወቅ አሳቻ መንፈስ ኢትዮጵያን አይሆኑ ለማድረግ እንደ ተነሳ ነው።
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እራሳቸው መዳን አለባቸው። ጥላቻን የላይኛው እዮር የሚፈቅደው አይደለም። አንድ ሙሉ ማህበረሰብ በሱናሜ ለማጥፋት ማሰቡ በራሱ ኢ- ተፈጥሯዊነት ነው። የጤናም አይደለም። የትዳር አጋር ያለው፤ እህት ወንድም ያለው ሰው እንዲህ ብቻውን ከጥላቻ ጋር ተጋብቶ ሊዘልቅ አይገባም። ቤተሰብ ባሊህ ሊለው ይገባል። ረጋ ያሉት ክብርት ቀዳማዊቱስ ምን ይሉ ይሆን?
 
ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ አሊ ለሎሬት ያበቃቸው አመክንዮ ጋር ሲጣሉ??? እንደገናም ጓደኛ፤ ሚስጢረኛ የሚሉት ቤርሙዳ ትረያንግሉ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ያን ሁሉ የሚሊዮኖች ፍቅር በጭካኔ አስደፍቶ፤ እርቃን ያስቀረ ከሆነ ተልዕኮው ሊመረመር ይገባል። የጠቅላይ ሚኒስተርነቱን ቦታስ፤ ቦታውን ለራሱ ፈልጎትስ ከሆነ? ቅናትስ ቢሆን? ዲያቆን ዳንኤል ክብረት አገር የመምራት ህልም ቢኖረውስ? ይቀናቅኑኛል፤ ይበልጡኛል ያላቸው ላይ ደባ አሰርቶ ቢሆንስ እነ ዶር አንባቸው መኮነን ላይ? ብቻ ለእኔ በፍጹም ያልተመቹ ሳምንቶች ናቸው። ከወረዳ፤ ከዞን እስከ ክልል የኦሮሞ ብልጽግናወች ስለምን የዲያቆን ዳንኤል የቤተ መንግሥት ቤተኛ መሆን ስለምን ሻከራቸው? ይህም ያልገባኝ ጉዳይ ነው። በወጥነት አቋም ስለምን ተያዘበት?
 
ለምን የሰው ልጅ በዚህን ያህል ጥልቀት ሰውን ይጠላል? አጤወቹ ቋሚ ሆኑን? ደርግ ዘለቀን? ህወሃት ምኞቱ ጸናለትን? ሞት የማያዳላ፤ ለሁላችንም የማይቀር ተሸክመነው ያለ ጥልቅ ጉድጓድ እያለ እፍኝ ለማትሞላ ጊዜ እንዲህ ለምን በክፋ እንተሳሰባለን? ውስጤ በብዙ አዝኗል። ልብሱ፤ ገበርዲኑ፤ አጀቡ፤ ፕሮቶኮሉ ሳስበው ብላሽ ነው የሆነብኝ። የውነት ብላሽ።
 
«የታዬ ደንደአ ድሎች»
 
የእኔ ክብሮች ምዕራፍ ፲፭ በዚህ ብቋጨው እመኛለሁኝ። እናንተም - እረፋ። እኔም - ልረፍ። ላዳምጥ። ላስተውል። እራሴን - ልረም። በምዕራፍ ፲፭ የገደፍኳቸው ይፈታተሹ። ጊዜ ወስጄ እንዲህ ዓይነት ከባድ ሁነቶችን ላጥና። ከኦሮሞ ሊቃናት የሚወጡ መረጃወች ከብደውኛል። ነገም ያስፈራል።
 
አጠቃላይ ሁነቱን ሳይ ዶር ለማ መገርሳን + ዶር ገዱን አንዳርጋቸውን (እንደተለመደው በመናጆነት) በአዲስ ኦሮማራ ተቀበሉን ዓይነት ነው። የዚህ መንፈስ በኽረ ዓላማ የጠቅላይ ሚር እጮኛ አመራ ሆኖ እንዳይወጣ ያለው ጥልቅ ስጋትን ምጥ የሚገላግል አቅጣጫ ቅየሳ ላይ እንደሆነ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን ሥልጣነ ዘመን እንዲያክትም በሚሹ የእነ አቶ እገሌ ዕድምታ ይመስለኛል። በብዙ ሳስበው የዶር አንባቸው ሰማዕትነት መሠረተ ጉዳዩ አጀንዳ አለመሆኑ ይገርመኛል። ሰማዕትነቱም ጎርበጥበጥ ሲያደርግ አላስተውልም። ይህ የሚያሳየኝ በዝምታ ውስጥ በፍፃሜው ላይ ስምምነት እንዳለ ነው።
 
ሁሉንም አበጥረን፤ አንተርትረን፤ አበራይተን ስለምናውቀው በጥንቃቄ፤ በፍጹም አትኩሮት እንከታተለዋለን። የማህበረ ኦነግ ልዋጭ ዘመን አይደለም እኛ የኦሮሞ ህዝብም የሚመኜው አይመስለኝም። ሁሉም ታይቷል። ሁሉም ተመዝኗል። ሁሉም ሁለመናው ተፈታትሿል።
ለኢትዮጵያ ፖለቲካ የ፰ ወይንም የ፲ ዓመታቱ ሂደት ብቻ ዩንቨርስቲ ነው። 
 
ደግሞ ደጋግሞ፤ እንደገና ደግሞ ደጋግሞ መውደቅ ለቀብር ይሆናል። ቀብርን የሚናፍቅ አንጋች መንፈስ ደግሞ ከአማራ ልጅ ይኖራል ብየ አላስብም። ከሁሉ የሚገርመኝ የሰማይ እና የምድር ንጉሥ፤ የሰማይ እና የምድር ልዑል፤ የሰማይ እና የምድር ገዢ የፈጣሪ ፈቃድ በየትኛውም ውይይት አላዳመጥኩም። አዳምጨም አላውቅም።
 
ያን ገናና፤ ተፈሪ እና አይደፈሪ የዓድዋን የደነደነ፤ የገነገነ የዞግ ሥርዕወ - መንግሥት በሰው እጅ ሥራ ዳንቴል የተፈጸመ አልነበረም። ወደፊትም አንዲት ስንዝር መራመድ አይቻልም ከአማኑኤል ፈቃድ ውጪ። ፕትርክናም ሆነ የአገር መሪነትን የሚወስነው ምኞት አይደለም። የእዮር ቅብዓ እንጂ። 
 
ቅብዓው ቢኖር የትኛውን ምክንያት ጥሶ እንዳሰቡት ዶር ለማ መገርሳ መሆን ይችሉ ነበር። የሆነ ሆኖ የኦሮማራ ቲም ሁሉም ብጹዑ፤ ሁሎችም ፃድቅ ሆነው ሰብዕናቸው ይገነባል። በዳይ ሆኖ ሲገለጽ በበዛ ስንክሳር እማዳምጣው አንድ የክፋ ሃሳብ ካፒቴን ብቻ እንደነበር ነው። ለማድመጥ አሰልቺ ነበር - ለእኔ። ያቅራልም። ህሊና ዳኝነቱን ተዘርፏል ባይም ነኝ። 
 
የገረመኝ ዶር ለማን ለማግኜት ቀጠሮ እንዲስተጓጎል ሳይቀር፤ ወጣት የኦሮሞ ሊቃናት ወደፊት እንዳይመጡ የበርሊን ግንቡ የሆነው ያው የክፋ ሃሳብ ካፒቴን መሆኑ ይነገራል። ይተነተናል። ለህወሃት ቁንጮወችም አደግዳጊ አድርባይ ይኽው መንፈስ። ለህወሃት ሰጥ ብሎ ያላረገረገ ማን አለና? አሁንም ህወሃት ይመለስልን የሚሉ የፖለቲካ ሊቃናት እና ሚዲያወቻቸው እኮ አሉ። እያዬንም ነው። 
 
እንዲህ ዓይነት ድርትርት ያሉ ሃሳቦች ለላቀው የፖለቲካ ሳይንስ ተፈጥሮም፤ ዲስፕሊንም አይመጥንም። የኢትዮጵያ ትውልድ ግን ያሳዝነኛል። ሁልጊዜ ድክመትን፤ ግድፈትን፤ ጭካኔን በወቅቱ የሥልጣን ተካፋይ መንፈሳት ሁሉ ባለድርሻ አካላት መሆናቸው እየተፈቀፈቀ በአንድ መንፈስ ላይ መካብ የተገባ አይመስለኝም። ለወደፊትም አይጠቅምም።
 
 ዛሬም፤ ነገም ሊታወቅ እንደሚገባ አበክሬ መግለጽ እምሻው ሁሉም ባጠፋው ልክ ሊጠየቅ ይገባል ከሚለው አስማሚ ሃሳብ ላይ ወጥ አቋም ሊያዝ ይገባል። ወጣት ተገድሎ ተዘቅዝቆ የተሰቀለበት፤ ሰው ተገድሎ የተቃጠለበት፤ የቡራዩ የቅዱስ የኋንስ ሰማዕትነት በኢትዮጵያ የተደገመበት ትራጀዲ የቅርብ መሪ ማን እና ማን ነበሩ???
 
በሌላ በኩል ደግሜ ማስገንዘብ የምሻው ጉልላት ጉዳይ፤ ጥላቻን የሚጸየፍ ሚዲያም ሆነ ፖለቲከኛ በጥላቻ ውስጥ ሆኖ የኔታ ሊሆን ፈጽሞ አይችልም። ጥላቻን፤ ጥላቻ አይፈውሰውምና። ሙግት የሃሳብ ከጥላቻ ጸድቶ ሊሆን ይገባል። ስንት ፋክት እያለ የኢትዮጵያ ተስፋ እና ራዕይ እንዲህ ጉስቁልቁል ባይል ምኞቴ ነው። 
 
ለዚህም ነው ሁለቱን ዓመት ባመዛኙ በማድመጥ ያሳለፍኩት። ወደፊትም በጥንቃቄ ሁሉንም ጉዳይ ነው እምከታተለው። የገረመኝ ቁምነገር ዶር ሚልኬሳ ከአንከር ቆይታቸው "ለማ ሥልጣን አይፈልግም ነበር። ኢትዮጵያን በጋራ ለመምራት መቻሉ ነበር የእሱ በኽረ አጀንዳ፤ ደመቀም ቢሆን ግድ አልነበረው፤ ዶር ወርቅነህ ገበየሁ ቢሆኑም ግድ አልነበራቸውምን ማለት ነው? ያ ከሆነ ስለምን ወደፊት አላመጧቸውም።
 
የዶር ለማ መገርሳ ስልጣን አለመፈለግ ሳይሆኖ መርኽ አንቆ ያዘ። እሳቸው እኮ ፖለቲካ ሳይንስን ሲማሩ፤ ኦህዴድን ሲቀላቀሉ የማንን ጎፈሬ ለማበጠር ነበር ለሥልጣን ካልሆነ? የኦሮምያ ፕሬዚዳንት ይሁኑ ሲባሉ አልሆንም ብለው ያመለከቱበት ሰነድ ካለም ቢገለጽልን ደስታውን አልችለውም።
 
ቀድሞ ነገር የኢህአዴግ ፓርላማ ትልቁ አካል ከዶር ለማ መገርሳ ይልቅ ተመራጭ አባሉን ዶር አብይ አህመድ አሊን ያውቃል። ስለዚህ መርኽን ቆየን ብንል እንኳን የፖለቲካ ሲነሪትን ስናይ ዶር አብይ አህመድ ሲኔር ፖለቲከኛ ናቸው ከዶር ለማ መገርሳ ይልቅ። በሌላ በኩል ዶር ለማ መገርሳን ማግኜት ሰማይ ደጅ እንደ ነበር ሟቹ ዲፕሎማት አንባሳደር ካሳ ከበደ ሲናገሩ ሰምቻለሁኝ። ይህን የኪሎምንጃሮ ተራራ የከፋው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዴት ሊወጣው ይችል ነበር?
 
በሌላ በኩል ኦህዴድ የጠቅላይ ሚኒስተርነት ቦታ ይገባኛል ብሎ ወሳኙስ አስወሳኙስ ማን ሆነ እና ነው ሥልጣን በአፍንጫየ ይውጣ ሊሉ የሚችሉት ዶር ለማ መገርሳ። "የፈለገ ቢሆን ግድ አልነበረውም ለማ" እምንባለው ዛሬ?
 
በሌላ በኩል ዶር አብይ አህመድ እኮ በመንግሥት ሥርዓት ውስጥ የኢህአዴግ ካቢኔ አካል የነበሩ፤ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር የነበሩ እንዴት የትውልድ አድርገው እንደገነቡት ህወሃትን በብዕሬ እየታገልኩ እሳቸውን ግን እከታተል ነበር። ከዛም ቀድሞ የኢንሳ መሥራች ከሆኑት ጋር አብረው የሚጠሩ ናቸው። 
 
በሠራዊቱ ውስጥ የተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይል አባል የነበሩ፥ በአካልም በሩዋንዳ የሠሩ፤ ባድመ ጦርነት ላይ በሙያቸው የተሳተፋ መሆናቸው ዝክረ ታሪካቸው ይገልፃል። ይህን ተመክሮ እና ልምድ እንደ ማበሻ ጨርቅ ጠቅልለህ የትም መጣል ህሊናዊ ዳኝነትን መሸሸት ይሆናል። ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ በመንግሥት አደረጃጀት እና አሰራር በቂ ተመከሮ አላቸው። 
 
ከሚኒስተርነት ወደ ጠቅላይ ሚር ለመሸጋገር በማህል ጋፕ የለም። ይኑር ከተባለ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተርነት ብቻ ነው። ይህ ዕውነት ነው። ትውልድ ዕውነትን እየተማረ ማደግ ይኖርበታል። ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ዕድል በሰጣቸው ቦታ ያገኙት ልምድ እና ተመክሮ የኢትዮጵያን ዕንባ ለማበስ፤ አይዞሽ ለማለት፤ ለማጽናናት ቻሉ ወይ? ይህን ነው እኔ እምሞግተው። 
 
ሳይንስና ቴክኖሎጂ የነበረው ሰባዊነት የት ተሰዶ ይህን ያህል የጭካኔ ቡፌ ኢትዮጵያ ዳግም እንድትሸከም መደረጉ ለምን ነው ሙግቱ? የትምህርቱም ጉዳይ ቢሆን ቀደምቶቹ ኢትዮጵያን ያበጁት ከየትኛው ዩንቨርስቲ ተመርቀው ይሆን። ከሊቅነት ሊህቅነት የሰማይ ስጦታ ስለሆነ ለርህርህና እና ለገርነት ይቀርባል የሚል ዕምነትም አለኝ። ያለቁ አጀንዳወች ዲሪቶ በዛባቸው። 
 
ሌላ ውሽክ እያደረገኝ ያዳመጥኩት ሥማቸውን ብዕሬ ነክቶት የማያውቀው የህወሃቱ ልቦና አቶ ጌታቸው አሰፋን አስመልክቶ ያነሱት ነጥብ ነው ዶር ሚልኬሳ። ዶር አብይ አህመድ ከአሜሪካ ስደት ሲመለሱ ለአቶ ጌታቸው አሰፋ አበባ አበረከቱ የተባለው ነው። ሥጦታ መስጠት ይወዳሉ ዶር አብይ አህመድ። ሳይንስ እና ቴክኖሎጂም እያሉ ይህንኑ ሲፈጽሙ ነበር። መሪ ከሆኑ በኋላም የታዘብኩት ያን ማስቀጠላቸው ነው። ስንት ፋክት እያለ የቂም ቅርፊት መፈለጉ ያው ቡቡው የአማራ ልብን ለመሳብ ሆን ተብሎ የተሰነቀረ ትንታ ነው - ለእኔ። በሰል ያለ ተደራሽ መሆን የሚችል ፋክት ይቅረብ። ለብለብ በቃ! ሆታም! ይገለማል።
 
ዶር ለማ መገርሳ በ18ኛው/ በ19ኛው/ በ20ኛው/ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ያልተሞከረውን አገገኛ ክስተት ያስጀመሩ ናቸው። የመጀመሪያው መቅድመ አሉታዊ ዴሞግራፊን ኢትዮጵያ ውስጥ ዕውን ያደረጉ ሰው ናቸው። ይህ ከየትኛው የዓለም የፖለቲካ መስመር እንደሚያሰልፋቸው ይመዘን። ፋሺዝምን መናፈቅ ነው። የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ዕልቂትን መናፈቅ ነው። ፋክቱ ወደዚህ መስመር ስለሚያቀና። እኔ ቲም ለማን ይሁን ቲም ገዱን በቀና ተቀብየ ብዙ፤ እጅግ ብዙ ለዕውቅናቸው ደክሜያለሁኝ። 
 
እንደ እኔ በስልት እና በጥንቃቄ ዕድሉ ፈሶ የህወሃት የጭካኔ መንፈስ አገርሽቶ ወደ ፋሺዝም እንዳይሸጋገር ያሳወቀም የለም። ኦሮማራ ባይሳካ አንድም ሊቅ አይተርፍም ነበር። ሁሉም በህወሃት መጎማጀት ሲጥ ይሉ ነበር። ስለሆነም በሽግግሩ መሪወች ላይ አንዳች አደጋ እንዳይደርስ ሥማቸው ሁሉ ነበር የተሰጠው። ምክንያቱም ኢህአዴግን ሞግተን ከዛ የወጣ ጢስ ማሾ ይሆናል ብለን አጋጣሚውን ላለማፍሰስ። 
 
የዶር ለማ መጨመት ልቤን የሚገዛው ጉዳይ ነበር። ምስክርነቴ የገዘፈ ነበር። ግን ቃላቸውን ያልጠበቁ፤ በቃላቸው ያላገኜኋቸው ሰው ናቸው። አዋርደውናል። የአሁኑ ዝምታቸውን ግን እጅግ ነው እማከብረው። የሳቸውን ብቻ ሳይሆን የኢዜማውን አቶ አንዱዓለምን ስክነትንም። 
 
በመጨረሻ የምለው በተለይ የፖለቲካ ሳይንስ ሊቃናት ሙያውን በሚያስከብር አቀራረብ እና ፍልስፍና ልጆቻቸውን ማለት አዲሱን ትውልድ ይቀረጽ ዘንድ ሊፈቅዱ ይገባል። አማተር አይደሉም። ከሌላ ሙያ ጋር ተዳብለው አይደለም እና ሃሳብ የሚያጋሩት። ወይንም የሚታገሉት። ፋክት - ገብ ፤ ዕውነት - ወዳጅ፤ መርኽ - አፍቃሪ ትውልድን ለማፍራት ከእያንዳንዳችን በግል፤ ከሁላችንም በጋራ የሚጠበቅ መብታዊ ግዴታቸን ነው። ዕውነት የስሜት መናጆ ሊሆን አይገባም። ሰብአዊነትም የማይክ ሜካፕ ሊሆን አይገባም። መርኽ ባጣ ቆየኝ ሊሆን አይገባም።
 
አቶ ጃዋር መሃመድ (ሃጂ)ከሃሳብ ቡፌ ጋር በነበረው ቆይታ "ታየ የተናገረው ነገር ሚስጢር አይደለም!" ይላል። እስኪ እሱ ሚስጢር የሆነ አመክንዮ የሚያውቀውን ይንገረን። ለምሳሌ የመስከረም 2011ቱን ለኦነግ አቀባበል 5 የአዲስ አበባ ነዋሪወች በአደባባይ ተረሽነዋል። ከዛ ቀድሞም ሰማዕትነት ማህል አዲስ አበባ ላይ ሀምሌ 19/2010 ዓም ኢንጂነር ስመኜው ተቀብለው፤ በታሪክ የጭካኔ ፈር ቀዳጅ የሆነ የአማራ ሊቃናት በመናህሪያ በዓታቸው ተረሽነዋል። ዕውነት ፍንጭ መተንፈሻ ሲያገኝ ከፋክክሩ ይልቅ ተጨማሪ ጭብጦችን ይዞ መቅረብ እንጂ የተለመደው ፋክክር ቢጤ ማጣጣል ይሁን መጣያ ሰልችቶናል። 
 
ድንግል እመቤቴ ሆይ! ምህረት ነሽ እና ምህረቱን አሰጪን። እባክሽን? 
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ ከብረቶቼ። አሜን።
ደህና ሰንብቱልኝ። አሜን።
ደህና እደሩልኝ። አሜን።
 
አባ ቅኑ ገራገር አማራየ እግዚአብሄር // አላህ አምላክህ እንዲህ ይልኃል ……
" እግዚአብሄርን እመነው እንጂ ይረዳሃል፤ ሥራህን አቅና በእሱም እመን።"
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
26/06/2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ሰውኛ እና ተፈጥሮኛ ዘመን ፈጣሪ መርቆ ያምጣልን። አሜን።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?