የኦሮሞ የተዋህዶ ልጆች የፈተና መባቻ።
ልባዊነት። „አቤቱ ለምን ርቀህ ቆምህ?“ መዝሙር ፲ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ 09.11.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ቋንቋ ጥበብ ነው። ቋንቋ እውቀት ነው። ቋንቋ ስልጣኔ ነው። ቋንቋ እድገት ነው። ቋንቋ ልሳን ነው። ቋንቋ ሙያ ነው። ቋንቋ ፍልስፍና ነው። ቋንቋን በሚመለከት ያለኝን እይታ በዚህ ፁሑፌ ማገናዘብ ይቻላል። https://sergute.blogspot.com/2018/05/blog-post_6.html ቋንቋ ሊቀ ሊቃውንትነት እን ጂ መወቀሻ ሊሆን አይገባም። ከአምስቱ የኦሮሞ ድርጅቶ የመብረቅ ወሳኔያዊ መግለጫ ማንፌሰቶ ወዲህ አማራ ግዕዝን በሁተኛ ቋንቋነት እንዲያጠና ዘመቻ መጀመሬ ይታወሳል። አሁን ዛሬ ከትኩስ መረጃ ዩቱብ አንድ መረጃ አገኘሁኝ። እኔ ግዕዝን የአማራ ህዝብ ማጥናት አለበት ያልኩት ለእኔ ለራሴ የትንቢት ያህል ነው የዛሬን መረጃ ሳገኝ የተሰማኝ። በወለጋ ብጹዕና አባቶቻችን መሰደዳቸው ብቻ ሳይሆን በቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት የያሬድ ዜማዊ ቅኝትም፤ በግዕዝ ቅዳሴም እንዲቆም መደረጉን አዳመጥኩኝ። ዝርዝርዝሩን እናንተው ሂዱበት ከሥር ሊንኩን እለጥፋለሁኝ። ዋና ቁም ነገር ግን ዛሬ የተፈቀደው የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የግዕዝ እግዳ ነገ ሃይማኖቱም እንዳይቀጥል የመጀመሪያው የክፉ ቀን ደወል ነው። የግራኝ ዋዜማ። የዳውዳውያን እና የጃውርውያን ፍልስፍና ይሄው ነው። „ቀስ እያለ እንቁላል በእግሩ ይሄዳል“ የሚበለውን ልብ ትሉ ዘንድ በአክብሮት እግልጻለሁኝ። አሁንም ቅድምም ከኦነጋውያን ጋር ያለው ድርድር ትውፊታችን ላይ የተቃጣ፤ ማተባችን ላይ የተቃጣ፤ በአብሮነታችን የተሳለ ሰይፍ ሊያመጣ ስለመቻሉ የህሊና ዝግጁነት የሚያስፈልግ ይመስለኛል። ቅኖቹ ዶር ለማ መገርሳ...