ልጥፎች

#ቀናሁኝ! ኢትዮጵያ ትሰብበት! 2) እማ ሆይ! የአንችስ ቀንሽ መቼ ይሆን? የህሊና ስልጣኔ ያላስቀና ምን ያስቀናል?

  #ቀናሁኝ !    የህሊና ስልጣኔ ያላስቀና ምን ያስቀናል? የሃሳብ ፋክክር #በመደማመጥ ተከውኖ #ስኬቱን ከማዬት በላይ ምን ያስቀናል?   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   ከማግኔቱ የአሜሪካ 2024 የምርጫ ፋክክር እና ክወና አቮላዊ ሙቀት ሳንወጣ ሌላም መልካም ሂደት ለማዬት በቃን። እንዲህም ሆነ …… ከጉንፋኔ ጋር እዬታገልኩኝ #የሱማሌላንድን አጓጊ እና ሳቢ የምርጫ ፋክክር በተለያዩ ሚዲያወች ስከታተል ሰነበትኩኝ። ግን ማህበረ - ቅንነት እንዴት ሰነበታችሁልኝ???    60 ዓመት የባከነውን ጊዜ፤ ጉልበት፤ መንፈስ አሰብኩት። በፋይዳ የለሽ ብክነትም እያንዳንዳችን በግል ሁላችንም በጋራ #ብትለታችን ለዚህ መሰል ህዝበ ጠቀም አቅም አለመብቃቱ #አሳፈረኝ ። ያቺ ትንሽ በቅኝ ግዛት የማቀቀች፤ እንደኛው ድሃ በሚባሉት ተርታ የምትገኝ የአህጉራችን ቤተኛ ሱማሌላንድ ለዚህ ክብር፤ ለዚህ ልዕልና፤ ለዚህ ልቅና መብቃቷ እጅግ ደነቀኝ። እጅግም አስቀናኝ። #ቅን የፖለቲካ #ሊቃውንት እና #ሊሂቃን ያላት መሆኗንም በጥልቀት አስተዋልኩ። ከዚህ ጋር ለሰባዕዊነት ያላቸውን አትኩሮትም ተማርኩበት። ለሰው ልጅ ሰውነቱን ከማክበር፤ ለዛም ከመጠንቀቅ በላይ ምን የመሪነት ዊዝደም አለና።   እንሆ ስልጡኖቹ የሱማሌላንድ ልጆች ተሳፋቸውን ሰንቀው፤ ተስፋቸውንም አሰልጥነው ጉዟቸውን በአብነት አስከበሩት። #ብርቱካኖች አሸነፋ። ብርቱካኖች ሲያሸንፋ በሰፋ ልዩነትም ነው። ገዢው ተሸናፊው ፓርቲም ሽንፈቱን ገና ሳያውቅ እኩል የፋክክር ሜዳ ፈቀደ። ይህ ልዕልና ስልጣኔ #የውሃ ልክም ነው። ሚዲያወች እኩል አገለገሉ። በመከባበር ላይ የታደመው ተፎካካሪ ህዝብ ግራ ቀኙን በጥሞና አዳመጠ። ቀኑ በጉጉት ተጠበቀ። ታዛቢወችም የደከሙበት ሂ...

"ኢትዮጵያ በየዓመቱ በ2 ሚሊዮን የሚጨምረውን ሕዝቧን መግታት ያስፈልጋት ይሆን?" BBC

    https://www.bbc.com/amharic/articles/cgeyzg382rjo ኢትዮጵያ በየዓመቱ በ2 ሚሊዮን የሚጨምረውን ሕዝቧን መግታት ያስፈልጋት ይሆን? 15 ህዳር 2024 "የተባበሩት መንግሥታት የዓለም ሕዝብ ከ40 ዓመታት በኋላ 10.4 ቢሊዮን እንደሚደርስ ትንበያውን አስቀምጧል። በዚህ ትንበያ ሕንድን ጨምሮ ስምንት የዓለማችን አገራት የዓለማችንን ግማሽ ሕዝብ ይይዛሉ። ከእነዚህ ስምንት አገራት ውስጥ ደግሞ ኢትዮጵያ ትገኝበታለች። የኢትዮጵያ የሕዝብ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው። በየዓመቱም በሁለት ሚሊዮን ይጨምራል። የተባበሩት መንግሥታት የሥነ ሕዝብ ፈንድ በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት የኢትዮጵያ አጠቃላይ የሕዝብ ብዛት 129.7 ሚሊዮን ደርሷል። ይህ ቁጥር በ28 ዓመታት ውስጥ እጥፍ ሊሆን እንደሚችልም ተተንብይዋል። በዚህ ትንበያ መሠረትም በ2044 የኢትዮጵያ ሕዝብ 259.4 ሚሊዮን እንደሚሆን ይጠበቃል። ይህም በሕዝብ ብዛቷ ከአፍሪካ ግንባር ቀደም የሆነችው ናይጄሪያ አሁን ካላት የሕዝብ ብዛት ይልቃል። ለመሆኑ የኢትዮጵያ የሕዝብ ብዛት መጨመር ምክንያቱ ምንድን ነው? መጨመሩስ ምን አደጋ ይዞ ይመጣል? ምንስ ዕድል አለው? በተባበሩት መንግሥታት የሥነ ሕዝብ ፈንድ የሥነ ሕዝብ እና ልማት ፕሮግራም ተንታኝ የሆኑት ወ/ሮ ገዙ ብርሃኑ፣ የሕዝብ ቁጥሩ ለመጨመሩ ምክንያቶችን ለማወቅ ሦስት መሠረታዊ ጉዳዮችን ማንሳት የግድ ነው ይላሉ። እነዚህም ውልደት፣ ሞት እና ፍልሰት ናቸው። የአንድ አገር የሕዝብ ቁጥር የሚወሰነውም እነዚህን ከግምት በማስገባት ነው። የውልደት እና የፍልሰት መጠን ሲጨምር እና የሞት መጠን ሲቀንስ የሕዝብ ቁጥር ላይ ጭማሪን ያስከትላል። ተንታኟ እንደሚሉት በኢትዮጵያ የውልደት እና ...