የሃይማኖት ተቋማት የህዝብ ሰቆቃ አጀንዳቸው አይደለም።
ሃይማኖት ምንድን ነው? „ልጄ የበደልከው በደል የሳትከው ነገር አንዳለ እወቅ ከዚህ በኋዋላ ዳግመኛ አትበድል ስለ ቀደመው ሃጢያትህ ንስሓ ገብተህ ተቀመጥ።“ መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፳፩ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ© ሥላሴ 02.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። እኔ ውዶቼ ስለ ሃይማኖት ፍልስፍና ልናገር አይደለም። ይህ ጸጋ የአቨው የሃይማኖት ሊቃውንት መክሊት ነው። ሃይማኖት ማለት ምንድን ነው ብዬ የምጠይቀው ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የሃይማኖት ተቋማት ከንፈር ከመምጠጥ በስተቀር በዚህ የመከራ ቀን ከህዝብ ጎን ሊቆሙ አለመቻላቸው ሃይማኖት አለ ኢትዮጵያ ውስጥ ለማለት ከበደኝ። የእውነት ከበደኝ ሃይማኖት አለኝ ለማለትም። የእውነት ይጭነቃል። ጂጂጋ ላይ ያን ያህል ሐዋርያት ሲታረዱ፤ አድባራት ሲነዱ፤ ምዕማናን ያን ያህል መከራን ሲቀበሉ አንድም ልዑክ ከቅዱስ ሲኖዶስ ተልኮ ሄዶ ቦታውን እስከ አሁን ድረስ አላዬም። ለመሆኑ ፕትርክና ምንድን ነው? ምዕመናን እቦታው ድረስ ሄዶ ካላጽናን? ዓምት ሙሉ መፈናቀል? ዓመት ሙሉ በሰው ሰራሽ ችግር እንዲህ ፍዳ መክፈል። ተቆጭ የለ። መካሪ የለ። የሚገስጽ የለ። ግርጫማ ጸጉር ያለው የለ። የሚፈራ የለ። በሃይማኖታዊ ተቋማት ለተጎዱት አንዳችም ነገር አልተደረገም። ማውገዙን እማ እኛ ድሆችም እናወግዘው የለ። በቃ ሚዲያ ላይ ወጥቶ መናገር የሃይማኖት አባትነት ያሰጣልን? ሃይማኖት ለዚህ መከራ ቅርብ ካልሆነ ማን ሊሆን ነው? በዬቦታው ለቅሶ ነው። በዬቦታው ዋይታ ነው። የመንግሥት መሪዎችን አይገስፁ የሚቆጣቸው የለ፤ የሃይማኖት አባቶች ቸልተኞች እና ግድየለሾች። ለነገሩ የራሰቸው ገማና ከሆነስ? ሌላው ቀርቶ ቡራዩ ላይ እስከ ...