ልጥፎች

የኢትዮጵያ ጤና ሚር ያወጣው አዲስ መግለጫ።

ምስል
 

#ወይ #ጢቾ? #የጢቾን የቀደመ ጥልቅ #ተፈጥሯዊነት #አቤቱ #የኦህዴድ #ሊቃናት #መልሱልን።

ምስል
  #ወይ #ጢቾ ? #የጢቾን የቀደመ ጥልቅ #ተፈጥሯዊነት #አቤቱ #የኦህዴድ #ሊቃናት #መልሱልን ።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ። አሜን።     #ጠብታ ።    ከየት እንደምጀምር አልውቅም። እኔ ለምለሙን ጢቾ እማውቀዋለሁኝ። ጢቾሻን እኔ የማውቀው ግን በዚህ አሰቃቂ ግፍ እና ሰው ጠል በሆነ፤ መስቀልን ገፊ #የማፈናቀል ታሪክ አልነበረምና ከበጎው ከናፍቆቴ ልነሳ። በአሜሪካኖች ሃሙስ በእኛ አርብ ነበር አደባባይ ሚዲያ ካርታውን ሲያቀርብ ጢቾም እንዳለበት የተገነዘብኩት። ቀደም ብሎም ምስራቅ አርሲ የሚል ጉግል ላይ ፈልጌ በጉልህ ላገኜው አልቻልኩም።    በእኛ አርብ ዕለት ግን አደባባይ ሚዲያ በጉልህ ሲያወጣው ማህጸኔ እንደ ዱባ ነው የተቀረደደው። አደባባይ ሚዲያ ገረጭራጫ ሚዲያ አይደለም፤ በስሜት ግንፍል ግንፍል የሚልም ሁነትም በርክቶ አላይበትም። በቃላት አጠቃቀም፤ በቅደም ተከተል አመክንዮወች፤ ሃሳብን በልዩነት አቻችሎ በማስተናገድም #ስክነት ስለማይበት በመደበኛ እከታተለዋለሁኝ። የቲሙ የሃሳብ ፍልሚያም ለትውልድ የመቻቻል ቀጣይነት አቅጣጫ ጠቃሚ ይመስለኛል።   "የጊዜ ባለቤት" ብሎ አምላካችን አመስግኖ የሚጀምረው የመምህር አቤል ጋሹ በር ከፋች ቃለ ህይወትም ይናፍቀኛል። #ይጠራኛልም ። ያው ልጅ ተክሌ እና እኔ ስንሟገት ነው የኖርነው፤ በቀረበበት ሚዲያ ሁሉ ናፍቄ አዳምጠዋለሁኝ። ቅንም ነው። አይሰስትም ትጉኃንን አጉልቶ ለማውጣት። ለኮሚኒቲውም ነፃ አገልጋይ ነው።    ባለቤት አልባ እስረኞችን ኢትዮጵያ ሲሄድ በአካል ያያል። ቀጠሮ ካላቸው በአካል ይገኛል። ሁነኛ #ተስፋዬ ነው። እኔ ኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኛ እንዲኖራት ፈጽሞ አልሻም እና ለእኔ በኽረ ጉዳዬ ነው...

ተስፋ ሰጪ ዜና WHO ምስጉን ተግባር ፈጸመ። (ከኖር በእግዜር ፔጅ ከጉታማ ካራሌ ሼር የተደረገ ነው። ፎቶውንም የወሰድኩት ከዚው ፔጅ ነው።)

ምስል
  ተስፋ ሰጪ ዜና ከኖር በእግዜር ፔጅ ከጉታማ ካራሌ ሼር የተደረገ ነው። ፎቶውንም የወሰድኩት ከዚው ፔጅ ነው።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።     እንዲህ ፈጣን እና የተደራጄ የርህርህና እርምጃ ተስፋ ይሰጣል። ያጽናናል። አይዟችሁን በአጽህኖትም ይልካል። ተመስገን። «አስቸኳይ ዜና!»    «በደቡብ ኢትዮጵያ በቫይራል ሄመሬጂክ ፌቨር (VHF) ወረርሽኝ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ፈጣን ምላሽ ሰጠ!   የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተጠረጠረ የቫይራል ሄመሬጂክ ፌቨር (VHF) ወረርሽኝ ዙሪያ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ከኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ከክልላዊ የጤና ባለስልጣናት ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።»   «የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ 8 ሰዎች በቫይረስ ሊያዙ እንደሚችሉ ተዘግቧል።   WHO ለዚህ ወረርሽኝ ምላሽ ለመስጠት አስቀድሞ የሚከተሉትን እርምጃዎች ወስዷል፦   1. ባለሙያዎች፣ መድኃኒቶችና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች እንዲሁም ለጤና ሰራተኞች የሚሆን የግል መከላከያ ቁሳቁስ (PPE) ወደ ተጎዱ ከተሞች ተልኳል።   2. በወረርሽኙ የተጎዱ ማህበረሰቦች ውስጥ ንክኪን የመከታተል (Contact Tracing) ሥራን ድርጅቱ ይደግፋል።   3. ሊኖር የሚችለውን ድንበር ዘለል ስርጭት ለመከላከል ከደቡብ ሱዳን WHO ቢሮ ጋር በቅርበት እየተሰራ ነው።   4. የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ እንዳስታወቁት፣ ለአስቸኳይ ድጋፍ እንዲውል 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) የአሜሪካን ዶላር ከWHO የአደጋ ጊዜ ፈንድ ለኢትዮጵያ ተለቋል። ድርጅቱ እንደ አስፈላጊነቱ ድጋፉን ...

ይድረስ ለኢትዮጵያ ጤና ሚር // ሚር ክብርት #ዶር #መቅደስ #ዳባ። አዲስ አበባ።

ምስል
  ይድረስ ለኢትዮጵያ ጤና ሚር // ሚር ክብርት  #ዶር #መቅደስ #ዳባ ።   አዲስ አበባ።    "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።       #መቅድም ።    ጤና ይስጥልኝ ክብርት ዶር መቅደስ ዳባ እንዴት ሰነበቱ። ዕንቅልፍ አጥቼ ያደርኩበትን ውስጤን ልልክለወት እንሆ ወሰንኩኝ። ትናንት የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስተር ያወጣውን መግለጫ ከፌስቡክ ፔጁ ላይ አግኝቼ ደጋግሜ አንብቤዋለሁኝ። በአሉኝ የማህበራዊ ሚዲያወች እና ኢሜሎቼም ተጠቅሜ ሼር አድርጌዋለሁኝ። እንዲህ አይነት ድንገተኛ እና አጣዳፊ ሥም አልቦሽ ወረርሽኝ ሲገጥም ከፍጥነት ጋር እርምጃ ለመውሰድ የተደረገ ንቅናቄ መኖሩን አረጋግጫለሁኝ። እርግጥ ነው በግንባር ቀደምትነት ለተሰውት የጤና ባለሙያወች መግለጫው ምንም ያለው ነገር የለም የሚል ቅሬታም አንብቤያለሁኝ። በመግለጫው ላይ ሰመዓታቱን ባልደረቦቹን የጤና ሚር አስቦ ቢሆን ቀጣዩን የገዘፈ ፈተና ለመቋቋም አቅምን በቅንነት ለማሰባሰብ ሆነ በተስፋ እነኛ ንጹኃን የህክምና ባለሙያወች ይሠሩ ዘንድ ይረዳቸዋል። ባለሙያወቹ በተቋማቸው ላይም ሙሉ ዕምነት አሳድረው #አለኝታችን የእኛነት ስሜት ፈጥሮ ውስጥነትን በፈቃደኝነትን ሊፈጥር ይችላል። በሌላ በኩል ይህንን ክፍተት አቻችሎ ችግሩን በወል ለመቋቋም #በሰፊነት ህሊናን ማሰናዳት የሚገባ ይመስለኛል። የጎደለውን ነገር አቅም ያለው እየሞላ፤ የጎበጠውን ነገር እያቃኑ ቢያንስ የአስቸኳይ ጊዜ የወረርሽኙን መከራ ለመግታት በብሄራዊ ጉዳዮች ላይ መረባረብ፤ የተዘናጉ ቦታወች ላይ እንዲህ አክብሮ ማስታወሻ በመላክ መሳተፍ ያስፈልግ ይመስለኛል። "ከሩቅ ዘመድ የቅርብ ጎረቤት" ለዚህ ጭብጤ ልኩ ይመስለኛል። #የነፍስ #አድኑን እንቅስቃሴ በቅንነ...

ለመከላከያ ምርጥ ዘር እና የአዘቦተኛ ዘር ልዩነት የሚጠቅም ጉዞ አይደለም። ለዛውም በዞግ ርዕዮት በምትመራ አገረ - ኢትዮጵያ። የኢትዮጵያ እናቶች የአገርም እናቶች ናቸው ክብርም ሽልማትም የሚገባቸው።

ምስል
  ለመከላከያ ምርጥ ዘር እና የአዘቦተኛ ዘር ልዩነት የሚጠቅም ጉዞ አይደለም። ለዛውም በዞግ ርዕዮት በምትመራ አገረ - ኢትዮጵያ። የኢትዮጵያ እናቶች የአገርም እናቶች ናቸው ክብርም ሽልማትም የሚገባቸው።        "የቤትህ ቅናት በላኝ።"     የአንድ አገር መከላከያ ለእኔ የአገር ሃኪም ነው። ሃኪምነት ሰብአዊነትም ነው የተፈጥሯዊነት ሚስጢርን ለተረዳ አቅም ላለው የአገር ምሶሰነቱን በፖለቲካ ሊቃናት ካልተበወዘ። ሠራዊት፤ ደህንነት፤ የጸጥታ አካላት ጉዳያቸው ሰው ሊሆን ይገባልም። ከግለሰቦች የሥልጣን ፍላጎት ተቋማት ሊሆኑ ይገባልም። በመርኽም በዲስፕሊንም። ይህ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሂደት ሲማጥ የተኖረበት ግን ያልተገላገልነው የፈተና ቋት።   #ምዕራፍ ፲፯   እንዴት አደርን? ጭምቷ ኢትዮጵያስ እንደምን አደርሽ ይሆን? እምዬ ሲዊዝሻ እየኖርኩብሽ የምትናፍቂኝ፤ የማልጠግብሽም የከተማ ገዳሜ፤ ደጓ ቪንትዬስ? ማህበረ ቅንነት የሥርጉትሻ ፔጅ ደጋጎችስ እንዴት ናችሁ።    #እፍታ ።    በኢትዮጵያ የችግሮች ሁሉ መነሻ ምንጭ ይሁን መዳረሻ፤ የመፍትሄወች መቃረቢያ ይሁን የስኬት ሲሳይ የተቋማት ግንባታ አትኩሮት ዝቅተኝነት ይመስለኛል። ተቋም የትውልድን ሽግግር ቅብብሎሽ በሥርዓት የመምራት አቅም የሚኖረው ከአመሰራረት #ጥራቱ ይነሳል። የአንድ ተቋም የሂሳብ ሥርዓቱን ሰነድ ካልተዝረከረከ የዛ ተቋም ብቃት መስካሪ አያስፈልገውም። ራዲዮሎጂው ነው። በኢትዮጵያ እራሳቸውን ችለው፤ እራሳቸውንም አስከብረው ከዘለቁት ተቋማት ውስጥ ዕድለኛው፤ በዕውነትም ዕድለኛው ተቋም የኢትዮጵያን አየር መንገድ ማንሳት በቂ ይመስለኛል። ክብሩ ልዕልናው ዝቅ ከፍ ሳይል የቀጠለው የአመሰራረቱ ጥራት ...