"ኢትዮጵያ በኢንተርኔት ነፃነት ዝቅተኛ ነጥብ ማስመዝገቧ እና የመንግሥታት ቁጥጥር የደቀነው ስጋት bbc

 

·     "  ኢትዮጵያ በኢንተርኔት ነፃነት ዝቅተኛ ነጥብ ማስመዝገቧ እና የመንግሥታት ቁጥጥር የደቀነው ስጋት"

https://www.bbc.com/amharic/articles/c0wwz5l2nvwo

17 ጥቅምት 2024

«በአፍሪካ የኢንተርኔት ነጻነት እየተሻሻለ ቢሆንም ኢትዮጵያ በግጭቶች እና በባለሥልጣናት እርምጃ ምክንያት በይነ መረብ ነጻ ያልሆነባት አገር መሆኗን ፍሪደም ሐውስ የተባለው የመብቶች ተቋም ያወጣው ሪፖርት አመለከተ።

ተቋሙ በአውሮፓውያኑ 2024 የዓለም የኢንተርኔት ነጻነትን በተመለከተ ባወጣው ሪፖርት ኢትዮጵያን ጨምሮ አስራ ሰባት የአፍሪካ አገራትን የነጻነት ይዞታን ያጠና ሲሆን፣ በዚህም ኢትዮጵያ ዝቅተኛውን ነጥብ አስመዝጋባለች።

ጥናቱ ከአፍሪካ አገራት መካከል አንጎላ፣ ግብፅ፣ ኢትዮጵያ፣ ጋምቢያ፣ ጋና፣ ኬንያ፣ ሊቢያ፣ ማላዊ፣ ሞሮኮ፣ ናይጄሪያ፣ ሩዋንዳ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሱዳን፣ ቱኒዚያ፣ ኡጋንዳ፣ ዛምቢያ እና ዚምባብዌን የዳሰሰ ነው። በዚህም መሻሻሎች እንዳሉ የጠቀሰ ቢሆንም ኢትዮጵያን ጨምሮ በአንዳንድ አገራት የበይነ መረብ ነጻነት ተሸርሽሯል ብሏል።

ጥናቱ የአገራቱን የኢንተርኔት ነጻነት ይዞታ 100 ነጥቦች የመዘነ ሲሆን፣ ዝቅተኛውን ወይምነጻ ያልሆነየሚል ደረጃን ያገኘችው ኢትዮጵያ 27 ነጥቦችን አግኝታለች። ደቡብ አፍሪካ ደግሞ ከፍተኛውን 74 ነጥብ በማግኘት የኢንተርኔት ነጻነት ያለባት አገር እንደሆነች ሪፖርቱ ጠቅሷል።

ፍሪደም ሐውስ ካጠናቸው የአፍሪካ አገራት መካከል ሰባቱ እየተጠናቀቀ ባለው የአውሮፓውያን ዓመት መሻሻሎችን ያስመዘገቡ ሲሆን፣ ስድስቱ ግን በኢንተርኔት መብት ይዞታቸው ላይ ማሽቆልቆል መመዝገቡን ሪፖርቱ አመልክቷል።

በተለይ ግጭቶች ባሉባቸው አገራት ውስጥ የኢንተርኔት ነጻነት እክሎት እየገጠሙት መሆኑን ያመለከተው ሪፖርቱ፣ የኢትዮጵያ እና የሱዳን ባለሥልጣናት በአገራቸው ያለውን የፀጥታ ሁኔታ ሰበብ በማድረግ የኢንተርኔት ግንኙነትን ያቋርጣሉ እንዲሁም የበይነ መረብ ጋዜጠኞችን ያሳድዳሉ ብሏል።

·        ኢንተርኔት የተጋረጠበት ስጋት

የኢንተርኔት ነጻነት መገደብ ከጊዜ ወደ ጊዜ አስጊነቱ ጨምሯል።

ናይጄሪያ ሌጎስ ውስጥ 45 ሺህ ኪሎ ሜትር የሚረዝም የኢንተርኔት መስመር ተዘርግቷል። በባሕር ውስጥ ተጉዞ እስከ ከተማዋ ይደርሳል።

አፍሪካየተባለው በባሕር ውስጥ የሚተላለፍ የኢንተርኔት መስመር ላለፉት አራት ዓመታት በቢሊዮን ዶላሮች ወጪ እየተዘረጋ ነው።

አውሮፓን፣ እስያን እና አፍሪካን ያስተሳስራል።

ይህ መስመር የተሻለ የኢንተርኔት ዝርጋታን የሚያረጋግጥ፣ የመረጃ ፍሰት ነጻነትን የሚያስጠብቅ እንዲሁም 46 የተለያዩ መስመሮች 33 አገራት የሚደርስ ነው ተብሏል።

የተወሰኑ የመስመሩ ክፍሎች ቢሠሩም ሙሉ በሙሉ አገልግሎት የሚጀምረው በቀጣይ ዓመት ነው። አሁን በአፍሪካ ጥቅም ላይ እየዋሉ ካሉ በባሕር ወለል ላይ ከሚገኙት ኬብሎች በአጠቃላይ የሚበልጥ አገልግሎት ይሰጣል።

ሜታ፣ ቻይና ሞባይል እና ቮዳፎንን ጨምሮ ሌሎችም የቴክኖሎጂ ተቋማትን ያሳተፈ እንዲሁም ከፍተኛ ወጪ የፈሰሰበት ፕሮጀክት ነው።

አፍሪካከዓለም ሕዝብ 70 በመቶውን በኢንተርኔት ለማስተሳሰር ዕቅድ ይዟል።

ኢሜል ለመላክ፣ በበይረ መረብ ቪድዮ ለመመልከት እና ለሌሎችም አገልግሎቶች ከባሕር በታች የተዘረጉ መስመሮችን እንጠቀማለን።

አንዳንድ አገራት በቀላሉ ሊቋረጡ የሚችሉ ኬብሎች ላይ የተመሠረተ የኢንተርኔት መስመር ዝርጋታ አላቸው።

 

የምስሉ መግለጫ, ቱአፍሪካ የተባለው በባሕር ውስጥ የሚተላለፍ የኢንተርኔት መስመር ላለፉት አራት ዓመታት በቢሊዮን ዶላሮች ወጪ እየተዘረጋ ነው።

ዓሣ ከማስገር ጋር በተያያዘ በሚያጋጥም ጉዳት፣ በመሬት መንቀጥቀጥ፣ በመሬት መንሸራተት እንዳንድ ጊዜ ደግሞ ሆነ ተብሎ በሚፈፀም ጥቃት የኢንተርኔት አገልግሎት ሊቋረጥ ይችላል።

ዋነኛው ስጋት የሚመነጨው ግን ከመንግሥታት ነው።

ቶፕ10ቪፒኤንባወጣው መረጃ መሠረት በአንድ አካባቢ ወይም አገር ውስጥ ኢንተርኔትን ማቋረጥ በአሁኑ ወቅት እየጨመረ መጥቷል።

የምስሉ መግለጫ, ሜታ፣ ቻይና ሞባይል እና ቮዳፎንን ጨምሮ ሌሎችም የቴክኖሎጂ ተቋማትን ያሳተፈና ከፍተኛ ወጪ የፈሰሰበት ፕሮጀክት ነው።

ፈተና ላይ ኩረጃን ለመከላከል ወይም የተቃውሞ ድምጽን ለማፈን በሚል ኢንተርኔት ከሚቋረጥባቸው አገራት መካከል ሕንድ በግንባር ቀደምነት ትጠቀሳለች።

በዚህ ዘርፍ ባለፉት ዓመታት ኢትዮጵያም የፈተና ኩረጃ እና የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችን ለመቆጣጠር በተደጋጋሚ ኢንተርኔት ማቋረጥ ከአፍሪካ ትጠቀሳለች።

ይህ በመንግሥታት የሚፈጸመው የኢንተርኔት አገለግሎትን የማቋረጥ ድርጊት በተወሰኑ አገራት ውስጥ ብቻ የሚያጋጥም ሳይሆን በርካቶች እንደፈለጉ የሚፈጽሙት እየሆነ ነው።

ከአውሮፓውያኑ 2019 እስከ 2023 ባሉት አምስት ዓመታት ኢንተርኔትን መዝጋት በከፍተኛ መጠን እየጨመረ መጥቷል።

  • 2019: 134 የኢንተርኔት መዝጋት ተመዝግቧል
  • 2020: 93 የኢንተርኔት መዝጋት ተመዝግቧል
  • 2021: 57 የኢንተርኔት መዝጋት ተመዝግቧል
  • 2022: 130 የኢንተርኔት መዝጋት ተመዝግቧል
  • 2023: 225 የኢንተርኔት መዝጋት ተመዝግቧል

በሕንድ ኢንተርኔት ማግኘት የሕዝብ መብት ሳይሆን የመንግሥት መገልገያ መሣሪያ ተደርጎ ይወሰዳል።

ኢንተርኔት መዝጋት እየተባባሰ ከመምጣቱ አንጻር የተባበሩት መንግሥታት ኢንተርኔት ማግኘትንቅንጦት ሳይሆን የሰብአዊ መብት አካልአድርጎ ሊፈርጅ እንደሆነ አስታውቋል።

በድረ ገጾች ላይ የሚደረግ ሳንሱርም እየጨመረ መጥቷል።

ባለፉት አምስት ዓመታት የኢንተርኔት ነጻነት እየቀነሰ ይገኛል።

ፍሪደም ሐውስየተባለው የመብት ተከታታይ ተቋም የሠራው ጥናት አገራትን በሳንሱር፣ በስለላ እና የኢንተርኔት አገልግሎትን መዝጋት ከፋፍሎ ያስቀምጣል።

አጥኚዎች እንደሚሉት የኢንተርኔት ነጻነት 13 ተከታታይ ዓመታት ቀንሷል።

በቅርቡ የኢንተርኔት ነጻነት ከቀነሰባቸው አገራት መካከል ኢራን እና ሚያንማር ይገኙበታል።

ቻይና በበይነ መረብ እንቅስቃሴ ማነስ የመጨረሻው ደረጃ ላይ ትገኛለች።

ለምን ኢንተርኔት ይቋረጣል?

ኢንተርኔትን ለመዝጋት የሚውሉ መተግበሪያዎች እየተበራከቱ መሄድ እና መንግሥታት እነዚህን መተግበሪያዎች ለመጠቀም ያላቸው ፈቃደኛነት መጨመር እንደ አንድ ምክንያት ይጠቀሳል።

በናሽናል ዲፌንስ ዩኒቨርስቲ የጥናት ባለሙያ የሆኑት ጃኪ ኪር እንደሚሉት፣ ኢንተርኔት ከመንግሥታት ይዞታ ውጪ ያለ ዓለም አቀፍ መድረክ ተደርጎ ይወሰድ ነበር።

ይሄ አስተሳሰብ ግን የምኞች ዓለም ነበርይላሉ ባለሙያዋ።

ይህ አስተሳሰብ የመጣው ኢንተርኔት እንዴት እንደሚሠራ በአግባቡ ካለመገንዘብ ነው ሲሉ ያስረዳሉ።

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ቢል ክሊንተን በአንድ ወቅት እንዳሉት ሰዎች ኢንተርኔት የሚጠቀሙበትን መንገድ መቆጣጠርተንቀሳቃሽ ነገርን ግድግዳ ላይ ለማቆም እንደመሞከር ነው።

መንግሥታት በይነ መረብን የሚቆጣጠሩበት ጊዜ መምጣቱ አይቀርም ነበርሲሉ ባለሙያዋ ያብራራሉ።

ኢንተርኔትን በመቆጣጠር ቻይናን የቀደማት የለም። ከፍተኛ ወጪ በማፍሰስ ሊታለፉ የማይችሉ ሶፍትዌሮች እና ሀርድዌሮች ተገንብተዋል።

ኢንተርኔትን ለመቆጣጠር ሰዎች በበይነ መረብ የሚመለከቱትን እና የሚያጋሩትን መከታተልም ጀምራለች።

ሌሎች አገራትም ቻይናን ተከተሉ።

ሩሲያ ባለፉት አራት ዓመታት በጣም ርካሽ በሆነ ዋጋ ኢንተርኔትን ከዓለም አቀፍ የበይነ መረብ ትስስር የሚቆርጥ መተግበሪያ እየገነባች ነው።

ከዩክሬን ወረራ በኋላ በኢንተርኔት ነጻነት ሁለት ደረጃ ወደታች ወርዳለች።

አክሰስ ናውለተባለው የመረጃ ተደራሽነት መበት ተቆርቋሪ ተቋም የሚሠሩት ማርዋ ፋታፍታዲጂታል አምባገነንነት እየተስፋፋ ነውይላሉ።

አፍሪካኢንተርኔት ተደራሽ ከሚያደርግባቸው አገሮች መካከል ሳዑዲ አረቢያ ትገኝበታለች።

የመስመር ዝርጋተው ሪያድ የደረሰው ከወራት በፊት ነው። በሳዑዲ የተቃውሞ ድምጾችን ማፈን ወይም መቅጣት የተለመደ ነው። ከመንግሥት ጋር ስምምነት የፈረሙ ተቋሞች በሳዑዲ ግዛት ውስጥ መሥራት እንዳለባቸው የሚወስን ሕግ አለ።

ተመሳሳይ ሕጎች በቱርክ፣ በዮርዳኖስ፣ በሕንድ እና በጀርመንም ተደንግገዋል።

ይህ ማለት የኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት በሕግ ተገደው ወይም ለፖለቲካ ሲሉ በሳንሱር ውስጥ ሊሳተፉ ይችላሉ።

ይህ አስጊ ነው ብዬ አምናለሁየሚሉት ባለሙያዋ፣ ተመሳሳይ የኢንተርኔት ገደቦች በመላው ዓለም እየተባባሱ እንደሚሄዱ ያስጠነቀቅቃሉ።

ቻይናን በመከተል አንዳንድ አገራት የምዕራባውያንን የኢንተርኔት ዝርጋታ ለመገዳደር ይሞክራሉ።

ሩሲያ አገር በቀል መተግበሪያዎች እንዲበለጽጉ የምትደግፈውም ለዚህ ነው።

ያንዴክስየተሠራው ጉግልን ለማስቀረትሲጆን ቪኬእያደረገ ፌስሱክ እየቀነሰ፣ሩቲዩብደግሞ ዩቲዩብን እየተኩ መጥተዋል።

ሕንድም በቻይና የተሠሩ መተግበሪያዎችን እያገደች ነው። በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ውጥረት እየተባባሰ መጥቷል።

አንዳንድ ምዕራባውያን አገራት የኢንተርኔት ነጻነትን ለመጠበቅ ይሞክራሉ። አሜሪካ ደግሞ ቲክቶክን ለማገድ ወስናለች።

እንደቴሙእናሼይንያሉ የቻይና መገበያያ መተግበሪያዎች ዕጣ ፈንታም ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል።

ዓለምን ወደ አንድ እያመጣ የነበረው ኢንተርኔት ከመቼውም በላይ በዓለም መካከል ክፍተት እየፈጠረ ያለበት ጊዜ ላይ ደርሰናል።»

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።