"ዕውቅና ለማግኘት ሲባል ወደ ሲኦል አናመራም" የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር» BBC. የእኔ ዕይታም።

 

"ዕውቅና ለማግኘት ሲባል ወደ ሲኦል አናመራም" የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር» BBC. የእኔ ዕይታ።

https://www.bbc.com/amharic/articles/cge9llldzj2o

(የእኔ ዕይታ። አይደለም ለሱማሌ ላንድ ለራሷ ለሱማሌም ይህ ብቃት አንቱ ነው። የአዲሱን የካቢኔ አቅም የአደረጃጀት ጥራት ሚዛን ክብደት አሳይቶኛል። የፖለቲካል አቅሙ ከገፃቸው ጋር ሳሰተውለው ቅብአም ግርማ ሞገስም አስተውያለሁ። ለቀንዱ ፖለቲካም እንዲህ በሳል አቅም ያለው ሰብእና ውድ ነው። ከምርጫው ሂደት ጀምሮ እኔ በሱማሌ ላንድ የዴሞክራሲ ሰላማዊ ስልጡን ጉዞ ምርኮኛ ሆኛለሁ። አገላለፃቸው ለሚመሩት በአት ያላቸውን ታማኝነት አሳይቶኛል። የፖለቲካ ንጽህና ማለትም ይህ ነው።)

1)                   "ህዝባችን መበልጸግ አለበት። ምጣኔ ኃብታችንን ልናሻሽል ይገባል። በዕውቅና ስም ግፍን አንቀበልም የትኛዋም አገር ብትሆን ይሄን ወስጄ ዕውቅና እሰጥሃለሁ የሚባል ነገር የለም። ዕውቅና የሚሰጠው አምላክ ነው፤ በጊዜው ይመጣል"

2)                   ለዓመታት ፖለቲከኞቿ አገራቸው ዕውቅና እንድታገኝ እየሰሩ ቢሆንም አዲሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለዕውቅና ሲባል "ህዝባችንን የሚጎዳ ነገር አንቀበልም"

3)                   "ለዕውቅና ስንል ሁሉንም ነገር እናደርጋለን ነገር ግን ለዕውቅና ሲባል ወደ ሲኦል አናመራም እንዲሁም ህዝባችንን አናጠፋም። ዕውቅናው የሶማሊላንድን ጥቅም እና የዚያችን አገር [ዕውቅናውን የምትሰጠው አገር] ጥቅም ባጣጠመ መልኩ ሊሆን ይገባዋል" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

4)                   አክለውም "ዕውቅና ሰጥተናችኋል ለማለት ሃገራችንን ለሌላ አገር መሸጥ እንዲሁም ሃብታችን እና ህይወታችን ሌሎች እንዲቆጣጠሩ ማድረግ ትርጉም የሌለው ነው"

«ከኢትዮጵያ ጋር የባህር በር መግባቢያ ስምምነት የተፈራረመችው ራሷን እንደነጻ አገር ያወጀችው የሶማሊላንድ አዲሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር "ዕውቅና ለማግኘት ሲባል ወደ ሲኦል አናመራም" አሉ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አብዲራህማን ዳሂር አደን አገራቸው ዕውቅና ማግኘትን ከፍ ያለ ስፍራ ብትሰጠውም "ህዝባቸውንንም ሆነ አገራቸውን የሚጎዳ መሆን የለበትም" ሲሉ ታህሳስ 27/ 2017 . በፓርላማ ባደረጉት ንግግር አብራርተዋል።

ሚኒስትሩ ባለፈው ዓመት ከኢትዮጵያ ጋር የተፈረመው የባህር በር መግባቢያ ሰነድ ግልጽነት እንደሚጎድለው ተናግረዋል።

የመግባቢያ ስምምነቱን የፈረሙት የቀድሞው የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ እና የኢትዮጵያ መንግሥት "ስምምነቱን አስመልከቶ የሚናገሯቸው ጉዳዮች እርስ በርስ የሚጣረሱ ናቸው" ሲሉ ሚኒስትሩ አብዲራህማን ዳሂር አደን አስረድተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የመግባቢያ ስምምነቱን ይቃወሙት እንደነበር በትናንትናው ዕለት በፓርላማ ባደረጉት ንግግር አብራርተዋል።

"እነሱ [ኢትዮጵያ] የባህር ጠረፍ ስናገኝ ነው ስለ ዕውቅናው የምናስበበት ነው የሚሉት። ለሶማሊላንድ ዕውቅና እንሰጣለን ያሉበት ቦታ የለም" ሲሉ ሚኒስትሩ ከፓርላማው የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ስምምነቱን አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያ ራሷን እንደ ነጻ አገር ካወጀችው እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ካላገኘችው ሶማሊላንድ ጋር 20 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የባህር ጠረፍ ለማግኘት የመግባቢያ ሰነድ መፈራረሟ ይታወሳል። በምላሹም ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ ዕውቅና ለመስጠት እንዲሁም ከልማት ኢንተርፕራይዞች ድርሻ ይኖራታል የሚል ነው።

ኢትዮጵያ በዚህ ስፍራ የባህር ኃይል ሰፈር እንደምታቋቁም እና በምትኩም ለሶማሊላንድ ዕውቅና ትሰጣለች መባሉን ተከትሎ እንደ ግዛቷ አካል የምታያት ሶማሊያ ጉዳዩን ወደ መንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት መውሰዷ ይታወሳል።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር የመግባቢያ ስምምነቱን የፈረመውን የሶማሊላንድ መንግሥት የተካው የአዲሱ አስተዳደር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እርሳቸውም ሆነ ፓርላማው የመግባቢያ ስምምነቱን መፈተሽ ይገባናል ብለዋል።

ሶማሊላንድ ባደረገችው ስድስተኛ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ ተቀናቃኝ የሆኑት የተቃዋሚው ፓርቲ ዋዳኒ መሪ አብዲራህማን ሞሐመድ አብዱላሂ (ኢሮ) ማሸነፋቸው ይታወሳል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ለማግኘት 33 ዓመታት ያህል እየጠየቀች ያለችው ሶማሊላንድ ዕውቅናን ማግኘት ከፍተኛ ስፍራ የምትሰጠው እንደሆነም ነው ሚኒስትሩ በፓርላማው የተናገሩት። ነገር ግን ለዕውቅና ሲባል "አገራቸውን ጉዳት ውስጥ የሚከት ነገር ውስጥ እንደማያስገቡ" በዚህ ወቅት አስረድተዋል።

"ለዕውቅና ስንል ሁሉንም ነገር እናደርጋለን ነገር ግን ለዕውቅና ሲባል ወደ ሲኦል አናመራም እንዲሁም ህዝባችንን አናጠፋም። ዕውቅናው የሶማሊላንድን ጥቅም እና የዚያችን አገር [ዕውቅናውን የምትሰጠው አገር] ጥቅም ባጣጠመ መልኩ ሊሆን ይገባዋል" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

አክለውም "ዕውቅና ሰጥተናችኋል ለማለት ሃገራችንን ለሌላ አገር መሸጥ እንዲሁም ሃብታችን እና ህይወታችን ሌሎች እንዲቆጣጠሩ ማድረግ ትርጉም የሌለው ነው" ሲሉ አክለዋል።

ምንም እንኳን ነጻ አገርነቷን ዕውቅና የሰጠ አገር ባይኖርም እንድ አገር የሚያስፈልገውን ሁሉ የምታሟላው ሶማሊላንድ፣ ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት በአፍሪካ ውስጥ በዴሞክራሲያዊነት ከሚጠቀሱ ምርጫዎች መካከል ያካሄደች እና ከተረጋጉ የአፍሪካ ቀንድ አገር አንዷ ናት።

በዘንድሮው ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲ ማሸነፉ እና የስልጣን ሽግግሩ ሰላማዊ መሆኑን ተከትሎ በሶማሊያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ "የሶማሊላንድ አስደናቂ የምርጫ ታሪክ እንዲሁም ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ለቀጣናው እና ከዚያም ባለፈ አርዓያ ነው" ሲል ማሞካሸቱ ይታወሳል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።