«የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ከሥልጣን እንደሚለቁ አሳወቁ» BBC. የእኔ ዕይታ። የህሊና ብቁ ስልጣኔ ትሩፋት። ኢጎን ያሸነፍ የብቃት ልዕልና። ድንቅነትም። ብልህነት።
«የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ሥልጣናቸውን መልቀቃቸውን ገለጹ።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c4gxn2dkg4lo
በቀጣይ ወራት የሚተካቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ለማወቅ እንደጓጉ ተናግረዋል።
ትሩዶ ማምሻውን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ምክር ቤታቸው "ለወራት መሥራት እንዳልቻለ" ተናግረዋል።
ምክር ቤቱ እስከ መጋቢት 24 ድረስ በሥራ ላይ እንደሚቆይም ገልጸዋል።
የትሩዶ ሊበራል ፓርቲ በ2021 ነበር ለሦስተኛ ጊዜ የተመረጠው።
ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኋላ የተቀዛቀዘውን ምጣኔ ሃብት ለማነቃቃት ፓርቲያቸው ቃል ገብቶ ነበር።
ይሄ አገር "እውነተኛ ምርጫ ይፈልጋል" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
"በውስጣዊ ሽኩቻ" ውስጥ እንደሆኑ ገልጸው ይህም ለካናዳውያን የሚጠቅም እንዳልሆነ ገልጸዋል።
ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመመካከር ሥልጣን ለመልቀቅ መወሰናቸውን አክለዋል።
ከፓርቲው ሊቀ መንበርነታቸውና ከጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው ነው የተነሱት።
ትሩዶ ፓርቲያቸው አዲስ መሪ እስከሚመርጥ ድረስ ሥልጣን ላይ እንደሚቆዩ ገልጸዋል።
እሳቸውን የሚተካው መሪ በሚካሄድበት ምርጫ ላይ "ይቺ አገር እውነተኛ ምርጫ ትፈልጋለች" ብለዋል።
ትሩዶ በሕዝብ ያላቸው ድጋፍ እየቀነሰ የመጣ ሲሆን ፓርቲያቸው በጠቅላላ ምርጫ ሊሸነፍም ይችላል።
የትሩዶ መልቀቅ በካናዳ ፖለቲካ አንድ ምዕራፍ የመገባደድ ያህል ነው።
"ፓርላማው ባለፉት ወራት ሥራውን በአግባቡ ማከናወን አልቻለም። በድጋሚ ወደ ሥራ መመለስ ያስፈልጋል" ብለዋል ትሩዶ።
ትሩዶ ለሦስት ጊዜ ተመርጠው ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል።
"ፓርላማው እንደ አዲስ ሲጀምር አገሪቱ የገጠማት ውስብስብ ችግር በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃም እንዲፈታ ያግዛል" ብለዋል።
ከሥልጣን መልቀቃቸው በአገሪቱ የተከሰተውን "መካረር" የሚያረግብ እንደሆነ እንደሚያምኑ ትሩዶ ተናግረዋል።
ትሩዶ እአአ በ2015 ሳይጠበቁ ፓርቲያቸውን ከሦስተኛ ደረጃ አንስተው አሸናፊ አድርገዋል።
የኑሮ ውድነትና አመራራቸው ላይ የተነሱ ጥያቄዎች በሕዝብ ያላቸውን ተቀባይነት ቀንሰውታል።
የኩዌቤክ፣ ኦንታሪዮና አትላንቲክ ግዛት የሊበራል ፓርቲ እንደራሴዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲወርዱ ሲጠይቁ ነበር።
26% ድምጽ ሰጪዎች ትሩዶን እንደደገፉና ይህም ከወግ አጥባቂው መሪ ፒሬ ፒቬሬ 19 ነጥብ ከፍ እንደሚያደርጋቸው ኢፕሶስ ሰርቬይ የሠራው ጥናት ይጠቁማል።
ትራምፕ ካናዳ በግዛቷ ድንበር የስደተኞች እንቅስቃሴን የማትቆጣጠር ከሆነ የካናዳ ምርቶች ላይ የ25% ቀረጥ ለመጣል መዛታቸውን ተከትሎ ቀጣዩ የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ከባድ ሥራ ይጠብቃቸዋል።
ትሩዶ ሥልጣን ሲይዙ ለስደተኞች ክፍት የሆነ አሠራርና የአየር ንብረት ለውጥን መታገልን ጨምሮ አዲስ የፓለቲካ አካሄድ ለመተግበር ቃል ገብተው ነበር።
አሁንም ቢሆን የአየር ንብረት ለውጥን መታገል መቀጠል አለበት ብለዋል።
"ተስፈኛና ለቀጣይ ዓመታት የተሻለ ዕይታ ያለው መሪ ያስፈልጋል። ያ ሰው ደግሞ ፒሬ ፒቬሬን አይደለም" ብለዋል።
ትሩዶ ሥልጣን መልቀቃቸውን በኦታዋ ከተማ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ሲያስታውቁ ደጋግመው "ታጋይ ነኝ" ብለዋል።
ትሩዶ በቦክስ ፍልሚያ ይታወቃሉ። ከወግ አጥባቂ ፓርቲ ጋር በፖለቲካው መድረክም ተፋልመዋል።
ባለፈው ወር የፋይናንስ ሚኒስትራቸው ክርስቲና ፍሪላንድ፣ የፖሊሲ አለመስማማትን ምክንያት በማድረግ ከሥልጣን መልቀቃቸው ጠቅሰው፣ ሚኒስትሯ በሥልጣን ቢቀጥሉ ደስተኛ እንደሚሆኑ ትሩዶ ተናግረዋል።
ሚኒስትሯ የለቀቁት ዶናልድ ትራምፕ በካናዳ ምርቶች ላይ ሊጥሉ ያሰቡትን ታሪፍ በተመለከተ ከትሩዶ አስተዳደር ምላሽ ጋር ባለመስማማታቸው ነበር።
ካናዳውያን ድመጻቸውን ሰጥተው የሚፈልጉትን ሰው እንዲመርጡ እንደሚሹ ተናግረዋል።
በማኅበረሰቡ መካረር ረግቦ "በአንድ ዓይነት መንገድ ላይ" የፓለቲካ ፓርቲዎች መቀጠል የሚችሉበት ዕድል እንደሚፈጠርም ገልጸዋል።»
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ