ልጥፎች

"#ሁለገብ ትግል" እና ትውልዱ።

ምስል
  " #ሁለገብ ትግል" እና ትውልዱ።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።     የማከብራችሁ የአገሬ ልጆች እንዴት አደራችሁ?   #ምዕራፍ ፲፯   "የሁለገብ ትግል" መሠረተ ሃሳብ ጠንሳሹ ግንቦት 7 ነበር። በዛ ዘመን "ሁለገብ" የሚለው የመነሻ ሃሳብ እርሾ ነበረው። እኔ እንደማስበው ከቅንጅት መራራ ስንብት በኋላ የተፈጠሩት፤ አገር ውስጥ ይታገል የነበረው አንድነት የግንቦት 7 አዲስ የሁለገብ ፍልስፍና መንፈስ የመጋራት አቅምን አጠይቆ ይመስለኛል ግንቦቲዝም ሁለገብ ትግል ዶግማው የነበረው፤ ይመስለኛል። ይመስለኛል እምለው እራሱን ችሎ ጥናት ስላልተደረገበት ነው የአቀረብኩት አመክንዮ።   አገር ውስጥ ግንቦቲዝምን በበዛ ጉጉት ይጠብቁ የነበሩ ተናጠላዊ መንፈሶችም ሊኖሩ እንደሚችሉ አስባለሁኝ። ግንቦቲዝም የቅንጅትን መራራ የስንብት መንፈስ ትንሳኤውን ያወጄ ንቅናቄ ስለነበር። ዲያስፖራ ላይ አንጃ አልተፈጠረም፤ ወጣ ገብም ሁነት አልነበረም። ግንቦት 7 ዲያስፖራውን በአካል የመምራት አቅም ስለነበረው ለሌላ ኃይል ድውለት አልሆነም።    #ግን ሁለገብ ትግል የትኛውን የትግል መሥመር ሊከተል ይችላል?   1) ሰላማዊ ትግልን። 2) የትጥቅ ትግልን። 3) ከዚህ ውጪም ሌላ የትግል መስክ ሊኖር ይችላል በእኔ ዕይታ። #የዝምታ #ዕድምታ ።    በዘመነ ህወሃት መራሹ ኢህአዴግ የሁለገብ ትግል አራማጅ ተብለው፤ "በአሸባሪነት" ተፈርጀው ብዙ በጣም ብዙ #ንጹኃን የጥቃት ሰለባ ሆነዋል። በተለይ በበዛ ሁነት የአማራ ልጆች። ሙየህወሃትን መንበር ከሥሩ የነቀለው ግን ከሁለቱም የትግል ስልቶች ውጪ የነበረ ዝቅ ሲል ጥቃት አሻም ያለ #ቅን መንፈስ፤ ከፍ ሲል #የዊዝደም ሙሉ አቅም...

#አስታዋሽ ያጣ ብሄራዊ ዕንቁ። የተዘለለ የጥበብ አገራዊ #ልቅና።

ምስል
  • #አስታዋሽ ያጣ ብሄራዊ ዕንቁ። የተዘለለ የጥበብ አገራዊ #ልቅና ።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።     https://www.youtube.com/watch?v=TL-9-_wfJW4 «ተጋብዤም ተሸልሜም አላቅም | መጀመሪያ ፊልም ስሰራ 50 ሳንቲም ነው የተከፈለኝ አርቲስት አልማዝ አበበ» #asham_tv | #አሻም_ቲቪ   አንዳንድጊዜ ኢትዮጵያ የጥበብ ባለሙያወች ብቻ #ሰገነት ትመስለኛለች። ክብሩ፤ መወደሱ፤ ድጋፋ አትኩረቱ፤ ሹመቱ ሽልማቱ፤ ዕድል እና እንክህ እንክህ መባሉ በአስተውሎት እከታተለዋለሁኝ። ለካስ ይህ ለሁሉም የጥበብ ሰወች አይደለም። በጥበብ ተሳትፎ ውስጥ የክት እና የዘወትር፤ የእዳሪ እና የቤት ልጅ፤ ዓይነታና እንጥፍጣፊ የሚል እጅግ የሰፋ የሚያስከፋ አድሏዊነት አለ?    የክብር አንባሳደርነቱ፤ የማስታወቂያ ዕድሉ ሁሉ …………-------- #ለተወሰኑት ብቻ??? ፍትኃዊነት ቢያንስ በእጅ ባለ ነገር መተርጎም ምን ያቅታል? አሻግሮ ከመጠየቅ??? በመዳፍ ያለ አቅም ስለምን ያቅታል??? ብዙ በጣም ብዙ የጥበብ ጥሪወችን በእኩልነት ላስተናገደች #ዕንቋችን አትኩሮቱ ስለምን ተሰደደ? ተቋማት ሰው መሆን የመቻል አቅማቸው መለኪያው ለእኔ #ፍትኃዊነት ነው። ጉማ አዋርድ፤ ለዛ አዋርድ ወዘተ የሚባሉ ሥርዓት ሲከውኑ አያለሁኝ። የጥበብ ቤተኞችም ተሞሽረው ይገኛሉ። #ባሊህ #ባይ ያጡ ደግሞ እንዲህም የጥበቡ #ቀንዲሎች አሉ። ቢያንስ ለባዕሉ የታዳሚነት ጥሪ ምኑ አነሰ #የአርቲስት አልማዝ አበበ??   ክብርት አርቲስት አልማዝ አበበ በዩቱብ የተለቀቁ ተውኔት ላይ ተሳትፎዋን አያለሁኝ። ከእሷ የማየው ለየገጸባህሪው #ተፈጥሯዊነት ብቃት በጥቂቶች ብቻ የሚገኝ ጸጋ ይመስለኛል። ብዙ ጊ...

#አብረን #እንፈር። የኢትዮጵያ ሴት የፖለቲካ ሊቃናት የአቤቱ ብልጽግና የካቢኔ #አባላት የት ናችሁ????

ምስል
  #አብረን #እንፈር ። የኢትዮጵያ ሴት የፖለቲካ ሊቃናት የአቤቱ ብልጽግና የካቢኔ #አባላት የት ናችሁ????   ዕውነት ለፈሪነት አልተፈጠረም!   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   የእኔ ክብሮች የአገሬ ልጆች እንዴት አደራችሁልኝ? እንዴት አረፈዳችሁ? ይህን መሰል #የዕንባ ውስጥን #የሚያውክ ዘገባ ባላቀርብ በወደድኩኝ። ግን እፍረቱ የጋራ ነው እና ስቃዩን ልንጋራ ይገባል ብዬ። አውጥቼ አውርጄ ከቢቢሲ ያገኜሁትን ዘገባ ለጥፌዋለሁኝ። እኔ በዘመነ ደርግ ተማሪ ነበርኩኝ። ደርግን የሚፋለሙ ህወሃት እና ኢዲዩ የሚባሉ በጎንደር አካባቢ ሽምቅ ተዋጊወች ነበሩ። በከተማም ነጭ ሽብር እና ቀይ ሽብር የሚባሉ የበቀል ገደላ ገደሎች ነበሩ። በአዋሳኝም ህወሃት ነበር። በኡምናህጀር በሰቲት አካባቢ የሻብያ ሁነት እንደነበረ አላስታውስም።    ግን የመንግሥት ሠራዊት፤ የተፋላሚወች የኢዲዮው እና የኢህአፓ ሠራዊት በዛን ጊዜ ከብልጽግና እና ከህወሃት ጦርነት ወዲህ የምሰማው ዓይነት #ሴቶችን #የጭካኔ አዲስ ማንነት እንዲኖራቸው የሚያስገድድ ዜና ሰምቼ አላውቅም። በዘመነ ደርግ የወጣቶች እስር ነበር። ትምህርት ቤት ላይም ድብደባ ነበር። እስር ቤት #ቶርች ነ ግድያም ነበር። የአደባባይ እርሸናም ነበር።    ከትምህርት ቤት በጅምላ ተወስደን ፋሲል ግንብ በጉልበት የእንብርክክ የመሄድ ቅጣትም ነበር። ካለምግብ እና መጠጥ እዛው ባዶ ክፍል ላይ ማደር፤ ውሃ በመኪና ሲመጣም #የጎርፍ ውሃ መሰጠት ነበር። ተሻምተን የጎርፍ ውሃ ጠጥተናል። የደረቀ ዳቦውንም ኮርሽመናል። እኔም ይህን ቀምሸዋለሁኝ። ከዚህ ውጪ #መደፈር እንዲህ በጀምላ አልሰማሁም። በህወሃት ጊዜም ታስሬ ነበር። በዘመነ ደርግ የወጣት ስደት በስፋት ነ...