ልጥፎች

ክርስትና እና እስልምና ዓይናችሁን አደራ ጠብቁ!

ምስል
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት +  የኢትዮጵያ እስልምና ሃይማኖት  ዓይናቸውን የመጠበቅ አምላካዊ  ግዴታ አለባቸው። ክርስትና ማለት  ሆነ እስልምና መታመን ነው። „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል“ መጽሐፈ ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute ©Selassie 17.12.2081 ከጭምቷ ሲወዘርላንድ ምሩቁ ይስህቅ! ·        ጠብታ ጤና ይስጥልኝ ውዶቼ የማካብራችሁ እና የምናፍቃችሁ የአገሬ ልጆች እንዴት አላችሁልኝ። አውሮፓ ስሜን አሜሪካ ያላችሁ እንዴት ይዟችኋዋል ብርዱ? ዘንድሮ በጋውም እረጅም ነበር፤ ክረምቱም ቀለል ያለ ነው እዚህ እንደ ሲዊዝ ከሆነ። ለነገሩ ገዳማዊቷ አገር ሲዊዘርላንድ በጋውም ሆነ ክረምቱ በልክ ነው፤ እጁን ታጥቦ የፈጠራት ብጽዕት ናት እና። በረድ የሚጥለው ተራራ ላይ ነው።  ሙቀትም በበጋ ምን አልባት ቢበዛ እስከ 5 ቀን ነው ከፍ ያለ የሙቀት ደረጃ የአዬር ንብረት ያለው እንጂ ቀሪው ለጤና ተመጣጥኖ እንደሚሠራ ምቹ ምጥን ነው። የገዳማዊት አገር ነገር እንዲህ ነው እንደ ህዝቧ ሁሉም በደንበር ነው፤ በልክ  …. የታደለች! ·        ዓይን። ብሩካን! ዓይን ፖስተኛ ነው። ዓይንም ብርሃን ነው። ዓይንም የምርምር ተቋም ነው ለአካላት ሁሉ። ዓይን በጥበብ ውስጥ የተቀመረ ተፈጥሮ ነው ያለው። ይህን ስል ግን ልበ ብርሃን የሆኑ ሉላዊ ዜጎችም እንዳሉን ነው እማስበው። የእነሱ አፈጣጠር ደግሞ ከማስተዋል ጋር ብልህነቱምን አርቅቆ ነው የፈጠራቸው። ል...

የኢትዮጵያ ሴቶች ለዕንቋማ ዘመናቸው ጥበቃ ሊያደርጉለት ይገባል።

ምስል
የኢትዮጵያ ሴቶች ለዕንቋማ ዘመናቸው ጥበቃ ሊያደርጉለት ይገባል። „እግዚአብሄር አምላክ በአዳም ከባድ እንቅልፍ ጣለበት አንቀላፋም፣  ከጎኑም አንዲት አጥነትን ወስዶ ሥፍራውን በሥጋ ዘጋው። እግዚአብሄር አምላክም ከአዳም የወሰዳትን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት። ወደ አዳምም አመጣት።“ (ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፪ ከቁጥር ፳፩ እስከ ፳፫። ) ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie  16.12.2018 ከጭምቷ ሲወዘርላንድ። ·        ከጠ ቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ የመንፈስ ፍልቅ በጥቂቱ። „ ወንድ እና ሴት በሚያስደንቅ ሁኔታ የተፈጥሮ ልዩነት አላቸው። ወንዶች በደንብ እንድትሰሙኝ እፈልጋለሁ። ሴቶች በሚያስደንቅ ሁኔታ ከወንዶች የተሻለ ብቃት አላቸው። “ /ከባለቅኔው ጠ/ሚር አብይ አህመድ የተወሰደ/ https://www.youtube.com/watch?v=NHhWHrJOuHU Ethiopia Dr abiy  የሰዉ   ልጆች   ልዩ   ብቃት   ክፍል   ሁለት https://www.youtube.com/watch?v=AHyuaT4mqz4 Ethiopia Dr abiy  የሰዉ   ልጆች   ልዩ   ብቃት   ክፍል   አንድ   „  ወንዶች በሴቶች ላይ የበላይነታቸውን ያረጋገጡ ጊዜ ግማሽ አካላቸውን አይደለም ቆርጠው የጣሉት። ትልቁን ዕወቀታቸውን ቀበሩት፤ ዕወቀታቸውን ቀብረው ሆነ ጨዋታው።“ ከባለቅኔው ጠ/ሚር አብይ አህመድ የተወሰደ/ „ ክርስትና ማለት ትንሳ...