የኢትዮጵያ ሴቶች ለዕንቋማ ዘመናቸው ጥበቃ ሊያደርጉለት ይገባል።

የኢትዮጵያ ሴቶች
ለዕንቋማ ዘመናቸው
ጥበቃ ሊያደርጉለት ይገባል።
„እግዚአብሄር አምላክ በአዳም ከባድ እንቅልፍ ጣለበት አንቀላፋም፣
 ከጎኑም አንዲት አጥነትን ወስዶ ሥፍራውን በሥጋ ዘጋው።
እግዚአብሄር አምላክም ከአዳም የወሰዳትን አጥንት
ሴት አድርጎ ሠራት። ወደ አዳምም አመጣት።“
(ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፪ ከቁጥር ፳፩ እስከ ፳፫።)

ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie
 16.12.2018 ከጭምቷ ሲወዘርላንድ።




·       ከጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ የመንፈስ ፍልቅ በጥቂቱ።

ወንድ እና ሴት በሚያስደንቅ ሁኔታ የተፈጥሮ ልዩነት አላቸው። ወንዶች በደንብ እንድትሰሙኝ እፈልጋለሁ። ሴቶች በሚያስደንቅ ሁኔታ ከወንዶች የተሻለ ብቃት አላቸው። /ከባለቅኔው ጠ/ሚር አብይ አህመድ የተወሰደ/

Ethiopia Dr abiy የሰዉ ልጆች ልዩ ብቃት ክፍል ሁለት
Ethiopia Dr abiy የሰዉ ልጆች ልዩ ብቃት ክፍል አንድ



 „ ወንዶች በሴቶች ላይ የበላይነታቸውን ያረጋገጡ ጊዜ ግማሽ አካላቸውን አይደለም ቆርጠው የጣሉት። ትልቁን ዕወቀታቸውን ቀበሩት፤ ዕወቀታቸውን ቀብረው ሆነ ጨዋታው።“ ከባለቅኔው ጠ/ሚር አብይ አህመድ የተወሰደ/


ክርስትና ማለት ትንሳኤ ነው። እዚህ ክርስትያኖች አላችሁ። ማነው ትንሳኤን ያወጀው? ክርስትና ምንድነው ሚስጢሩ? ክርስትና ማለት ትንሳኤ ነው አይደለምን? የክርስትና የመጨረሻ ultimate ሚስጢር ትንሳኤ ነው! አይደል? ማነው ትንሳኤን ለሐዋርያት ያወጀውመግደላዊት ማርያም አይደለችንም?“  አይገርሙም እኒህ ንባብ ሊሂቅ? /ከባለቅኔው ጠ/ሚር አብይ አህመድ የተወሰደ/




ሙስሊሞችም ልነገራችሁ። ነብይ ጅብሪልን ካነጋገሩ በኋዋላ መጥተው ክድጃን ሲነግሯት ያናገርህ እኮ ጅብሪል ነው ያለችው ናትክድጃ እኮ ናት! የመጀመሪያዋ የእስልምና ተከታይ እኮ ናት ክድጃ! የነብዩን መልዕክተኝነትን ያረጋገጠቸው የመጀመሪያ ሴት ማን ናት? ማን? ብለው እራሳቸውን ይጠይቁና ይመለሰሱታል በድጋሚ አስርግጠው ይምልሱታል። ክዳጃ!“ / ከባለቅኔው ጠ/ሚር አብይ አህመድ የተወሰደ/

...       ወግ ቢጤ ... 

ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንዴት ናችሁ? ዛሬ ነጩ አበባን እዮር ልኳል። አይዋ ነጮ እዬራዊ አባባ የምሥራቹን ይዞ ብቅ ሲል ታዳሚው ደግሞ ጫ ብሎ ያስተናግደዋል። በዚህች ሰዓት እኔ ይህን ስጽፈው ሰው በምድር የሚንቀሳቀስ አይመስልም እኔ በምኖርባት ቅድስት ከተማ። 

እኔ ከምኖርባት ቅድስት ከተማ የሚወለዱም እስከ አሁን የማውቃቸው ሰውኛ ርህርህና ያላቸው ናቸው። ከተማዋም ለሰውኛ ጠረኗ ልዩ ነው። እወዳታላሁኝ። እትብቴ የተቀበረባት ነው እምትመስለኝ ቢንቲዬን። ቀብሬም እዚኸው እንዲሆን ነበር የተናዘዝኩት። ዛሬላችሁ ግን አሻቦ ንግድን ልሰብ አልኵኝ። ይሁን አይደል? ሜዞ ከተገኜ ብዬ .. 

መቼም ኢትዮጵያ አዬር መንገድ እንደ ወትሮ በወዘተረፈ ማዕቀብ ከጣለባቸው ከዘረዘራቸው የሥም ዝርዝሮች ውስጥ አንዷ ሥርጉትሻ ስለምትሆን አሁን ግን ምህረት ስለወረደ አጋጅ የለምና ከረጢቴን ጠርቀምቅም እድርጌ ወደ እዮራዊ ነጮው መጭ ልል አሰኝኝ። አሻቦ አስመጪና ላኪ ልሆንላችሁ፤ ታዲያንላችሁ ግን የጫታው ግርማው እና ግርማታው አሰፈራኝ እና ተግ አልኩኝ … ተግታ ውብ ነው አይደለምን? እነደዚህ ዓይነት ጸጥታ ነፍሴን ይገዟታል። ብዕርም ታንቆረቁረዋለች …

·       ልባሟ እምቤቴ ካዳመጥሽኝ።

ከላይ የለጣጠፍኳቸው መሰረታዊ ሉላዊ የሴቶችን ልቅና በድፍረት የመሰከረ ምልክታ ከእኛ የተፈጠሩት ዶር አብይ አህመድ ከተናገሩት የተወሰደ ነው። በዛሬ ዓመቱ ሙግቴ በአብይ ኬኛ „አብይ ለእኛ ለሴቶችም አናባቢያችን /ቫወላችን/ ነው ስል ክፍል ሦስትን ሠርቼው ነበር በዚኸው ትራስነት።

ያን ጊዜ ብዙም ከቁብ የቆጠረው የለም ምልክታዬን። ዛሬ ግን ያልኩት እዬሆነ እዬታዬ ነው። የለመደባቸው የህውሃት ህዋስ ቤተኞች „ቀልብ ለመሳብ“ ብለው ቢያብጠለጥሉትም ሉላዊው መንፈስ ግን ግርማ ሞገስ አድርጎ አምደኛ አደረገው ጭብጡን። ያ አፍሪካን ሊደርሽፕ መጋዚንም ካወዳደራቸው ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ውስጥ ጠ/ሚር አብይ አህመድ አሸናፊ እንደሆኑ ገለጦልናል። ገናም ይቀጥላል። በዚህ ዙሪያ አልተጋንበትም እንጂ ዓለም እራሷ በሴቶች ዙሪያ ባለው ዓለምን የናኝ የዕውቅና ሙሉ ክብር ሌላም ቢያደርግ አይደንቅም።

ወጣት ለሆኑ ሴት ሊሂቅ ደግሞ ይህ ንዑድ መንፈስ ያለውን ወ/ሮ ጽዮን ተክሉን ናሙና አድርጌ በዚህ ግልጬ ነበር። ወይ ጊዜ እንዴት ይሮጣል ዓመት ሆነው እኮ!

ናሙናዬ ልዕልቴ ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ እንዲህ ዓይነት ሴት ናቸው።

„አለቆች ነን ለምንድነው ሰራተኞቻችነን ፉሊ ማድረግ ያቃተን፤ ያልቻልነው። እነዚህን ነገሮች አንድንጠይቅ፤ ራሳችን ስንጠይቅ ስንመለከት ምን ይታዬናል? „ድመት ሆነን አንበሳ ነው የሚታዬን? ወይንስ አንበሳ ሆነን ድመት ይታዬናልወይንስ ሰው ሆነን ሰው ይታዬናልስለሳይንስ ስናወራ፤ ሳይንቲስት ለመሆን ሰው ብቻ  መሆን በቂ ነው። ማሰብ፣ ሃሳብን ማደራጀት፤ በምክንያት ማስቀመጥ፤ ከዛ በኋዋላ ደግሞ ማስተላለፍ።“

ይህን ቦታ መድረክ ደፍሮ መስጠትን ከውስጡ ሆኜ መርምሬ ነበር የዛሬ ዓመት ሴቶችን ውስጡ ያደረገ ሊሂቅ ሊከበር፤ ሊመሰገን፤ ልማጎትለትም ስለሚገባ ነበር ፊት ለፊት ወጥቼ የሞገትኩት። ምንም እንኳን ወጀቡ በግራ ቀኝ ያን ጊዜ ቢያዋክበኝም። ለዚህም የሳተናው ብራና ይለፉን ሰጥቶኝ / ኢትዮ ሪጅስተር/ እሱም ለሴቶች ቅን ስለሆነ ለጥፎለኝ መተንፈሻ ቧንቧዬ ስለሆነልኝ የኢትዮጵያ ቅኖች ከልባችሁ ያላችሁ አንስት እህቶቼ ልትጸልዩለት ይገባል። አይገኝም እንዲህ ለሴቶች አቅም ይለፍ የሚሰጥ።

በዛ ጹሑፍ ውስጥ እንዲህ ብዬ ነበር … ጠ/ሚር አብይ አህመድ ለመራሂት ወ/ሮ ጽዮን ተክሎ „ከእርምጃ ወደ ሩጫ ሞቶ" ላይ ስላሳተፏቸው ነው እንዲህ ብዬ የጸፍኩት … ዛሬን እማ ብጹዕ አባታችን ሊቀ ጳጳስ አቡነ የሖንስ እንዳሉት „ከትርጉም በላይ ነው“

„በወንዶች ዓለም ሴቶች ያላቸውን ዕምቅ ሃብት አናይ ዘንድ ዕውቅና ሰጥቶ ለዚህ ስላበቃን፤ የሰማዮዋ ጠሐይ መሬት ላይ ወርዳ ሃብታችን እንደትሆን፤ የእኛ እንድንላት፤ እኛም አለንበት፤ ቤተኛ ነን እንል ዘንድ ለዚህ ስላበቃን የሰማይ ታምር ነው፤ ክብሩ ይስፋ አማኑኤል አባቴ። አሜን!“

·       ን ሲሰጥ አይነግር።

ቀንቶን፤ ወፊቷ አውጥታን፤ አንገታችን ቀና አድርጎ፤ የለበስነው ትቢያ አራግፎ እንሆ ዛሬ ሴቶች ዕውቅ በሆነው የፖለተካ መዋቀር በክብር የተጋባቸውን ቦታ አግኝተዋል። ለቃሉ ያደረ፤ ስለቃሉ የሚኖር መሪ አላዛሯ ኢትዮጵያ ሰጣት። ቃል ኪዳኑ መጋቢት 24 ቀን 2010 ተሠረ። እንዳለን ሆነልን። ተመስገን።

በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ፤ በተገኘው ዕድል ሁሉ አቅም ያላትን ሴት ወደ ፊት ለማምጣት ምልጃ፤ የማንፌስቶ ማህበርተኝነት፤ የክት እና ዘወትር ልጅነት፤ የክት እና የዘወትር ዜግነት፤ ብረት መዝጊያ የሆነ ዘመድ እንሆ ሳያስፈልግ ተማላዋንም የሚፈለግ መርህ ንድፉ ብቻ የሆነ ሥርዓት ለመፍጠር ቁርጠኛው የኢትዮጵያ ሴቶች የመብት ተሟጋች ጠ/ሚር አብይ አህመድ ያሰበለ ተግባር እዬፈጸሙ ይገኛሉ።

ዛሬ ለኢትዮጵያ ሴቶች የብርሃን ቀናችን ነው። ለኢትዮጵያ ሴቶች የተሰፋችን መባቻ ሳይሆን ከተስፋችን ጋር ተገናኝተናል። የኢትዮጵያ ሴቶች ዛሬ ሁነኛ ዋቢ ሙሴ አለን። እናትን ማከበር፤ የትዳር አጋርን ማፍቀር፤ ሴት ልጅን መውደድ ማለት በዚህ ይገለጣል። ይህ ራስን ያሸነፈ የተግባር እርምጃ በዬትኛውም ዘመን፤ በዬትኛውም ሁኔታ አይደለም ዓለም እኛም ያላሰበነው የእዮር ስጦታ ነው ከሰማይ ዱብ ያለልን ድንግል ገጸ በረከት።

የፈለገ ዓይነት ሥርዓት ይዘርጋ የፈለገ ዓይነት የመንግሥት መዋቅር ይታለም ግን እንዲህ ሥር ነቀል የሆነ በሴቶች አቅም ዕውቅና ላይ  የማህበራዊ ለውጥ እንብርት ኢትዮጵያ ታገኛለች ተብሎ አይታሰበም ነበር። ህልም ነው የሚመስለው የሆነው ሁሉ።

እኛ እራሳችን ለእኛ የፖለቲካ ዕውቅና፤ ለእኩልነታችን ነጻነት ሳይሆን የምንታገለው ለወንዶች ዓለም የፖለቲካ ልቅና፤ ሥልጣን፤ ዝና እና ውደሳ ነበር ስንተጋ የኖርነው። ደስታችን … እልልታችን ለተባዕት ባለሥልጣናት ዕውቅና ብቻ ነበር። ይህ ዘመን ግን ስለራሳችን እናሰብ ዘንድ ፊደል እያስቆጠረን ነው። ዘመኑ የፊደል ገበታችን ነው። የ ኢትዮጵያ ሴተች ስለራሳችን እራሰችን ረስተን ችል ብለን የኖርን ነን።

አብሶ አንስት ሆነው በሴቶች አቅም እና ችሎታ በር እንዲዘጋ ያበሩ እና የተባበሩ፤ ለለመስከር አንደበታቸው ለተዘጋው አንስት ሁሉ ዘመን ትምህርት ቤት ከፍቶላቸዋል፤ እራሳቸውን ወቅስው ከዘመኑ ምህረት ጋር እንዲወዳጁ።  

አርጀንቲናዊቷ ኢቫ /ኢቢታ / ህይዋን/ ፔሩ አርጀንቲናን በሥርዓት ለውጥ ሳይሆን በህሊና ማህበራዊ ለውጥ ነው የካነችው። ውቧ ኢቫ ፔሩ የተሳከለት ድንቅ አርቲስት፤ ተናፋቂ የፖለቲካ ሰው፤ እጽብ እንቁ የድሆች እናት፤ ታማራዊት የሰብዕዊ መብት ተሟጋች እና የራዲዮ ጋዜጠኛ ነበረች። 

አሁን አርመን በሴቶች ዙሪያ ጠንከር ያለ ሥርዓት የዘረጋች አገር ናት፤ ትጋቷም መዋቅራዊ ነው። የድንቋ የኢቪታ ግን የሥርዓት ለውጥ ብቻ ሳይሆን በሴቶች አመለካከት ላይ ደንቃራ በነበሩ የአስተሳሰብ ለውጦች ላይ ማህበራዊ ንቃተ ህሊና አብዮት ነበር ያካሄደቸው። ጠ/ሚር አብይ አህመድም የተከተሉት ይህን ነው። የናፈቀኝን አግኝቻለሁኝ እኔ።

ይህ እርምጃቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ ነው ሁሉም እራሱን ፈትሾ የጎደለውን እንዲያ ያደረገው። ለሺህ ዘመናት ሴቶች ተሰውተዋል፤ ለሺህ ዘመናት ሴቶች ግብር ሲያቀርቡ ኖረዋል ግን የእነሱ ክህሎት፤ አቅም፤ የማድረግ ችሎታ ግን ለወንዶች ዓለም እልልታ አጃቢነት ነበር። ዘብርሃነ ኢትዮጵያ እቴጌ ጣይቱ ግዞት የታወጀባቸውም አቅማቸው ስለተፈረ ነበር በራስ ተሰማ ናደው ሴራ እንዲያ ያ ሁሉ የብልህነት ጥበብ ተሰምሶ የተቀበረው።

ዛሬ ግን ዘመን ተቀዬረ። በሴቶች ዘርፍ የተገኘው ለውጥ ሥር -ነቀል ነው። ከዚህ በላይ የምንጠብቀው ምንም ነገር ሊኖር አይገባም። ሥርዓቱን እራሱ የሚያመጣው ይኸው አቅም ይሆናል።

የሚገረመው ማህበራዊ ንቃተ ህሊናውን እንዴት የሰመረ እንደሆነ ነው። ቃለ ምልልሶችን የልቤ አድርጌ ስከታታላቸው ሴቶች ሃሳባቸውን ለመግለጽ ያላቸው አቅም ከመቃብር የወጣ ያህል ይሰማኛል። ደፋሮች ሆነዋል። ተባዕቶችም በሴቶች ላይ ያላቸው አሜኔታ ጉልበታም ሆኗል። ጠ/ሚር አብይ ለ ኢትዮጵያ ሴቶች የሰጡት ታላቁ ስጦታ መታመንን አብርከተውልናል። አመኑን ከልባቸው። ይህ የሰው ሥራ ነው ብዬ ማመን እኔ ይሳነኛል። እንደ ቅድስት ኦርቶዶክስ አማኝነቴ የመንፈስ ቅዱስ ድንግል ምርቃት ያለበት ነው ሆኖ ያገኘሁት።

ምክንያቱም የሴት ሊቃናት ተቀባይነት ጉልህ ነው። ሴቶችን ለመሪነት ማሰብ እራሱ ውግዘ ከአርዮስ የሚያሰኝ ነበር። መጻፍ ራሱ። እኔ አንድ ጊዜ ዓለምን በሙሉ ሴቶች ቢመሯት ዓለም ምን ትምስል ነበር?ሴቶች የሚመሯት ዓለም ናፈቀኝ የሚል ጹሑፍ ጽፌ ወዲያው ነው የተነሳው። 

ፈሪው አይዋ ግራ በእሱ ላይ ያነጣጠርኩ ስለመሰለው ራድ ያዘው እንዲህ ዱብ ዕዳ ከሰማይ አውርዶ ንፈሱ ፍላጎቱን ሆነ ህልሙን ጨርቄን ማቄን ሳይል ሊሸኝልኝ። ተመስገን!

አሁን ተወደደም ተጠላም ብቻ ሳይሆን የማንፌሰቶ ማህበርተኞች ተባዕት የፖለቲካ ሰው የሴት መሪ ያስፈልገናል እስከ ማለት ደርሰዋል። ይህን ማህበራዊ ንቃተ ህሊና እኔ በአነሰ ግምት 50 ዓመት ከእንግዲህ ይወስድብናል ብዬ አስበው ነበር። እኔ ካለፍኩ በኋዋላ ሌሎች ያዩታል ነበር ህልሜ። 

እንዲያውም የሴቶችን አቅም በማውጣት፤ በመግለጽ፤ በማጉላት እረገድ እራሷ ሴቷም ስለማትራራልኝ፤ ስለምትታገለኝ ብዙውን ዘመን በዝምታ ነው ያሳልፍኩት። ሙሉ አቅሜን ሥራ ላይ አላውልኩትም በሴታዊት ተጋድሎ። በዚህ ዙሪያ ብዙ ከመስራት በራሴ ላይ ማዕቀብ ጥዬ ነፃነቱ ይምጣ እንጂ በወንዶች አለም ቢሰክን ይሁን በማለት ነው እሰራ የነበር። አንዷ ቪክተምም እኔው ስለሆንኩኝ። መፈናፈኛ አልነበረም። እዚህ ውጭ አገር እራሱ ... 

ብቻ ተመስገን ይቅደም እና… ሁሉንም እርሙን እንዲያወጣ ያደረገው ዘመን ሁሉንም አሳዬን። የድልም አለው ዓይነት፤ የውጤትም አለው ዓይነት፤ የስኬትም አለው ዓይነት፤  የስጦታም አለው ዓይነት። ይህ የዘመን ለውጥ ለኢትዮጵያ ሴቶች ሆነ ለአህጉራችን ለአፍሪካም ልዩ ጌጣማ ነው። ዛሬ የለውጡ መድረኩ መላጣ አይደለም፤ ዓውዱ ድርቀት በወናነት የሚዳንስበት አይደለም። ውብ ነው አልባብ ባልባብ ነው። አብቧል። ሴቶች ጥበቦች ናቸው። እነሱ የተገኙበት ዓውድ ሁሉ የፈካ ነው። ድምጻቸው ቃናው እራሱ የተመቼ ነው።


ይህ የስኬት እርምጃም ኬኒያ ለመከተል እዬከጀለች ነውና ለአህጉራችንም አዲስ ምዕራፍ ያቀዳጀ ታላቅ የብስራት ዓዋጅ ነው። ለዚህም ነው "አብይ የአፍሪካ ሴቶች አንባሰደር" ብዬ ገና ጉባኤው መክፈቻ ላይ ጽፌ የነበረው፤ በአፍሪካው  የመሪዎች 11ኛ ጉባኤ ላይ። የውሳኔውም አቅጣጫ እኔ ባሰብኩት ልክ ነበር። ጠ/ሚር አብይ ውስጤ ካሉት የውስጥ ነው። የላይ የታይታ የከንቱ ውዳሴ አይደለም። ባለቤት ለሆኑለት ነገር ሁሉ ግንባር ቀድም ወታደሩ ናቸው።

ዛሬ የኢትዮጵያ ፓርላማ ካቢኔ 50% በሴት ሊሂቃን የተገናባ ነው። ተመስገን!ለዚህ ነው የዛሬ ዓመት ሥርጉትሻ አብይ  ለእኛ ለሴቶችም አነባቢያችን ነው ብላ የጻፈችው። 

እኔ ጠ/ሚር ቢሆኑ ይህን ሊያደርጉ እንደሚችሉ ቅንጣት አልጠራጠረም ነበር። እኛ ነፃነታችን የሚታወጀው አብይ ጠ/ሚር ከሆነ ብቻ ነው ብዬ ለእንድ የብዕር ጓደኛዬ ሁሉ ጽፌያለሁኝ። ለዚያውም ያን ጊዜ እሳቸው የኦሮምያ የጽ/ቤት ሃላፊ ነው የነበሩት። ውሹም አልነበረም የጠ/ሚርነት ቦታው። 

እያንዳንዱን የኢትዮጵያ ችግር የእኔ ላለ ሙሴ ዕድሉን ካገኜ የሚገደው የለም እና። ሴቶች በሚመለከት የሚዋዋሱትን፤ የሚመላላሱትን ባህላዊ ተደሞ ሳይቀር በልጅነት ጊዜ የነበረው ክንውን ሳይቀር ከጎረቤቶቻቸው፤ ከሰፈር ካሉ እናቶች ጭምር ነው የሚነሱት። ይህ የመነሻ ነጥብ በሴቶች ዙሪያ ምን ያህል ጥልቅ የጥናት እና የምርምር ተግባር እንዳደረጉ አመላካች ነው።




እኛ ሴቶች ሉላዊንም ያክላል ለጠ/ሚር አብይ አህመድ መንፈስ ደባል አይደለንም። ቤተኛ ነን። እኛ ለጠ/ሚር አብይ አህመድ ህሊና በቀጠሮ የተያዝን አይደለንም፤ ዘወትራዊ ዘላቂያዊ አብይ አንኳር አጅንዳ ነን። እኛ በጠ/ሚር አብይ አህመድ ልቦና ውስጥ ባይታዋር አይደለንም የደማቸው መሠረት ነን።

ስለዚህ የኢትዮጵያ ሴቶች ለነፍሳችን፤ ለሩሃችን፤ ለኑሯችን፤ ለተስፋችን፤ ለራያችን፤ ለሐሴታችን፤ ስለመኖራችን ሙሴ ስለገኘን ለዚህ መንፈስ ብርቱ ጥንቃቄ፤ ለዚህ መንፈስ ብርቱ ጥበቃ፤ ለዚህ መንፈስ ትጋት ያለው ጸሎት፤ ለዚህ መንፈስ ራስን እስከ መስጠት የሚያደርስ ተጋድሎ ማድረግ ይጠበቀብናል።

ለውጡ የእኛ ነው። ለውጡ ስለ እኛ እውቅና ድል ላይ ያሰቀመጠን ነው። ለውጡ ስለ ሴቶች የእኩልነት ተጋድሎ ድልን ያበሰረ ነው። ለእኛ በኽራችን የሆነም ነው። ድላችን ነው የሆነው ለውጡ ለእኛ ለሴቶች። ምስጋና እና ክብር ለኦሮሞ ፕሮቴስት እና  ለአማራ የማንነት የህልውና ተጋድሎ። ካሱን!

ጣማራ ተጋድሎዎቹ አብሶ ለኢትዮጵያ ሴቶች ዕንቁን ያሳፈሰ፤ የመንፈስ ትርፍን በክብር ያጎናጸፍ ለሁለገብ ብቃታችን ሙሉ ዕውቅናው ብልዕልና ያዘከረ የተጨባጭ ውጤት ላይ የተገኜ ባለውለታችን ናቸው። የስኬት ባለቤት ያደረገን እኛኑ ነው። እኛ ምን ስለመሆናችን፤ እኛ ማን ስለመሆናችን፤ እኛን ውስጣችን ያሳዬ ራዲዮሎጂያችን ነው ይህ ለውጥ።

በተፈጠርንባት መሬት በባይታወርነት ለቁጥር ብቻ የምንፈለግ፤ አቅማችን አላግባብ ሲቀዳድ የነበረበትን ዘመን እንሆ ሸኝቶ እኩልነታችን በላተለመደ ሁኔታ መንበር ላይ ያዋለ ሽልማታችን ነው ለውጡ።

በፈለገው የአብዮት ዓይነት ይህ ዕድል አይገኝም ነበር። የተገኘው የሴቶች መብት ተሟገች የሆነ መንፈስ ሙሴ መሆን በመቻሉ ብቻ ነው። ይህን ደግሞ ሰብዕና ለመገናበት ነው ተብሎ ዘራፍ እንደማይባል ተስፋ በመድረግ። ተረገጡ ይኸው ነው። ሌላ ተፎካካሪ/ ተቀናቃኝ/ ተቃዋሚ ድርጅት እድሉን ቢያገኘው ፈጽሞ  ከአጀንዳ የማይቆጥረው ነበር ነገረ ሴቶች።

እያለን መሰረዛችን ብቻ ሳይሆን ህልፈታችን እና ክስመታችን በደቦ ዘመቻ ስንመነጠር ነው የኖርነው፤ ለዛውም በነፃነት አገር። ነፃነታችን ተቀምተን ከዜግነትዝርዝር ተወግደን፤ አነገታችን ደፍተን ለመቀመጥ እንኳን ያልተፈቀደልን ምንዱባን ነበርን።

በወንዶች የፖለቲካ ዓለም የሚፈራው አምክንዮ ልክ እንደ አማራው አቅም የሴት የፖለቲካ ሊሂቃን መንፈስ፤ የሴት፤ ጸሐፍት ብዕር እና ብራና፤ የሴት የፖለቲካ ዲቤት ነው። እነኝህ መሰረታዊ ጉዳዮች የተባዕቱን  የፖለቲካ ሊሂቃን ዓለም የሚርዱ የሚያስጨንቁ ነበሩ። በዚህ ውስጥ የሴቶችን የብቃት ዕውቅና ለማሰብ ፈጽሞ አይቻልም ነበር። ስለሴቶች የማድረግ አቅም የውሽማ ሞት ያህል የተሰወረ፤ አደራሻ ያልነበረው ነበር። 

የሴቶች ክህሎት በላዩ ላይ የተዘጋበት የተከረቸመበት አጀንዳ ነበር። ይህ ገማና ተሸክሞ ለነፃነት፤ ለዴሞክራሲ፤ ለአዲስ ሥርዓት ግንባታ ተጋድሎ ሲባል እኔ ከዚህ ከገዳማዊ ቤቴ ሆኝ እታዘባለሁኝ። በዬትኛው በተሰጠን ነፃነት? በዬትኛው ባዬነው በጨብጥነው፤ በዳሰሰንው የዴሞክራሲ ልክ ነገን እንሰብ? እንደምንስ ነገን ተስፋ እንድርግ? አልነበረም እኮ ነፃነት በሉት ዴሞክራሲ እዚህ ውጪ አገር። 

ትግሉ ለማንፌሰቶ ማህበርተኛ ጥቂት በዞግም፤ በጋብቻም፤ በምንትሶም በቅብርጦስም እትብተኛ ሴቶች ከሆነ እንደዛ ይነገረን እንጂ ለኢትዮጵያ ሴቶች በሙሉ የሚለው ተርብ ግን ተረት ነው የነበረው። ይህን ያልፈታ ይህን ባሊህ ያላለ፤ ይሀንን ያልደፈረ የፖለቲካ ሊቀ ሊሂቅ "መሪነት" የሚለውን ቃል ለመስጠት እዬተዋለ ሲታደር፤ አቅሙ ሲፈተሽ፤ ሲመነዘር ወቄቱ ተዛነፍ ይሆናል። ነገረ አግድሞሽ።

እኔ ስለ አላዛሯ ኢትዮጵያ ነፃነት ብተጋም በሴቶች በኩል ያለው ጭቆና እንዲህ ሥር - ነቀል መፍትሄ ያገኛል ብያ አይደለም፤ አልነበረምም። ምከንያቱም የሁሉም ተፎካካሪ/ ተቃዋሚ/ ተቃናቃኝ ፓርቲዎች ሊቀመናብርት ተብዕቶች ናቸው። የሚጣመሩት፤ የሚዋህዱት፤ የሚቀናጁት፤ የሚደራደሩት፤  የሚሿሿሙት፤ ዲቤት የሚያደርጉት እነሱው ናቸው። የብዕር ወቃሳ የማያስተናግድ አውራ ፓርቲ ለማግስት ሁነኛ ነው ብሎ የህሊና ፊርማ ለማስቀመጥ ጋዳ ነው የነበረው። 

ስለዚህ ሴቶች ብርሃን በአጭር ዘመን ያያሉ የሚል የተስፋ ጭላንጭል አልነበረኝም ከዛሬ ዓመት በፊት ... ተስፋ ማድረግ የጀመርኩት ዶር አብይ አህመድ በፖለቲካ ተሳትፏቸውን ወደ ኦህዴድ መዛወራቸውን ሳይ ብቻ ነበር። ቀድሜ መንፈሳቸውን በሌላ የህሊና አጠባ ፕሮግራም አውቀው ስለነበር ልክ እንደ ፈላስፋው ዶር ምህረት ደበበ። 

አሁን ተፎከካሪ የሆኑ 8ቶሽ አንድ ሆን ብለውናል። ይልቅ ዘመኑ ስለፈቀደ አንዲት ሴት ጠብታ ስላለች በመንተፍረቱ እሷን እንደሚያመጡ ልብ ልክ ነው ወደፊት … ማጣፊያው ስለሚያጣራቸው። ብቻ ለወንዶች ዓለም ፖለቲካኞች / ለወንዶች የሥልጣን ፍላጎት ማህበርተኞች ይህ ዘመን ያስገመገመ ንደት ነው የለቀቀባቸው በሁሉም ዘርፍ ነው። ሳያስቡት፤ ሳያልሙት ዱብ እዳ ወረደባቸው። ተሰማዬ ሰማያት። ሁሉ ነገር ለነገ ነበር የሚቀጥሩት ... 

የተዚህ በፊቶች የ81 የፖለቲካ ድርጅቶች መሪዎች ወንዶች ናቸው። በቃ። የተቃነጁትም ይሁኑ በተናጠል የሚታገሉትም መሪያቸው ወንድ ነው። "የሽግግር መንግሥት" እያሉ ቢያሰሉም፤ ያ ሳይሳካ ሲቀር ደግሞ "የተጽዕኖ ፈጣሪ መንግሥት" ቢባል ያው እነሱ ነው ሽግግርም፤ የተጽዕኖፈ ፈጣሪ አንድነት መንግሥትም የሚሆኑት ዙሮ ተመልሶ እነሱው ናቸው። ዘመን ከዘመን የወንዶች የዘውድ ዘመን የማይነቃነቅ ከዛው ለዛው የቸከለ።

 በፍጹም የማያፍሩበት ነገር 40 ዓመት ሙሉ ራሳቸውን ለመተካት አለመቻል ብቻ ሳይሆን፤ ሴት ሊሂቅ ወደ ፊት ለማምጣት አለመድፈራቸው ነው። ወጣቶችንም ይፈሯቸዋል። ወጣት ሆና ሴት ከሆነችማ እንደ ጉድ ነው የሚያርዳቸው። 

አሁን ብሄራዊ የፖለቲካ ሊሂቃን የጋራ ስብሰባ፤ ንግግር ሲባል ገበርዲን እና ከረባት ብቻ። በውነቱ ያሳፍራል ያን ያህል ድርቅ የመታው ራዕይ። ውክልና የሌላውን ከዬት ይመጣል።

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሊቃናት ተብዕቶች ደፋሮች አይደሉም። ፈሪዎች ናቸው - በጣም። አሁን አንዳንድ የቴሌቮዥን ፕሮግራሞችን አያለሁኝ። ፖስተሩ የወንድ ብቻ ነው። በቃ ኢትዮጵያ ሴት የነፃነት ተጋድሎ አደረገች በዚህ 40 ዓመት ውስጥ የላትም ... ማፈሪያ!

የሴት አክቲቢስት የለም፤ የሴት ሞጋች የለችም፤ የሴት ጋዜጠኛ የለችም፤ የሴት ጸሐፊ የለችም፤ የሴት የፖለቲካ ሊሂቅ የለችም። አለች ግን በህሊና የተሰረዘች ናት። በመንግሥት ሚዲያ ነው ይህን የማዬው።

ይህን ሴቶች እራሱ ባሊህ ሊሉት አይፈቅዱም። እንዴት በጎደሎ እንደምንታይ። አይጋበቸውም። "እንደ ንጉሥ ዳዊት የቤትህ ቅናት በላኝ አይሉም።" አያቃጥላቸውም አያንገበግባቸውም። የሚገርም እኮ ነው። ለዚህ ነበር እኔ ለዓለሙ ማህበረሰብ አቤቱታ በተለያዬ ጉዳይ ስጽፍ መብቴ ጨለማ ውስጥ ሆኖ ነው የምጽፍላችሁ እል የነበረው። አንዲት ሴት ማዬት አልቻልነም ተፎካካሪ/ ተቀናቃኝ/ ተቃዋሚ በሚባለው ውስጥ። 

የግራ ፖለቲካ መንፈስ አራማጆች ሴቶች ወደፊት ከመጡ ጉዳቸው እንደሚፈላ ያውቁታል። ሴቶች መንፈሳቸው የተደራጀ ነውዝርክርኮች አይደሉምሴቶች ባላቸው አቅም እንጂ በሞገድ ትራስነት አይኮፈሱም። ለዚህ ነው በዬተገኝበት ቦታ እምንታገተው።

ዛሬ ደፋር ጀግና ሊሂቅ ገጠማቸው ነው አርፈው ቁጭ አሉ። ይህን ግዑዝ፤ የማይፈጥር፤ የማይተክል፤ የማያሰብል መንፈስ ተሸከመው እንዴት እንደሚያሸንፉ ይታያሉ በመጪው ምርጫ። ት የሌለባት ኢትዮጵያን በድርቅ ትመታልኝ ብሎ የሚፈርም ዕብን ካለ ይታያል። 

ለነገሩ አሁን በገርዳሜም በገርማሜም መወታታፉ አይቀሬ ይሆናል። እስቲ ዋናዋን ሊቀመንበሯን ቦታ ይሰጣት እና እንፈታተሽ በተፎካካሪዎች ዘንዳ። እነሱ ከሴት ሥር ሆነው ሊመሩ? „ካለ አበደ በቀር ዱባ ቅል አይጥልም“ ይላሉ ጎንደሮች እንዲህ መሰል ተዛነፍ ገመና ሲገጥማቸው …

እግዚአብሄር ከሰማዬ ሰማያት ወርዶ የሰራውን ታምር ግን ሊጋፉት አይቻላቸውም። እንሆ አሁን ምርጫ ለሚሉት ነገር ሴት ሊሂቅ ነው የምትሰበስባቸው። ለዛውም እንደ ጦር የሚፈሯት በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ በስውርም በግልጥም ሲያሳድዷት የኖረቸው ሴት ክብርት ወ/ት ዳኛ ብርቱካን ሚዲቅሳ።

ስለሆነም ማንኛውም ኢትዮጵያዊት ሴት የማንፌስቶ ማህበርተኛ ያልሆነችው ማለቴ ነው ባለ ማንፌሰቶዋ እሷ የፈለገችውን ትሁንብት፤ ሌላዋ ተማላዋ በዝምታ ውስጥ ያለችው እባዛኛዋ፤ አንገቷን ደፍታ የተቀመጠችው፤ ቀብረናታል የተበላቸው እንደ ሥርጉትሻ ያለች አንስት ግን ትናንት ያልነበረ፤ ወደፊትም በህልም ሊታሰብ የማይችል ዕንቁ ዕድል ፈጣሪ ሰጥቷል እና ከጠበቃዋ ከጠ/ሚር አብይ ጎን በመቆም በማናቸውም ዘርፍ ትጋቷን መቀጠል አለባት። የሴቶች የመንፈስ ምርጫ አብይ እና ሌጋሲው ሊሆን ይገባል። መብቷን አሳልፋ መስጠት የለባትም። አቅሟንም የትሜና ማባከን እንደ ድሮው አይኖርባትም።

የአብይ መንፈስ ለሴቶች አነባቢ ብቻም ሳይሆን ተናባቢ መጸሐፋችን፤ ተመራማሪ ድርሳነ ሳይንቲሳችንም ነው። የአብይ መንፈስ ለእኛ ለኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቀናችን ነው። የአብይ መንፈስ ለእኛ ለሴቶች ሙሴያችን ነው።
የአብይ መንፈስ ለእኛ ለኢትዮጵያ ሴቶች መሪያችን ብቻ ሳይሆን የበኽር ልጃችን፤ ታናሽ እና ታላቅ ወንድማችን፤ የመንፈስ ርህርህናችን፤ የሩሃችን ዋስ ጠበቃችን፤ የልቅና ውስጣችን፤ የማይነጥፍ ቅናችን፤ የሚዘልቅ ቀናችን፤ የቅኔ ዘመናችን ነው።

ስለሆነም በማናቸውም ዘርፍ በተገኘው የሥራ ሃላፊነት ሁሉ የአብይን ሌጋሲ ለማስፈጽም መትጋት ግዴታችን ነው። ኑሯችን ነው። ህይወታችን ነው። ስለ መኖሩ መጸለይ ግዴታችን ነው። በቅንነት ለመንፈሱ ጥበቃ ማድረግ ወላዊ ግዴታችን ነው። ራሱን ተፃሮ እንደ ቆመው የወለጋ ህዝብ ሳንሆን የራሳችን እራሳችን ስለመሆኑ ከውስጣችን ልንቀበለው ይገባል።

                        በጠ/ሚር አብይ የድጋፍ ሰልፍ ባህርዳር፤


አብይ ለእኛ ለኢትዮጵያ ሴቶች የደም ጋናችን ነው። „ልብ ያለው ሸብ“ ይላሉ ጎንደሮች። ሁላችንም ለአብይ ሌጋሲ ዘብ አደር መሆን ይጠበቅብናል - ቅን ሴቶች በሙሉ። ስለ እናቱ፤ ስለ እህቱ፤ ስለ ሴት ልጁ፤ ስለ ትዳር አጋሩ ግድ የሚለው ተባእትም ክብረቱን መጋራት ይኖርበታል። ይህ መንፈስ ዘመንን ያናገረ ጨለማን የገፈፈ ባለ ብሩሕ ማርዳዊ ዘመን ነው። በፍላጎታችን ውስጥ የሰከነ ጣዝማችን ነው። በራዕያችን ውስጥ የዘለቀ ንጥር ወርቃችን ነው።

ጠ/ሚር አብይ አህመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋዋላ በዬክልሉ በተካሄደው ስብሰባ እራሱ የሴቶች ተሳትፎ ዕጹብ ድንቅ ነበር። በራስ የመታማመን አቅሙ ብጡል ነበር። ይህን እኔ በተደሞ ታድሜበታለሁኝ። ገናስ ምኑ ታይቶ? አደብ የገዙ አቅሞች ቀስ እያሉ ወደ መድረክ ይመጣሉ። የአብይ መንፈስ ሠራዊቱ እልፍ ነው። ሴቶችም የእልፎቹ ቅኖች ፈቃደኛ ቤተኞች ነን። ራሳችን ተጻረን አንቆምና። ቅነቾዩ የጨለማ ዘመን አይናፍቀንም፤ ሞገድንም አናምልክም።

የኢትዮጵያ ሴቶች ከንፋስ መና ሳይሆን መዳፋችን ላይ ባለው ነታዊ ህይወት ተጠቃሚነታችን ስላዬን በዚህው ውስጥ እራስን ሆኖ መገኘትን ለይደር አንቀጥረውም።  ለዚህ ያበቃን አምላክ ይመስገን።

በዚህ ውስጥ የኢትዮጵያ ሴቶች ልናስተውለው የሚገባ ጉዳይ ከራሱ በላይ ለእኛ ለሴቶች አስቦ ራሱን ወደ ምክትል ሊመንበርነት አውርዶ፤ ክብር አያሻኝም፤ የአገሬ ትንሳኤ የሴቶች የእኩልነት ዘመን እሻላሁ ያለውን ድንቅ የምዕት ቅኔን ዶር ለማ መገርሳን የልብ አድርስ ማለት፤ መጸለዬም ያስፈልጋል። ሌሎቹ አያደርጉትም ነበር። ራሳቸውን እንደ ተከሉ ኖረው 40 ዓመት አስቆጥረው ሲለያዩም ራሳቸውን ሸመው ነው የሚገኙት።

በሌላ በኩል የአማራ እና የኦሮሞ የተጋድሎ መንፈሶችን አድምጠው ለድል ያበቁት የለውጡ አስገኞች ባለትልቅ ጆሮዎች፤ አቶ ደመቀ መኮነን፤ ዶር ገዱ አንዳርጋቸው፤ ዶር አንባቸው መኮነን፤ አሁን ከሆነ ደግሞ የጀርባ አጥንቷ ክብርት ወ/ሮ ሙፍርያት ካሚሌን ፈጠሪ እንዲጠበቅልን በጸሎት መርዳት ያስፈልጋል።

ይህ ሳያዩ ያላፉት ቆሞስ ተስፋዬ ጌታቸውንም አባታችን አማኑኤል ነፍሳቸውን በጽረ አርያም ያኑርልን። አሜን!ፊት ለፊት ያለውጡ ግን ለለውጡ ቀጣይነት ሌት እና ቀን እንቅልፍ አልባ ለሚተጉ ንጹሃንንም ፈጣሪ ይጠብቅልን፤ አሜን!

እኔ ፍርሃት አለብኝ። የደቦ ግድያ ዘመቻው፤ የደቦ የፍርሻ ትንኮሳው፤ የደቦ ሴራው ትብብትብነት በጠ/ሚሩ የተቃጡትን የግድያ ሙከራዎች ሁሉ ሳይሳኩ ሲቀሩ ሽፍት ሊያደርጉ ይችላሉም እላለሁ።

ስለዚህ ከእግዚአብሄር በታች አማንያን በትጋት መጸለይ መጸለይ አለብን - ሳንደክም። አቅማችን ሃይላችን ፈጣሪያችን ነውና።

አብይ ኬኛ!
አብይ የሁላችንም ነው!
አብይ ማግሥታችን በቅጡ ያሰላ ስንዱ አደራጃችን ነው!
አብይ ለሴቶች መብት ግንባር ቀደም ተሟገች፤ ዋቢ፤ ዋስ ጠባቃችን ነው!
ዓራት ዓይናማው መንገዳችን የአብይ ሌጋሲ ብቻ ነው!
የነገ ሰው ይበለን አምላካችን። አሜን!



                                       የኔዎቹ ኑሩልኝ።


 


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።