ልጥፎች

#ግን #አንዱ #ሆስፒታል #ለምን #በክቡር፦ #ሰማዕቱ #ዶር. #አንዱአለም #ዳኜ #አይሰየምም????

ምስል
  #ግን #አንዱ #ሆስፒታል #ለምን #በክቡር ፦ #ሰማዕቱ #ዶር . #አንዱአለም #ዳኜ #አይሰየምም ???? ቅዱስ መንፈስ የረበበት ብሩክ። አንድ መምሪያ ብቻ ሳይሆን አንድ ህልው ሆኖ እዬሠራ ያለ ሆስፒታል ነው በሥሙ መሰዬም ያለበት። ዘገባውን ከማቅረቤ ጋር ግን የግል ዕይታዬነን …   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"      ከእሱ በላይ #ክብር ፤ ከእሱ በላይ #ሞገስ ፦ ከእሱ በላይ #ማዕረገ - ህይወት ምን አለና! #ቁርጠኛ #ውሳኔ #ይጠይቃል ሃሳቤ። ለምን ከውስጤ ገባ ብዬ ሳስብ ምላሹ ተፈጥሮው ውስጤን አሸንፎ ተደላድሎ የመቀመጥ አቅሙ #አንቱ በመሆኑ ነው። ዜናውን ስሰማ ድንጋጤዬ ከባድ ነበር። በቀጥታ ነውከውስጤ የገባው። መረጃውን ሳልሰማ ማለት ነው። መረጃውን ሳገኝ በዚህ ልክ #ትህትና ፤ በዚህ ልክ #ቅንነት ፤ በዚህ ልክ #ውስጥነት ፤ በዚህ ልክ #አገልጋይነት ፤ በዚህ ልክ ለሌሎች መኖር #ድንቅ ሰብዕና ሊመጣ ወይንም ሊገኝ ነው???    አንዱ ሆስፒታል በሥሙ ይሰዬም እና ትንሽ የወል ሃዘናችን የመጽናኛ አቅም ያግኝ። ሌላ ማሰብ እኮ አልተቻለም። ረቂቅ የሆነ የማናውቀው #ስበት አለው ፀጋውም ሁነቱም። የስብሰባው ጭብጥ ፈጣን እና የአንጀት በመሆኑ መልካም ጅምር ነው። ፡ልትመሰገኑም ይገባል።    በሥሙ ወርክሾፖች፤ ሰሚናሮች፤ ፓናል ዲስከሽኖች በቀጣይነት ቢኖሩም መልካም ይመስለኛል። ዝክረ ታሪኩ በፎቶ፤ በመጸሐፍ፤ በመጋዚን በበራሪ ጹሁፍ በተከታታይ ሊሰራበት ይገባል። የዘመን ሥጦታ ፒላር ነውና። የትውልድ ድርሻውን እራሱን ሸልሞ ሰማዕትነት የተቀበለ ጀግና ነውና። ፋውንዴሽን ለማቋቋም ማሰብ፤ የሙያ አጋሮቹ ውጭ የሚኖሩ አጀንዳቸው ሆኑ ትጋቱ እና ሰማዕትነቱን ለዓለም የሙያ አ...

በግራ ቀኝ ተረብ ላይ ያላችሁ ቀልዱን እባካችሁ አቁሙ። ዝምታ #ዕውነቱን አለማወቅ አይደለም።

ምስል
  በግራ ቀኝ ተረብ ላይ ያላችሁ ቀልዱን እባካችሁ አቁሙ። ዝምታ #ዕውነቱን አለማወቅ አይደለም።    "የቤትህ ቅናት በላኝ።"                       ©እፍታ።   አቁሙ ስል ትዕዛዝ አይደለም። የአማራ ፖለቲካ የአማራ #እናት ማህጸን እና የአማራ #አባት አብራክ ቀራንዮ ላይ ማቱን፤ ምጣቱን እያስተናገደ ያለበት ስለሆነ ነው ውስጤን ፍንትው አድርጌ እማጋራችሁ። ለአደባባይ እንደ ቄጤማ የማይነሰነስ ትጋትም ስላለኝ ደፍሬ መናገር እችላለሁኝ። ነዶ አይደለም እዬታጨደ ያለው የአማራ ትውልድ ነው።    ሩብ ብልጽግና፤ ግማሽ ብልጽግና፤ ሩብ ብአዴን፤ ግማሽ ብአዴን፤ ሩብ ኦህዴድ፤ ግማሽ ኦህዴድ፤ ሩብ ደህዴን፤ ግማሽ ደህዴን፦ ሩብ ህወሃት፤ ግማሽ ህወሃት መንፈሱ ያላችሁ ሁላችሁም እራሳችሁን - መርምሩ። አደብ ግዙ። የሞገትንላቸው አሁን ላይ የት ላይ እንደሆኑ መደባቸውን እያዬን ነው። ጊዜ ራዲዮሎጂ ነውና።   በአማራ ፖለቲካ እጁን ያልነከረ፤ #አብሲት የማያበስል የለም። ግማሹ ለኑሮው፤ ከፊሉ ለዝና፤ ጥቂቱ #በሰባዕዊነት ሊሆን ይችላል። የትግሉ ዝንቅንቅነት አቅም ያላቸውን ጓዳ እያስቀመጠ፦ የአማራ ፖለቲካ የሁሉም የኢቤንት ሜዳ ሆኗል። ሁለት ዓመት ሊሞላው ነው። ጠርዝ ለጠርዝ የሚሄዱ ትጉኃን በዝምታ የባሰውን ብቻ እዬነካኩ የሚገኙት እኔን ጨምሮ።    የኦህዴድ " #ሰብረናቸዋል ፤ በትነናቸዋልም" ምንጩ ይኼው ነው። ዕውነቱ #አልተሰበርንም ፤ #አልተበተንም ። ጉዳዩ ሙሉ ቀን፤ ሙሉ ሌሊት ዲስኩር እና ፎቶ ቢያሰለች ብቻ ሳይሆን፤ "አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል" ሆኖ ነገር አለሙ ለማን? ለምንስ? አቅ...