#የኤርትራ የፖለቲካ ሊቃናት መሻት የኢትዮጵያ ፖለቲካ #ማስተር ማይንድ መሆን ነው። የጹሁፌ መነሻ የBBC ዘገባ ነው። አያዠዋለሁም።
#የኤርትራ የፖለቲካ ሊቃናት መሻት የኢትዮጵያ ፖለቲካ #ማስተር ማይንድ መሆን ነው። ዘገባው የBBC ነው። እንዳይቆራረጥ ተያያዥ ጉዳዮችን በዬሰዓቱ የወጡ መረጃውን ያካተተ ዘገባ ስለሆነ ይመለከተናል። ስለዚህ ሙሉውን አያይዤዋለሁኝ። • የአሜሪካ መንግስት እስራኤል ለሱማሌ ላንድ የሰጠችውን እውቅና ካጸደቀ አሁን ያለው የዓለም ፖለቲካ መጨናነቅ ረብ ይላል። ይህ ደግሞ አይቀሬ ነው። አንድ ዴሞክራሲን ዕውን ያደረገ ራስ ገዝ አስተዳደር፤ ወሳኝ ለጂኦ ፖለቲክሱ ወሳኝ ሚና ያለው ቦታ የምኞቱ ስኬት ቅርብ ነው። ቢቢሲ ዛሬን አህዱ ያለበትን ተጨማሪ ማብራሪያ አክያለሁኝ። የሰሞናቱ መስማማት ግርም ብሎኛል። https://www.bbc.com/amharic/live/cy8jldx8vp3t "የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና መስጠቷን ተከትሎ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ" https://www.bbc.com/amharic/articles/c623py0j3xpo "የሶማሊላንድ የዕውቅና ጉዞ እና የእስራኤል ውሳኔ ቀጠናዊ አንድምታዎች #ቆራጣ ዕይታዬን አክላለሁኝ። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። ለሱማሌላንድ እስራኤል ከሰጠችው የዕውቅና ደፋር መግለጫ ባላነሰ ኢትዮጵያ ሰፊውን የዴፕሎማሲ ተግባር ሰርታላቸዋለች። ምርጫቸውን ዓለም በትጋት የተከታተለላቸው በኢትዮጵያ ምክንያት ነበር ብዬ አምናለሁኝ። ለአሁኑ የእስራኤል ውሳኔ አደፋፋሪው የኢትዮጵያ እና የሱማሌ ላንድ ለጋ ያልጠና ስምምነት ነበር ብዬ አስባለሁኝ። የኢጋድ አቋም አልገባኝም። ባይቸኩል፤ ገለልተኛ ሆኖ ቢቆይ ጥሩ ነበር ብዬ አስባለሁኝ። በሌላ በኩል እስራኤል ለወሰደችው ደፋር ጥንቅቅ ያለ...