#ሰንበትን #ለመጠያዬቅ። #ኦባንግሻ የት ነው ያለኽው?

 

#ሰንበትን #ለመጠያዬቅ#ኦባንግሻ የት ነው ያለኽው? 
 
ባለህበት እግዚአብሄር ይጠብቅህ። አሜን።
 
"አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 Obang Metho - Obang Metho added a new photo.
 
ሌሎች የሰብአዊ መብት ሞጋቾቼ ቀጣይ ተሰጣቸው ዕድል ለአንተ #ተነፈገ ወይንስ #ፈቅደህው ይሆን??? እነሱስ ስለምን ዝም አሉ። ብቻ የሰላም ያድርገው። አሜን።
 
 
አንተ ብርቱ የሰላም ወዳጅ፤ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ፤ የኢትዮጵያዊነት #ዘብ #አደር አቶ ኦባንግ ሜቶ የት ነው ያለኽው? 
 
#በህይወት አለህን? ጤንነትህ #ደህና ነው ወይ? ትዳርህ ተሳካን? ግን እንዴት አለህልኝ የምር ወዳጄ ኦባንግሻ??? አማኑኤል አባቴ ይጠብቅህ። አሜን።
 
የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችህን ኤክሱን እና ፌቡ አልፎ አልፎ መልዕክት ከፃፍክ ብዬ እጎበኛቸዋለሁኝ። ትንሽም #ፍንጭ የሚሰጥ ነገር አላገኜሁም። 
 
በቃ! ኦባንግሻ የአንተ ታሪክ በዚህ መልኩ ቄሱም፤ መጸሐፋም #በዝምታ ይቋጭን??? ለነገሩ ኮነሬል ጎሹ ወልዴስ የት ናቸው። ስለ ክቡርነታቸውም ሰምቼ አላውቅም። ኢትዮጵያ እንደገቡ ደማቅ፤ ክብራቸውን የመጠነ አቀባበል በቤተ መንግሥት መደረጉን አይቼ ነበር። ከዛ በኋላ ግን??? ወፍ ዜና ነጋሪ የለም።
 
ወይ አጋጣሚ እነ ማህበረ - ሌንጮ ስኮዬር፤ ዶር ዲማ ነገዕወ በፓርላማ በሚንጎባለሉበት ዘመን፤ እነ አቶ ዳውድ ኢብሳ ያሻቸውን ባሻቸው ሰዓት በሚናገሩበት ዘመን፤ እነ አቶ ስብኃት ነጋ በክብር ወደ አሜሪካ ተልከው የኢትዮጵያን ፖለቲካ እንደ አሻቸው ሲያምሱት፤ ሲያተራምሱት እያዬንም ነው። 
 
ከሳቸው ምን ብጣቂ #ርህራሄ ይገኛል ተብሎ የክብካቤ ሞዝቦልድ እንደ ተሰናዳ ባይገባኝም። የጭካኔ፤ የአረማዊነት፤ የክህደት ልምድ እንገብይ ተብሎ የትውልዱ መንፈስ ያውኩታል። ለኢትዮጵያዊነት ወና እና የፈለሰ፤ ለዛውም የሻገተ ሃሳብ ፍለጋም ሲተጋላቸው እናያለን። የሆነ ሆኖ መንፈሰ ህወሃት ብክል ነው። ለትውልድም ለአገርም አይሆንም።
 
ስለሆነም የአቶ ስብኃት ነጋ ልሳኖች #ዝምታችን ቢከበር ጥሩ ነው። ለህውሃት ቢጠቅሙት ኑሮ ከወደቀበት ረግረግ ባወጡት ነበር ሥልጣን ላይ እያለ አይዋ ህወሃት። የትግራይ ህዝብማ ሁለት ያጣ ጎመን ነው የሆነው። ሃይማኖተኛውን ህዝብ እግዚአብሄር ይርዳው አሜን። ግን ፖለቲካ ቢቀር፤ ጥንቅር ቢል ኢትዮጵያ በተፈጥሮዋ ብትተዳደር እንዴት ከፍትህ በላይ #የርትህ መንገድ በተከፈተላት???
 
የሆነ ሆኖ የማይናፈቁት እንዲናፈቁ እንዳይረሱም ሃሳባቸውንም በአሻቸው ጊዜ በሚገልጹበት ዘመን አንተን ኦባንግሻን የበላ ጅብ አለመጮኹ #ያስጨንቃል። የተሰጠህ ዕድል ይህ ከሆነ፤ የላይኛው መፍትሄ እስከሚያቀብል ድረስ በትዕግሥት #መጠበቅ#መጠበቅ#መጠበቅ። ነግሬህም ነበር በነሃሴ ወር 2010 ዓ.ም። እናትህ ናፍቃህ፤ ጓጉተህ ተጓዝክ። የሆነው ሆነ። 
 
"አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
ውዶቹ ክብሮቹ እንዴት ናችሁ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
21/12/2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።