"የዘር ሐረጋቸው ከኢትዮጵያዊ ስለሚመዘዘው #ሙዲ፤
ከአቶ ኪሩቤል ፔጅ ያገኜሁት ነው። እሳቸው ደግሞ ከአቶ አረፍዓይኔ ያገኙት ነው። ኢትዮጵያ ለሚከብር #ጊዜ መስጠት፦ #አትኩሮትን በበቂ መለገስ ያስፈልጋል። በእጅጉ ያስፈልጋል። ፎቶውም ከእነሱ የወሰድኩት ነው።

በ1298 ዓ/ም የዛሬ 727 ዓመታት ላይ፤ የባሕር ላይ ጉዞውን የጀመረው ማርኮ ፖሎ በጻፈው ታሪክ ስለኢትዮጵያውያን ሲገልጽ እንዲህ ይላል፤
‹‹…ልታውቁት የሚገባ ነገር አለ፡፡ በሐበሻ ምድር ምርጥ የሆኑ ወታደሮች አሉ፡፡ አብዛኞችም ወታደሮችም ፈረሰኞች ናቸው፡፡ ፈረስም በብዛት አላቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ተዋጊዎችና ኃይለኞች ናቸው፡፡ በሕንድ አገር ስላሉትና ከምናደንቃቸው ዕውቅ የሕንድ ወታደሮችም የሚበልጡ ናቸው፡፡….›› ብሏል፡፡
በዓለም ላይ የኢትዮጵያ ወታደሮች እጅግ ተፈላጊና ዝነኞች ነበሩ፡፡ በዚህም የተነሳ በተለይ የምዕራብ ሕንድ ክፍል የሆኑት #ጉጂራትና ማሃራሽትራ ገናና እና ሀብታም ግዛት ስለነበሩ፤ ይህንን ገናናነታቸውን ለማስቀጠል ሲሉ ጠንካራ ሠራዊት መገንባት ፈለጉ፡፡ በዚህም የተነሳ ከ1460 አስከ 1474 ዓ/ም ድረስ ባለው ጊዜ ለአቢሲኒያ ወታደሮች ታላቅ አድናቆት የነበረው ሡልጣን ሩቀዲን ባራቅ የአቢሲኒያን ወታደር ፈለገ፡፡ በወቅቱም የዓረብ ነጋዴዎች የጦር ሠራዊት፤ ከቻይና፣ ከኔፓል፣ ከኤንዶኒዥያ፣ ከማሊዥያ እና ከዛሬዎቹ ዓረብ ሀገራት ያቀርቡ ስለነበረ፤ ከአቢሲኒያ 8‚000 ወታደሮችን ለሡልጣን ሩቀዲን ባራቅ አቀረቡለት ሲል የራሺያ ዩንቨርስቲ ጆርናል ኦፍ ባንግላዴሽ የምርምር ወረቀት አረጋግጧል፡፡
በመቀጠልም፤ ይህ ጥናት አቢሲኒያዊያን ወታደሮች ከሁሉም ጦረኞች በታማኝነትና በጥንካሪያቸው በጣም ይለያሉ ሲል አረጋግጧል፡፡
አያይዞም የአቢሲኒያ ወታደሮች ከሌሎች በተለየ ውድ ነበሩ ሲል ጽፏል፡፡ ከታማኝነታቸውም የተነሳ ደረጃቸው ከፍ ያለ ሲሆን፤ በሡልጣኑ ዘንድ በፖለቲካው፣ በቢዝነሱ፣ በቤት ውስጥ ጉዳዮች ሁሉ አማካሪ ነበሩ፡፡
ከዚህም አልፈው ከሡልጣኔቱ ጋር ከነበራቸው ቀረቤታ የተነሳ፤ ቤተ መንግሥቱን የሚጠብቁ እነሱ ነበሩ፡፡ ቀሪዎች ደግሞ የጦሩን ክፍል የአዛዥነት ሥልጣን ያዙ፡፡ በጊዜ ሂደት ከወታደሩ አስተዳደርም አልፈው፤ ስምንቱ ሺህ ሁሉ በተለያየ የሥራ መስክ ተመድበው፤ በፍርድ ቤት በዳኝነትም ሆነ በንግዱ፣ በግብር ስብስባው፣ ሕግ በማስከበሩ፣ የንግድ ሥርዓቶችን በማስከበር ሥራ ሁሉ ተሠማሩ፡፡
ቀስ በቀስ በሲቪልና በወታደራዊ አስተዳደር የማይታጡ ሆኑ፡፡ እንዲህ እንዲህ እያለ በቤንጋል ሚናቸው የማይተካ ሚና እየሆነ መጣ፡፡ ሲል የራሺያ ዩንቨርስቲ ጥናት ያረጋግጥልናል፡፡
ይህ የማይተካ ሚናቸው ጣሪያ ላይ ደርሶ በ1480 ዓ/ም፤ ሚናቸውን ለመቀነስ የቤንጋል ባለሥልጣኖች ተሰብስበው እየመከሩ በነበሩበት ወቅት፤ ከታች እስከ ላይ አቢሲኒያዊያን ስለነበሩ፤ ሚሥጢሩ ወጣና ከስብሠባው እያሉ፤ አቢሲኒያዊያን ፈጣን እርምጃ ወስደው፤ ሡልጣኔት ጃላሉዲን ፋታንን ገደሉት፡፡
ጀርመናዊው ሄነሪ ብሉማን ጆርናል ኦፍ ኤዥያቲክ ሶሳይቲ ኦፍ ቤንጋል በተሰኘው ጥናቱ ሡልጣኔት ጃላሉዲን ፋታን ገድለው ሐበሾች ከሥልጣን ጠባቂነት አልፈው፤ ሻዳክ ባራክ የተባለውን ያሰዲን ባራክ ብለው የቤጋል ሡልጣኔት አድርገው አነገሡት ሲል ጽፏል፡፡
በተከታታይም 4 ነገሥታት ሐበሾች መንገሳቸውን አረጋግጧል፡፡
8‚000 አቢሲኒያዊያን ወታደሮች ከኢትዮጵያ ወደ ሕንድ ቤንጋል ስለመሄዳቸው፣ በወቅቱ አብረዋቸው በሚኖሩት በፐርሺያ ጻሕፍት ተጽፎላቸዋል፡፡ በተለይ የኒዘመዲን አህመድ የተባለው ‹‹ተበቃቲ አክባሪ›› ዘግቦታል፡፡
ዛሬ ላይ እነዚህ ኢትዮጵያዊያን ወልደው ተዋልደው ቤንጋል የተባለው የጥንት ግዛት ለ2 ተከፍሎ፤ ምዕራብ ቤንጋል ሕንድ ውስጥ ሲገኝ፤ ምሥራቅ ቤንጋል ደግሞ በባንግላዴሽ ውስጥ ይገኛል፡፡ እናም የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሪንድራ ሙዲ ከኢትዮጵያ በጦር ሠራዊትነት ተመልምለው ከዛሬ 500 ዓመት በፊት ከሄዱት "ከጉጅራት" ማህበረሰብ የተገኙ ናቸው።
ዛሬ ላይ ሕንድና ባንግላዴሽ የምናያቸው ፀይሞች ከዚህ የሄዱ ናቸው። በምን አግባብ ሄዱ??? በዘመኑ ከነበረው ንጉስ ጋር ተስማምተው ወይስ በባሪያ መልክ ተሽጠው? ብለህ ለጠየቅኽኝ ልጅ አካሄዳቸው በግላቸው ከነጋዴዎች ጋር ተስማምተው በቅጥር ነው የሄዱ። ንጉሥ ደግሞ ዛሬ ላይ ቪዛ እንደምንለው ከእሱ ሀገር ፈቅዶላቸው ስለመሄዳቸው ማኅተም ያለው ወረቀት ይሰጣቸዋል።
ይህንን የሚመስል አንድ ታሪክ ልጨምርልህ፦ ጣሊያን ለሊቢያ ወታደር አስፈልጓት ስለነበረ ከኢትዮጵያ ወታደር ትቀጥር ነበር። ለእነዚህ ፍቃደኛ የቅጥር ወታደሮች ተፈቅዶላቸው ስለመውጣታቸው ማኅተም ያለው ወረቀት ተሰጥቷቸዋል። በኋላ ላይ የሞቱት ሞተው የተረፉት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ልጅ ኢያሱ የከተማ ጠባቂ አድርገው ቀጥረዋቸው ስማቸውም "ጥሩቡሌ" ይባሉ ነበር፤ ከ ከሊቢያ ከተማ ትሪቦሊ መምጣታቸውን ምክንያት በማድረግ። እናም በባርነት ሳይሆን በቅጥር ነው ወደ ሕንድ የሄዱ።"
Abere Arefe Ayinie Adamu
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ