#አባት እና የኢትዮጵያ #ፖለቲካ። ጋዜጠኛ፤ ጸሐፊ፤ የታሪክ ሙሁር፥ #ደፋር ተናጋሪ፤ ሞጋች፤ የአማራን መንፈሳዊ ጸጋ አክባሪ ናቸው አቶ ታዲዮስ ታንቱ
#ምዕራፍ ፲፯
ጋዜጠኛ፤ ጸሐፊ፤ የታሪክ ሙሁር፥ #ደፋር ተናጋሪ፤ ሞጋች፤ የአማራን መንፈሳዊ ጸጋ አክባሪ ናቸው አቶ ታዲዮስ ታንቱ። ህይወታቸው ከካቴና ጋር የተዋደደ ነው። ምክንያቱም ንግግራቸውን፤ ዕምነታቸውን፤ ዕውቀታቸውን ለማስተላለፍ የግል ኤዲትንግን የማይሹ ግልጽ እና #ቀጥተኛ የሆነ ሰብዕና አላቸው።
እርግጥ ነው ቃለ - ምልልስ ሲደረግላቸው ጥንቃቄ የሚጠይቁ፤ #ጊዜ የማይፈቅድላቸው የአገላለጽ ልበለው የታሪክ ምስክርነትን አጉልተው እንዲያቀርቡ ሲፈለግ የሳቸው መዋለ ዕድሜ #ካቴና እንዲሆን ገጠመኙን አመቻቸ። #ዕውነት ተስማሚ ጊዜ ይጠይቃል። #ፍትህም ወቅት ነው የሚወስንለት ብዬ አስባለሁኝ። በእኔ ፍልስፍና ውበት እራሱን አካባቢ ይወስነዋል ብዬ አስባለሁኝ። ለሁሉም የመኖር ዘይቤወች ሬድሜድ ሊጠበቅ አይገባም ባይም ነኝ።
ድንጋጌሜ እንደ #ተርጓሚው ነው። እኛ የፍትኃብሄር ይሁን የወንጀለኛ መቅጫ ህግ እና ሥርዓቱን ይሁን የአፈፃጸም ሂደቱን ከባለሙያወች በላይ #ጊዜ ሰፊውን የኃላፊነት ድርሻ ይወስዳል። በዘመኑ ባለው ሥርዓት ውስጥ ነው የሂደቱ ክንዋኔወች የሚወሰነው።
ሰሞኑን በዩክሬን እና በራሺያ ጦርነት ኢኮኖሚው የደቀቀው #ዘለንስኪዝምን ለማትረፍ አውሮፓ ማዕከል ላይ ራሺያ አምና፤ ተማምና ያስቀመጠችው ገንዘብ ለዩክሬን ይሰጥ የሚል ጠንካራ አቋም አዳምጫለሁኝ።
በዚህ ሃሳብ ይሁን ውይይት ውስጥ የየአገሮች ህገ - መንግሥት፤ ዓለም ዓቀፋ የፋይናስ ሥርዓቱ እና አፈፃጸሙን፤ #ዴሞክራሲ እና ተስፋውን፤ ዕውነት እና ሚዛናዊነት፤ ፋክት እና ትውልዱን ያሳየን ጊዜ ራዲዮሎጂ ነበር።
በመጨረሻ የአውሮፓ ቁንጮ ፖለቲከኞች ተግባራዊ ማድረግ ለጊዜው ባይችሉም፤ ለውሳኔም ለድርጊትም ሃሳቡ አቅም #ቢያጣም ቅሉ ግን ጉልበታም ዝንባሌውን ሳስብ በዕውነት የነገ የፍትህ ሥርዓት እና ግሎባላይዜሽን #አስፈርቶኛል። እራሱ ሃሳቡ መነሳቱ፤ የፈጀው የውይይት ጊዜ፤ ለዚህ ሃሳብ መንሸራሸር የፈሰሰው መዋዕለ መንፈስ #ያስደነግጣል። በአደራ የተቀመጠን ገንዘብ ጥቅም ላይ ለማዋል ኃላፊው ማን ነው?
ይህን ይዘን ዕውነትን፤ ፋክትን፤ ፍትህን በኢትዮጵያ ፖለቲካ ለማስፈን #ጊዜ ነው ሊዳኜው የሚችል የሚል ግብረ መልስ እናገኛለን። የኡትዮጵያም ፖለቲካም ይሁን፤ የሚዲያ አጠቃቀም ዘይቤ #ዝርግነት #ሰውን #የማትረፍ፤ #ከአደጋ #የመጠበቅ ታስቦ የማይታወቅ ጉዳይ ነው።
#ነፃነትን የሚወስነው ጊዜ ነው። ወይ ሙሉ፤ ወይ ሲሶ፤ ወይ እርቦ፤ ወይንም እኩሌታ ድርሻ ሰጪ ለአጤ ነፃነት ጊዜ ነው ባለዘውዱ። ትናንት ዕውነት የነበረው ዛሬ የሚያስከስስ፤ የሚያስቀጣ ወንጀል ሊሆን ይችላል። የዛሬ ዕውነት ደግሞ የነገ ወንጀል ሊሆን ይችላል።
ስለዚህ ፖለቲከኛውም፤ ጋዜጠኛውም፤ ሚዲያ ላይ ያለውም #ሰው #ማትረፍ ላይ ሊሠሩ ይገባቸዋል ብየ አስባለሁኝ። የጋዜጠኛ አባት ታዲዮስ ታንቱ እንግልትት ማለት ምንጩም ሲጠይቋቸው አይጠነቀቁላቸውም ነበር። ውስጤ ጭንቅ ይለውም ነበር። የሆነ ሆኖ የአንጀት በሽተኛ መሆናቸውን ሲናገሩ ሰምቻለሁኝ። የአንጀት በሽታ እስር ቤት ማስተናገድ የገዘፈ የህይወት ፈተና ነው።
አንድ ዕውነት፤ አንድ ፋክት፤ አንድ ታሪክ በተፈጥሮው ልክ ፍትህ ለማግኜት #ዳኛው ጊዜ ነው።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
21;12/2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ