#ትውልድ እና የኢትዮጵያ #ፖለቲካ።

 

#ትውልድ እና የኢትዮጵያ #ፖለቲካ
 
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
 
 
መስኪ ጠንካራ ጸሐፊ፤ ብርቱ ሞጋች፤ #በዕውቀት ላይ የተመሠረተ የፖለቲካ ተንታኝ ናት። ከ2013 እኢአ ጀምሮ ነው በብዕሯ የማውቃት። ትጉህ ናት። ትጋቷ #ተከታታይ ነው። ደራሽ ታጋይ አይደለችም። ባለቤቷ አቶ ፍጹም የፖለቲካ ሰው አይደሉም። የመኖር ነፃነቷን አላሰሩትም። ስለዚህ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉልህ ተሳትፎ ታደርግ የነበረች ባለትዳር፤ የሁለት ፍቅር የሆኑ ልጆች #ክብርት እናት ጸሐፊ እና መምህርት ስትሆን፤ የምታቀርባቸው ሃሳቦች #ጉልበታም ናቸው።
 
በጣም እንደ ታላቅ እህት #ስለምሳሳላት #ዩኒሴፍ የመሰለ የበጎ አድራጎት ድርጅት #ልጆች #ተኮር በፈለገችው ፎርማት በኢትዮጵያዊነት ወይንም በአማራነት ትጀምር ዘንድ የመነሻ ሃሳብ ጽፌ ነበር። ጓደኛየ ስላልሆነች ትየው፤ አትየው፤ ይድረሳት አይድረሳት አስተያዬቴ አላውቅም። ለጓደኞቿ ግን ይነግሯት ዘንድ በትህትና ነግሬያቸው ነበር። የሆነ ሆኖ ያን መንገድ ብትመርጥ #ተመራጭ#ፍጹም የተሻለም ይሆን ነበር። ለስኬቱም ጥርጥር አልነበረኝም።
 
#መምህርነት እኮ ሁለገብነት ነው። ሁሉን የሰጠው ሙያ ነው መምህርነት። አባቴ አቨይ፤ ታላቅ እህቴም መምህር ሆነው የዕውቀታቸውን ዲካ አውቀዋለሁኝ። የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አደራጅም ስለነበርኩኝ መምምህራን ልቅም፤ ክውን፤ ጠፈፍ ያለ ሥራ ይዘው እንደሚቀርቡ ምስክርም ነኝ። ድንቅ ሙያ ነው መምህርነት። የበጎ አድራጎት የልጆች ብትጀምር ታሳካውም ነበር። ለመብት ለልጆች የሚቆም ተቋም ኢትዮጵያ ያስፈልጋታል ብዬ በጽኑ አምናለሁ። ለዚህ ደግሞ ምርጫየ መስኪ ናት። 
 
#የሆነ ሆኖ።
 
ብልጽግና ብዙ ሴት ሊቃናት አሉት። መስኪን ከመሰለ ፖለቲከኛ ጋር የሙግት መድረክ ከፍቶ ነፍሴን በህይወት እያለሁ ያረካታል ብየ ሳስብ መስኪ ለካቴና ተሰጠች። በተደጋጋሚ። የመጀመሪያው የእስር ፍቺ ላይ ነበር ለየት ያለ መንገድ እንድትከተል ሃሳብ ያቀረብኩላት። የሆነ ሆኖ ……
 
! ትውልድ #ከካቴና አይማርም። ከካቴና #ፍርሃት፤ ፤#ሥጋት እና የሥነ - ልቦና ችግር፤ በራስ ያለመተማመን ስውር በሽታ ነው የሚታፈሰው። ይህ ደግሞ ለማግሥት አይጠቅምም።
 
#የመስኪን የፖለቲካ አቋም ወሳኟ እሷው ናት። 
 
የምታውቀውም እሷው ናት። እኔ ግን ትዳሯ፤ ልጆቿ፤ ወላጆቿ ሲንገላቱ ማየት ውስጤን ያመዋል። አዲስ ታዳጊ ወጣቶች ከመስኪ ጥንካሬ ሊማሩ እንዳይችሉም #የካቴና ስጋት ይገድበዋል። ይህን የሚያስታርቅ ሆደ #ሰፊ ፖለቲካ ኢትዮጵያ ያስፈልጋታል ብዬ አስባለሁኝ። ለዚህ ያብቃን አሜን።
 
ሌላው በዘመነ ህወሃት እስረኛ የነበረ ዛሬም እስረኛው ጋዜጠኛ አባይ ዘውዱ ነው። አሁን ከፋኖ የተወሰነው ኃይል የህወሃት ጋር ለመሥራት ዳርዳርታውን ሲሰማ ምን ይል ይሆን???? ሊደግፈው ወይንስ ሊቃወመው? ይህን የሚወስነው እሱ ነው። በሌላ በኩል የጭካኔ ዶግማ ከአቶ ስብኃት ነጋ ትውልድ ይማር ዘንድ #ውይቡ፥ የወረዛውን መንገድ ሲያዳምጥ ምን ይል ይሆን? በእሱ ልቦና በፍጽምና "ጀግንነት" የሚያስበው ሰብዕና አለ። 
 
ስለእሱ ያለውን አሁናዊ ሁነት ሲሰማ ምን ይል ይሆን? እሱ ለታሰረት ዓላማ ተስፋው ስለመቀጠሉ፤ ወይንም ስለመንኮላሸቱስ ያስብበት ይሆን? ቃለ ምልልስ ሲያደርግ ኳች እንደሚያስፈልገው አስብ ነበር። ችግሩ ኢትዮጵያ ያሉም ይሁኑ ውጭ ያሉ የፖለቲካ ትጉኃንን ለማግኜት ሰማይ ደጅ ነው። ስለዚህ መረዳዳት፤ መደማመጥ አልተቻለም።
 
#የሆነ ሆኖ???
 
ባለቤቱ፤ ልጆቹ፤ ትዳሩ ተስፋቸው የእስረኛ ስንቅ ማመላለስ ሲሆን ያሳዝነኛል። ጋዜጠኞች አይደለም ኢትዮጵያ እየኖሩ ውጪ አገርም በአቀራረብ ዘይቤያቸው ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል ብዬ አስባለሁኝ። በሁለት ምክንያት።
 
1) ተጨማሪ #ተቀናቃኝ መፍጠር ስለማይበጅ።
2) አክሰሱ ላላቸው ታዳጊ ወጣቶች የጋዜጠኝነት ተስፋ ላይ #አሉታዊ ተጽዕኖ ስላለው። 
 
በአቀራረብ ዘይቤ የቃላት ምርጫ ጥንቃቄ በብርቱ ያስፈልጋል። አሁን የጋዜጠኛ አባት ታዲዮስ ታንቱ የችግር ምንጭ ቃለ ምልልሳቸው ሳይታረም ለህዝብ ስለሚቀርብም ነው። ዕውነት ሁልጊዜ አልጋ ባልጋ አይደለም። የጊዜ ማዕቀፍ ይወስነዋል። ኤዲቲንግም የለመድ ያለበት የሙያው ግዴታ ነው። ኮርሱ ላይ እያንዳንዷ ከዶት ያነሱ የትንፊሽ፤ የምራቅ፤ መውጣት እና መውረድ መታረም ይኖርበታል።
 
ለነገሩ በኢትዮጵያ የሚዲያ ታሪክ #ኤዲቲንግ የተለመደ አይመስለኝም። ሥራው አድካሚ ነው። የደፈረውም የለ። እንደአለ ስለሚቀርብ ለማድመጥ ይከብዳል። ላይፍ ላይ ምንም ማድረግ አይቻልም። ኩርኩሩም ይቻል ይሆናል። አድሮ ውሎ ለሚደመጥ ቅን ከኤቲክስ ውጭ ነው ኤዲት ሳዬደረግ አንድን የድምጽ ቅጂ ማቅረብ።
 
ትውልድ ወላጅ እስር ቤት ሆኖ እንደምን ይማር? ቁልፋ ጥያቄ ይህ ነው። ልጆች የአባትን፤ የእናትን እቅፍ ጠረን፤፦ትንፋሽ ሲያጡ በሥነ ልቦናቸው ላይ ምን ይከሰታል። መንግሥትም ፖለቲከኞችም በጥንቃቄ ሊያስቡበት ጉዳይ ነው። በአንድ ሚዲያ አየው የነበረ ጋዜጠኛ ቴወድሮስ ዘርፋ በአጠያዬቁ ስታይል #እሰጋለት ነበር። በአዲስ ስታዲዮ ሥራ ጀመረ። ለካቴና በቃ። ጠንቃቃነት ያተርፋል እንጂ አያከስርም። #ቸር #ያሰማን። አሜን። 
 
ሌላው ጥሞና ለየትኛውም ህይወት #ጥሞና ያስፈልጋል። 
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergure©Selassie
21/12;2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።