#በፋኖነት ተጠርጥረው ካቴና ላይ የሚገኙ ወገኖቻችን በርካታ ናቸው። ምህረት #ሰፊነትን ይጠይቃል።
#ምዕራፍ ፲፯
ፋኖነት የዘመናት ትውፊት ነው። ትውፊቱ በየዘመኑ ኢትዮጵያዊነትን የታደገ ባለውለታ ነው። በዘመነ አብይዝም በብልጽግና እና በህወሃት በነበረው የፋመ ጦርነት ፋኖነት ብልጽግናን የታደገ ባለውለታ ነበር። ከህወሃት ጋር ብልጽግና ባደረገው ድርድር ግን ተገፋን በሚል ስሜት ፋኖነት ዱር ቤቴ ካለ ዓመት አህዱ፤ ዓመት ክለቱ፤ ዓመት ሠለስቱ እያለ ቀጥሏል።
ፋኖነትን በሚመለከት #አውድዮ ሠርቼ ዩቱብ ቻናሌ ላይ ስላለ መዘርዘር አያስፈልገኝም። ዕይታየን የፈቀደ ዩቱብ ቻናሌ ላይ ያገኜዋል። የሆነ ሆኖ በተገፋን ስሜት፤ በተገለልንም የውስጥነት ቁጭት፤ በተጨማሪ የአማራ ፖለቲካዊ ጭብጦች ፖለቲካዊ ጉዳዮች፤ አጋጣሚውን በመዳፍ ለሚፈቅዱ ፖለቲከኞችም ሁነውበት፤ በፋኖ ምክንያት ብዙ የአማራ ልጆች ለካቴና ተዳርገዋል።
አሁን በቅርቡ በአንዱ የፋኖ ድርጅትን አሻም ያለ የካፒቴን ፻ ዓለቃ ማስረሻ ሰጤ ድርድር ከብልጽግና ጋር አድርጓል። በፋኖ ምክንያት የታሠሩትስ በዚህ ሂደት መፍትሄ ይሰጣቸው ወይንስ #አይሰጣቸው የሚታወቅ ነገር የለም።
ሁሉም እናት አለው እና የአማራ እናቶች ምህረትን፤ የምሥራች ዜና ይናፍቃቸዋል እና ፈጣሪ ይረዳቸው ዘንድ አምላኬን እለምናለሁኝ። በአፋር በርሃ ታስረው የነበሩ በሺህ የሚቆጠሩ እስረኞች ሁኔታም መረጃው የለም። በብልጽግና መንግሥት በይፋ የወጣውን ነው የለጠፍኩት። ምህረት #ሰፊነትን ይጠይቃል። ቸራችሁን ያሰማን። አሜን።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
21/12;2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ